በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ሉሜ ወረዳ ኤጄሬ ቀበሌ አንድ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ የ18 ሰዎች ህይወት አለፈ።

ንብረትነቱ የመከላከያ አየር ሀይል የሆነው ሄሊኮፕተር ዛሬ ረፋድ 18 ሰዎችን አሳፍሮ ከድሬዳዋ ቢሾፍቱ መብረር ላይ እያለ ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ኤጄሬ ቀበሌ ላይ ነው የተከሰከሰው።

ባጋጠመዉ የመከስከስ አደጋ በበረራዉ ላይ የነበሩ ሁሉም ሰዎች ህይወት ማለፉን የተገለፀ ሲሆን፥ ህይወታቸውን ካጡት ውስጥ 15ቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሶስቱ ደግሞ ሲቪሎች መሆናቸው ታውቋል።


የአደጋዉ መንስኤም በመጣራት ላይ መሆኑንም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *