በሶርያ የአየር ክልል ውስጥ የነበረች 14 ሰዎችን የያዘች የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላን የደረሰችበት አልታወቀም፡፡ወታደራዊ አውሮፕላኗ በምን ምክንያት እንደወደቀቸች እስከአሁን ይፋ ያደረጉት ነገር የለም ተብሏል፡፡

ሆኖም ሲኤንኤን የአሜሪካ ባለስልጣናት ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ በሶሪያ ወታደራዊ ኃይሎች ኢላማ መደረጓን ጠቅሰዋል፡፡

የሶሪያ ወታደራዊ ኃይሎች አውሮፕላኗን ኢላማ ያደረጓትም በስህተት ሲሆን በወቅቱ እስራዔል በአራት ኤፍ 16 ጀቶች የአየር ጥቃት እየፈጸመች እንደነበር የሩሲያ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡

ሆኖም የእስራዔል ወታደራዊ ቃልአቀባይ ስለጉዳዩ ምንም አስተያየት አልሰጡም ፡፡

በተጨማሪም አሜሪካንና ፈረንሳይ ከጉዳዩ ጋር ስማቸው የተነሳ ሲሆን ሁለቱም ከጉዳዩ ጋር ምንም የሚያገናኛቸው ነገር ያለመኖሩን ጠቅሰዋል፡፡

በአውሮፓውያኑ 2015 ቱርክ በሶርያ ድንበር የሚገኝን አውሮፕላን መታ መጣሏ የሚታወስ ሲሆን በዚህም ሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማቋረጥ በቅተው ነበር፡፡

ምንጭ፦አልጀዚራ -ኤፍ.ቢ.ሲ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *