በናይጄሪያ አስር ግዛቶች ውስጥ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ100 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካታ ቤቶችንም ከጥቅም ውጪ አድርጓል፡፡

ይህንን ተከትሎም የሀገሪቱ የብሄራዊ አደጋ ኤጀንሲ በአራት ግዛቶች ማለትም በኮጊ፣ ኒጀር፣ አናምብራ እና ዴልታ ግዛቶች ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ አውጇል፡፡

ዴልታ በነዳጅ ምርቷ የምትታወቅ ግዛት ሲሆን ከዚህ ጋር ተያያዘ የደረሰ አደጋ ስለመኖሩ የተባለ ነገር የለም ተብሏል፡፡

በዝናብ የተጠቁት ሁለቱ ግዛቶች በማዕከላዊ የሀገሪቱ ክፍል ይገኛሉ፤ ቀሪዎች ደግሞ በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

በአውሮፓውያኑ 2012 ተመሳሳይ የጎርፍ አደጋ ተከስቶ የ140 ሰዎችን ህይወት ሲነጥቅ በአስርሺዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ ማፈናቀሉ የሚታወስ ነው፡፡

በናይጄሪያ የዝናብ ወቅት ከመስከረም ጀምሮ እስከ መጋቢት ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን በዚህም ከፍተኛ የሆነ የጎርፍ አደጋ እንደሚያስከትልም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *