የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 53ኛ መደበኛ ስብስባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በላከው መግለጫ አመልክቷል።

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲን ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ ደንብ፣ ብሔራዊ የሎጂስቲክስ ስትራቴጂና በመንግስት ግዙፍ የልማት ድርጅቶች ውስጥ ያለውን ድርሻ በከፊል ወደ ግል ለማዛወር የተላለፈውን ውሳኔ ለማስፈጸም በተዘጋጀው ጋይድ ላይን ላይ  መክሮ ውሳኔ አሳልፏል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ መቋቋም መንግስት በውጭ ያሉ ኢትዮጵያሰዊያን እና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን በአገራችን ሁለንተናዊ  እድገት ላይ የሚኖራቸውን ገንቢ አስተዋዕኦ መሰረት በማድረግ በአሁኑ ወቅት ያለውን ተነሳሽነነት በአግባቡ በመጠቀም ሁሉም የዳያስፖራ አባላት በአገር ልማት ላይ የጋራ አቋም እንዲይዙ ለማስቻልና በመንግስት የተቀመጠውን የፖሊሲ አቅጣጫ ለማስፈጸም ይረዳል ተብሏል።

በመሆኑም የቀረበው ረቂቅ ደንብ ውይይት ከተደረገበት በኋላ አንዳንድ ማሻሻያዎችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እንዲወጣና በስራ ላይ እንዲውል ምክር ቤቱ ወስኗል።

ብሔራዊ የሎጂስቲክስ ስትራቴጂ ላይ የመከረው ምክር ቤቱ ላለፉት አስር ተከታታይ ዓመታት የተመዘገበው አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገትን ተከትሎ የገቢና የወጭ እቃዎችና የአገር ውስጥ የንግድ እንቅስቃሴ በመጠንና በአይነት በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ እንደሆነ ተመልክቷል።

በመሆኑም በአገራችን የውጭ ንግድ ልማት ለመደገፍ መከናወን ካለባቸው ቁልፍ ተግባራት ውስጥ ዋናው ቀልጣፋና ውጤታማ የሎጂስቲክስ ስርዓት ለመዘርጋት ብሔራዊ የሎጂስቲክስ ስትራቴጂ በስራ ላይ አንዲውል ምክር ቤቱ ወስኗል።

ምክር ቤቱ በመጨረሻም በመንግስት ግዙፍ የልማት ድርጅቶች ውስጥ ያለውን ድርሻ በከፊል ወደ ግል ለማዛወር የተላለፈውን ውሳኔ ለማስፈጸም በተዘጋጀው ጋይድ ላይን ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ የተወያየበት የፕራይቬታይዜሽን ፕሮግራሙ የሚመራበትን የአሰራር ስርዓት የሚያመለክት ጋይድ ላይን በስራ ላይ እንዲውል ምክር ወስኗል።

ጽህፈት ቤቱ የላከው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 53ኛ መደበኛ ስብስባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

ምክር ቤቱ የተወያያው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲን ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ሲሆን የኤጀንሲው መቋቋም መንግስት በውጭ ያሉ ኢትዮጵያሰዊያን እና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን በአገራችን ሁለንተናዊ  እድገት ላይ የሚኖራቸውን ገንቢ አስተዋዕኦ መሰረት በማድረግ በአሁኑ ወቅት ያለውን ተነሳሽነነት በአግባቡ በመጠቀም ሁሉም የዲያስፖራ አባላት በአገር ልማት ላይ የጋራ አቋም እንዲይዙ ማስቻልና በመንግስት የተቀመጠውን የፖሊሲ አቅጣጫ ለማስፈጸም የሚረዳ ተቋማዊ አደረጃጀት እንዲኖር ለማድረግ ረቂቅ ደንቡ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ አንዳንድ ማሻሻያዎችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እንዲወጣና በስራ ላይ እንዲውል ምክር ቤቱ ወስኗል።

ብሔራዊ የሎጂስቲክስ ስትራቴጂ ሌላው በምክር ቤቱ የታዬ ጉዳይ ነው። ላለፉት አስር ተከታታይ ዓመታት የተመዘገበው አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገትን ተከትሎ የገቢና የወጭ እቃዎችና የአገር ውስጥ የንግድ እንቅስቃሴ በመጠንና በአይነት በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ነው። በመሆኑም በአገራችን የውጭ ንግድ ልማት ለመደገፍ መከናወን ካለባቸው ቁልፍ ተግባራት ውስጥ ዋናው ቀልጣፋና ውጤታማ የሎጂስቲክስ ስርዓት ለመዘርጋት ብሔራዊ የሎጂስቲክስ ስትራቴጂ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ስትራቴጂው በስራ ላይ አንዲውል ምክር ቤቱ ወስኗል።

ምክር ቤቱ በመጨረሻም የተወያየው በመንግስት ግዙፍ የልማት ድርጅቶች ውስጥ ያለውን ድርሻ በከፊል ወደ ግል ለማዛወር የተላለፈውን ውሳኔ ለማስፈጸም በተዘጋጀው ጋይድ ላይን ላይ ሲሆን የፕራይቬታይዜሽን ፕሮግራሙ የሚመራበትን የአሰራር ስርዓት የሚያመለክት ጋይድ ላይን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ጋይድ ላይኑ በስራ ላይ እንዲውል ምክር ቤቱ ወስናል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *