የአርበኞች ግንቦት ሰባት በኤርትራ አለኝ ሲል የነበረውን ወታደራዊ ካምፕ ዘግቶ ከኤርትራ ወደ አማራ ክልል እያቀና መሆኑንን በምስል የተደገፉ መረጃዎች እያመላከቱ ነው።

ግንባሩ ወታደሮቹን በሁመራ በኩል ለማሰጋባት ጉዞ መጀመሩ ከመገለጹ ውጪ ዝርዝር መረጃ አልተካተተም። ግንባሩ ይህንን እርምጃ መወሰዱን የመንግስት ሚዲያዎች ቢዘግቡትም ምን ያህል ወታደሮች፣ ወይም በምን ያህል ደረጃ የተደራጀ ሰራዊት እንደሆነ ያሉት ነገር የለም።

arebegnoch-G7-2-750x430

በተመሳሳይ የግንባሩ አመራሮች ሰራዊቱ ሰላማዊ ኑሮውን እንዲመራ ለማስቻል እየሰሩ መሆናቸውን መግለጻቸው የሚታወስ ነው። ከኤርትራ ወደ ሁመራ እያቀና ያለው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሃይል አማራ ክልል ሲደርስ ደናቅ አቀባበል ይደረግለታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከወዲሁ እየተጠቆመ ነው። ፋና የሚከተለውን ዘግቧል።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

አርበኞች ግንቦት 7 ቡድን ታጣቂዎችም ከካምፑ በመውጣት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ላይ መሆናቸው ተነግሯል። የአርበኞች ግንቦት 7 አባላቱ በሁመራ በኩል በማድረግ ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባትት ጉዞ መጀመራቸውንም የተለያዩ የኤርትራ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ የትጥቅ ትግል ማቆሙን ማስታወቁ ይታወሳል። አርበኞች ግንቦት 7 በኤርትራ ያለውን ወታደራዊ ካምፕ በመዝጋት ታጣቂዎቹ ወደ ሀገር እንዲመለሱ ያደረገውም ይህንን ተከትሎ ነው።መንግስት በውጭ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ስምምንት መድረሱ መድረሱ ተከትሎ በውጭ ሀገራት የሚንቀሳቀሱ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ መወሰናቸው ይታወሳል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

ከእነዚህም ውስጥ አርበኞች ግንቦት 7፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ)፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ እና ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ተጠቃሽ ናቸው።

መንግስትም ነፍጥ አንግበው የነበሩ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን፣ ከህረተሰቡ ጋር የሚቀላቀሉብትንና ዘላቂ ኑሮ እንዲመሩ ለማስቻልም በጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ውስጥ የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት በቅርቡ ተቋቁሟል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *