አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ነገ እንደሚዘጋ በኦፊሳል የቲውተር ገጹ አስታወቀ። ኤምባሲው ይህንን ያስታወቀው በነገው ቀን በአዲስ አበባ ከፈተኛ ሰልፍ ይደረጋል በሚል ለጥንቃቄ ነው።

በመልዕቱ ማሳረጊያ ኤምባሲው በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የሚሳተፉ ሃሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲገልጹ መክሯል። ስለ ሰልፉ ሁኔታ በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የብሄራዊ የድሀንነት ምክር ቤት ዛሬ ጥብቅ መግለጫ ማውጣቱ አይዘነጋም። በመግለጫው ካሁን በሁዋላ ሀገወጦችን መታገስ እንደማይችል፣ ሊታገስ የሚችልበት አንጀትም እንደሌለው አመልክቷል። መንግስት ትዕግስት እንደሌለው ያስታወሰው መግለጫው የአገሪቱ የጸጥታ ሃይል አስፈላጊውን የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑንን፣ እርምጃ መጀመሩንና እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስቧል።

2018-09-18 (2)

የተቃዋሚ ፓርቲዎች በህብረት ሆነው መንግስት ህገወጦች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርበዋል። ይህ ነገ ተጠራ የተባለው የተቃውሞ ሰልፍ በማን እንደተጠራ፣ ሕጋዊ ፈቃድ እንዳለውና እንደሌለው እስካሁን በይፋ አልተገለጸም። ይሁን እንጂ ሰሞኑንን በቡራዩና አካባቢው የተከሰተውን ዘግናኝ ድርጊት አስመልክቶ እንደሚሆን ይገመታል። 

ሰልፉ ጥንቃቄ የተሞላበት፣ ስርዓትን የተከተለ፣ አላማውን የማይስትና ለሌሎች ቡድኖች መጠቀሚያ እንዳይውል ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ የሁሉም ጤነኛ ዜጎች እምነት ነው። ከዚህም በተጨማሪ አሁን መረጋጋት በሚያስፈልግበት ወቅት ወደ አልተፈለገ መተራመስ ላለመግባት ሃላፊነት የሚሰማቸው ወገኖች በሙሉ በየቄያቸው ወጣቶች ወዳልተገባ ተግባር እንዳያመሩ ሊያስጠነቅቁና ሊከላከሉ ይገባል።

ፖሊስ የተገዙ ቡድኖች አገሪቱን በየአቅጣጫው ወደ ብጥብጥ ለመክተት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን መግለጹ አይዘነጋም። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም ህዝብ ልቡን እንዲጠብቅ፣ ሃሳቡን እንዲሰበስብ፤ የፖለቲካ ድርጅቶችም በተፈጠረው መድረክ ተጠቅመው ሃሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲያራምዱ ዛሬ እረፋዱ ላይ ምክር መለገሳቸው አይዘነጋም።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *