ዛሬ ፓርቲ መሆኑን ያወጀው ኦህዴድ አስራ አራት ነባር አመራሮችን በክብር መሸኘቱን ይፋ አድርጓል። ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ / ኦዴፓ በሚል ስያሜ እንዲጠራ የወሰነው ኦህዴድ በጅማ እያካሄደ ባለው 9ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ ነው ነባር አመራሮቹን በክብር ያሰናበተው። የተሸኙት ነባር አመራሮች የምስክር ወረቀ ወስደዋል።

አቶ አባዱላ ገመዳ
አቶ ጌታቸው በዳኔ
አምባሳደር ኩማ ደመቅሳ
አምባሳደር ግርማ ብሩ
አምባሳደር ድሪባ ኩማ
አቶ እሸቱ ደሴ
አቶ ተፈሪ ጥያሩ
አቶ ሽፈራው ጃርሶ
አምባሳደር ደግፌ ቡላ
አቶ አበራ ሀይሉ
አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ
አቶ ኢተፋ ቶላ
አቶ ዳኛቸው ሽፈራው
አምባሳደር ጊፍቲ አባሲያ ተሰናባቾቹ ናቸው።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ስንብቱን የሰሙ ” ህወሃት በማይደርስበት ቦታ አስቀምጡዋቸው” በሚል  በማህበራዊ ገጾች በፌዝ ስሜታቸውን እየገለጹ ነው።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *