በታለመና በታቀደ መልኩ አገሪቱን በብሄር ግጭት ለማተራመስ በገንዘብ ሃይል የተደራጀው የህቡዕ ሃይል አንድ ቲም መሪዎች ከሙሉ መረጃዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉ ታወቀ። በአዲስ አበባ አምስት ሰዎች መገደላቸው ተሰማ።

በተደጋጋሚ ራሳቸውን ተራ ሌቦች በማስመሰል አገሪቱን ለማፈራረስ ሲነቀሳቀሱ የሚታዩት ወገኖች በቁጥጥር ስር የዋሉት በተሽከርካሪ ያጅበው የሚመሩትን አንድ ቡድን ሲያሰማሩ ነው። የቡራዩ የዛጎል ምንጮች እንዳሉት እነዚህ በቁጥጥር ስር የዋሉት የነውጥ አቀነባባሪ ሃይል አንድ ክንፍ ወይም ቡድን አመራሮች ናቸው። ሲያዙም የእጅ ቦንብ፣ ሽጉጥ፣ ክላሽና የነብስ ወከፍ መሳሪያዎች ተይዞባቸዋል።

የአገሪቱን ህዝብ እርስ በርስ ለማተራመስ ከየብሄሩ እየመረጡ ጥቃት የሚያደርሱት የተደራጁ ሃይሎች አካል የሆነው አንድ ቡድን ከዘጠና እስከመቶ የሚሆኑ ነብሰገዳይ አባላትን የሚያሰማራ እንደሆነ የቡራዩ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ሃላፊ ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክ ሲናገሩ ተሰምተዋል። እሳቸው ዛሬ ይህንን ይበሉ እንጂ የክፋት ወንጀሉ ሰላባ ከሆኑት መካከል አንድ እናት መቶ የሚጠጉ ይሆናል ሲሉ ለመንግስት ቲቪ ተናግረው ነበር።

የቡራዩ መረጃ አቀባዮች እነዚህ የተገዙ የሽብር ሃይሎች በወጉ የታጠቁ፣ በአንዳንድ የበታች መዋቅር የሚታወቁ፣ የታቀደ ዓላማ ያላቸው፣ የኦሮምኛ ተናጋሪ ቢሆኑም የኦሮሞን ህዝብ ግራ የሚያጋቡና የማይወክሉ ስለሆኑ በፍርሃቻ ራሳቸውንና አካባቢያቸውን ለመጠበቅ ራሳቸውን ለማደራጀት መገደዳቸውን ተናግረዋል።

በአዲስ አበባና በቡራዩ አካባቢ ወደ ሰባት መቶ የሚጠጉ ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል። አሁንም ህዝቡ በሚያደርገው ጥቆማ መሰረት ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ እየተያዙ ነው። ፖሊስ እንዳለው እነዚህ ሃይሎች የተገዙ መሆናቸው ማሰረጃ ተገኝቷል። ይሁን እንጂ ማን ገዛቸው ለሚለው ምላሽ አልሰጠም።

ይህ በንዲህ እንዳለ ዛሬ ይህንን ተግባር ለመቃወም አደባባይ ከወጡ ሰልፈኞ መካከል አምስት መገደላቸውን ፖሊስ ይፋ አድርጓል። ይህም የሆነው በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በፒያሳና በመርካቶ ዝርፊያ ለመፈጸም ሙከራ በመታየቱ፣ የጦር መሳሪያ የያዙና ከጸጥታ አስከባሪዎች ላይ መሳሪያ ለመንጠቅ ሙከራ ብመደረጉ ነው። ከሞቱት በተጨማሪ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸውም አሉ።

በተመሳሳይ ዜና ሰባት የሚሆኑ የፖለቲካ ደርጅቶች እነዚህ ተገዝተው አገሪቱን ለማተራመስ የተነሱ ሃይላት ተለይተው እንዲታወቁና ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ ከህግና ስርዓት ውጪ በሚንቀሳቀሱ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በአንድነት ጠይቀዋል። በተለያዩ ደረጃ ያሉ የክልልና የፌደራል አስተዳደር አካላት፣ መሪዎች፣ እንዲሁም ፖሊስና የአዲስ አበባ አስተዳደር መንግስት በህገወጦች ላይ የያዘው ትዕግስት መሟጠጡንና ካሁን በሁዋላ እንደማይታገስ አሳውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ህዝቡ ያገኘውን ድል ለማስጠበቅ በማስተዋል እንዲንቀሳቀስ በተደጋጋሚ መጠየቃቸው አይዘነጋም። አቶ ለማ መገርሳም የአገሪቱ ፖለቲክ ቀናነት የጎደለው የሸር በመሆኑ ህዝቡ ሊማር እንደሚገባወ፣ አቶ ገዱ በበኩላቸው ህዝብ ባለመተባበሩ ለባርነት ተዳርጎ መኖሩን፣ በተለያየ ወቅቶች በማሳሰቢያ መልክ መናገራቸው አይዘነጋም። ዶክተር መረራ ደግሞ በትናንትናው እለት ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በአስቸኳይ ሁሉን ያካተተ የሽግግር ስርዓት ካልተዘጋጀ ጉዳዩ ወደ ከፋ ደረጃ ሊደርስ እንደሚችል ቅድሚያ ትንቢት ሰጥተዋል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *