አቶ ጌታቸው ረዳ የሚባሉት የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የኦሮሞ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ነኝ የሚሉት ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ገቢሳ መገናኘታቸውን የሚሳየው ምስል ይፋ ከሆነ በሁዋላ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። ምስሉ በተለይ ኦነግን ሲራገሙና ስሙን እንኳን ላለመጥራት ሲጠየፉ የነበሩ የህወሃት ደጋፊዎች በቅጽበት የኦነግ ደጋፊዎች መሆናቸው በሚያስተጋቡበት በዚህ ወቅት መሆኑ ደግሞ አጀንዳውን አግዝፎታል።

አቶ ጌታቸው “ኦሮሞና አማራ እንዴት አንድ ሊሆን ቻለ” በሚል በንዴት የድርጅታቸው ጥፋት እንደሆነና ይህ ሊሆን የማይገባው፣ የማይታመን ጉዳይ እንደሆነ ሲናገሩ የሚያሳብቅ ቪዲዮ ከተሰራጨ በሁዋላ ከድርጅታቸው ውጪ ወዳጅ አልባ ናቸው። ሕዝቅኤል ጋቢሳም በአክራሪ አመለካከታቸው ነጥብ ያለባቸው መሆናቸው ሁለቱ ምን አገናናቸው የሚል ጥያቄ እንዲነሳ ምክንያት ሆኗል።

ጉዳዩ በሌሎች ብሄረሰብ አባላት ብቻ ሳይሆን የቅርብ ጊዜውን ሊረሳ የማይችል ጠባሳ እያሰቡ በሚነዝራቸው የኦሮሞ ተወላጆች ዘንዳም በመልካም አልታየም። ጊዜው ሁሉም በአፉና በጉያው የያዘውን ” መርዝ” የሚተፋበት ወቅት በመሆኑ የሚሆነውን ማየት መልካም ነው የሚሉም አሉ። 

ፎቶ ዘ- ሃበሻ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *