” አብረን አፈር ፈጭተን ነው ያደግነው። አባቴን መቱት። አባቴን ጎዱት ብሎ ሲደውልኝ ራሴን መቆጣጠር አቃተኝ። ከየት እንደመጡ አናውቅም። እንዲህ ያለውን ድርጊት የሚፈጽሙት የተገዙ ወንጀለኞች ያደረሱት ጥፋት ከሚወራው በላይ ነው። ግን አስቀድሞ ምልክት ስለነበር ፖሊስም ሆነ አስተዳደሩ የሚቀርብለትን አቤቱታ ለመስማትና እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ አልነበሩም” ይላል የጓደኛውን ስም እየጠራ በቁጭት የሚናግረው ወጣት።

” ቡራዩ አስተዳደር አላት እንዴ” ሲል በፌስቡክ ገጹ የሚጠይቅ የቡራሩ ወጣት እንደሚለው በርካቶች ይህንን ጥያቄ ያነሳሉ። ዛሬ የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ  ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በፌስ ቡክ ገጻቸው እንዳሉት ከሆነ የህዝብ ቅሬታና ቡራዩ አስተዳደር የላትም ወደሚል ድምዳሜ መድረሳቸው ትክክል ይመስላል።

እሳቸው እንዳሉት ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ የጸጥታ አካላትና የስራ ኃላፊዎችም በቁጥጥር ስር ወለዋል። ከየትኛው የእርከን ደረጃ እንደሆነ ባይታወቅም በቁጥጥር ስር የዋሉት ሃላፊዎችና የጸጥታ አካላት በስም አልተገለጹም። የኦሮምያ ፖሊስም ሆነ የጸጥታ አካሉ ባሳየው ቸልተኝነት፣ እንዲሁም ባቀረበው ሰንካላ ምክንያት የተነሳ ሰፊ ተቃውሞ ሲሰነዘር መሰንበቱ ይታወሳል።

በኦሮሚያ፣ በሶማሌ ክልል፣ በሃዋሳ እና በሌሎች ስፍራዎች በውክልና የሚካሄደውን አገር የማተራመስ ድርጊት አኩራፊ ሃይሎች፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥቅማቸውን ያጡ ቡድኖች አሁን በስራ ላይ ያለውን አስተዳደር ” አገር መምራት አልቻለም” በሚል ወንጅሎ የመንግስት ግልበጣ ለማካሄድ የታለመ ሴራ መሆኑ በተደጋጋሚ እየተጠቆመ ነው።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *