በደቡብ አፍሪካ ሶዌቶ ግዛት በውጭ ሀገር ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ባለው ጥቃት የአንድ ኢትዮያጵያዊ ህይወት ሲያልፍ አንድ ሌላ ኢትዮጵያዊ ደግሞ ጉዳት ደርሶበት ህክምና እየተከታተለ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሀገሪቱ መንግስት ጋር በመሆን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማስቆም እየሰራ እንደሚገኝም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ እየተፈጸመ ካለው ጥቃት ኢትዮጰያውያን ራሳቸውን እንዲጠብቁ ያሳሰበ ሲሆን፥ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲም በሀገሪቱ ሀውቴን ግዛት ሶዌቶና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በትናትናው ዕለት ማሳሰቢያ ማውጣቱ የሚታወስ ነው።

ባወጣው ማሳሰቢያ፥ ከነሃሴ 23 2010 ዓ.ም ከሠዓት በኋላ ጀምሮ በሀውቴን ግዛት ሶዌቶና አካባቢው በኢትዮጵያውያን ዜጎች ንብረትና ሀብት ላይ ጥቃት መድረሱን አስታውቋል።

በአካባቢው ከሚገኙ የማህበረሰብ አደረጃጀቶችና ዜጎች ላይ በተገኘው መረጃም ጥቃቱ መፈፀሙን መረዳት እንደቻለም ኤምባሲው ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሪቶሪያ ኤምባሲ ጉዳዩን ለመንግስት አካላት ከማቅረቡ በተጨማሪ ዲፕሎማቶቹን በማሰማራት ከዳያስፖራ ፎረም ጋር በትብብር ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝም አስታውቋል።

ስለሆነም በአካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ነው ኤምባሲው ያሳሰበው።

ተጨማሪ መረጃ ዜጎችም ዜጎች በ0123462110 እና በ0123462947 የስልክ ቁጥሮች መጠቀም እንደሚችሉም ገልጿል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *