የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ህብረተሰቡ በማህበራዊ ድረ ገፅ በሚለቀቁ መረጃዎች ተደናግሮ ለሁከትና ግጭት በር መክፈት እንደሌለበት አሳሰበ።

ኮሚሽኑ በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጠው መግለጫ፥ ከምንግዜውም በበለጠ ለዜጎች ሰላምና ደህንነትና ለህግ የበላይነት መረጋገጥ ክሌሎች የፀጥታ ሀይሎች፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከመከላኪያና ከመላው ህብረተሰብ ጋር እየሰራ እንደሆነ ገልጿል::

ኮሚሽኑ፥ በድሬዳዋ ከተማ በአንዳንድ አካባቢዎች በቤቶች ላይ ምልክት መደረጉን ተከትሎ ምልክቱ የጥቃት ነው በሚል በማህበራዊ ድረ ገፅ ስጋት ፈጣሪ ሀሳቦች መሰራጨታቸውንም በመግለጫው አንስቷል።

በመሆኑም የአስተዳደሩና የፌዴራል የፀጥታ አካላት ከትላንት ጀምሮ ማን ለምን አላማ ምልክቱን እንዳደረገ በመከታተል ጎን ለጎንም የተጠናከረ ጥበቃ እያደረጉ መሆኑን የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብ ግኑኝነት ዲቪዥን ሀላፊ ዋና ሳጅን ባንታለም ግርማ ገልፀዋል።

እስከ አሁን በተጨባጭ የተፈጠረ ችግር የለም ያሉት ዋና ሳጂን ባንታለም ግርማ ህብረተሰቡ በማህበራዊ ድረ ገፅ በሚለቀቁ መረጃዎች ተደናግሮ ለሁከትና ግጭት በር ሳይክፈት የለት ተእለት ሠላማዊ ኑሮውን ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በከተማዋ ሁከት ለመፍጠር የሚፈልግ አካል ካለም በድሬዳዋ የማይሳካ መሆኑንና ፖሊስም የማይታገስ መሆኑን አውቆ ከጥፋት ድርጊት እንዲታቀብ አሳስበዋል።

ህብረተሰቡ ስጋት ፈጣሪ እንቅስቃሴዎች ባየ ጊዜ በ025 111 16 00 እና በ025 111 52 11 ስልክ ቁጥሮች ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥም ዋና ሳጅን ባንታለም ግርማ ጠይቀዋል።

በተያያዘ ሀምሌ 29 2010 ዓ.ም በድሬዳዋ ለ13 ንፁሀን ዜጎችና ህልፈትና ለንብረት መውደም ምክንያት የሆነውን ሁከት ተከትሎ ፖሊስ የደረሰበትን የምርመራ ውጤት የፊታችን ማክሰኞ ለሕዝብ በይፋ የሚገለጽ መሆኑን ዋና ሳጅን ባንታለም ግርማ አሳውቀዋል ።

መረጃውን ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ነው ያገኘነው። EBC

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *