የአዲስ አበባ ልጆች በመታሰራቸው ሁላችንም አዝነናል። እስራቱ ከ ዶክተር ዐብይ ጋራ አይገናኝም። ሆኖም የሚታሰሩት አንድ የሚጣራ ነገር ስለአለ ነው። ያ ነገር ከተጣራ በኋላ ብዙሀኑ ይፈታሉ። ጉዳዩ እንደሚከተለው ነው። —

አንደኛ፥ ኦሮሞና አማራን ለማጋጨት፥ ሁለተኛ ዶክተር ዐብይን ደካማ አስመስሎ ለማሳየት እና አሳይቶም ማስተዳደር አልቻልክምና ስልጣን ልቀቅ ለማለት የስልጣን ጥመኞች የቡራዩን ግድያ አቀዱ። አቅደውም ፈጸሙት። ከእዛም በአደስ አበባ ወጣቶች ሰልፍ ውስጥ ሰርገው ገብተው የኦሮሞ ንብረቶችን በድንጋይ ደበደቡ።

የአዲስ አበባ እና የፌዴራል ፓሊስ ኮሚሽነሮች እንደነገሩን እነዚህ የስልጣን ጥመኞች ሁለት አይነት ሽብርተኞችን አገንዝበው (ገንዘብ አስጭነው) እና መሳሪያ አስታጥቀው ወደቡራዩ ላኩአቸው። አንደኛው ግንቦት 7 ን ተመስሎ አማርኛ የሚናገር፤ ሁለተኛው ኦነግን ተመስሎ ኦሮምኛ የሚያወራ።

በመጀመሪያ አማርኛ የሚናገረው ሽብርተኛ ግንቦት 7 ትን ተመስሎ አማርኛ እየተናገረ በ ቡራዩ ፊትለፊቱ ያገኛቸውን የተወሱኑ ኦሮሞዎች ገደለ። ቀጥሎ፥ ኦሮምኛ የሚናገረው ሽብርተኛ ኦሮምኛ እያወራ ኦነግን ተመስሎ በየቤቱ እየገባ አማራን እና ጭዳ የሆኑለትን የደቡብ ሰዎች ያለርህራሄ አረደ። ንብረትም ዘረፈ።

ይህን በመቃወም የአዲስ አቧ ወጣቶች ሰልፍ ሲወጡ ሽብርተኛው ተቀላቅሏቸው የኦሮሞን ንብረት እየመረጠ ጎዳ። ከዛ በኋላ ከፍተኛ ሰልፍ በአሜሪካን ኤምባሲ አካባቢ ለማስደረግና ሰርጎ ገብቶ ቀውጢ ለመፍጠር አሴረ። ዳሩ ግን የመጀመሪያውን ሰልፍ ተከትሎ የአዲስ አበባ ልጆች በመታሰራቸውና መንግሥት ሴራውን አውቆ ሰልፉን በማገዱ እቅዱ ሳይሳካለት ቀረ። ቢስካለት ኖሮ ወጣቶቹ መሀል ገብቶ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙትን የኦሮምያ ተቋማትን እና ንብረቶችን፣ ቤተመዘክሩን ጭምር፥ አመድ አድርጎ፥ ይህን ያደረጉት የግንቦት 7 እና ሌሎች አማሮች ናቸው ብሎ እነሱ ላይ አላክኮ ኦሮሞን እና አማራን በመላው ሀገሪቱ ሊያፋጅ ነበር። እግዚአብሄር ግን እንዲህ እንዲሆን አልፈቀደም።

ነገሩ እንዲህ የከረረ በመሆኑ ሽብርተኞቹ ተጣርተው እስኪለዩ ድረስ ይህን ሴራ የማያውቁት የአዲስ አበባ ልጆች በጅምላ ታፍሰው ታስረዋል። ሽብርተኞቹ እየተመረመሩ ከ 500 በላይ ተይዘዋል። ግን ገና ያልተያዙ ስለአሉ እነሱ ሲያዙ ንጹሆቹ የአዲስ አበባ ልጆች ይፈታሉ ማለት ነው። ይህ ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እኔ አላውቅም። ቶሎ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ። ከፓሊስ ለ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይም የተነገረው ይህ ስለሆነ የፓሊሶቹን ምርመራ እንዳያደናቅፍ ብሎ እሱም የልጆቹን ባፋጣኝ መፈታት እንደሚጠብቅ ነው ለኔ የተረዳኝ። ስለእዚህ ዶክተር ዐብይ አምባገነን ሆነ የምንለው ተሳስተናል። እሱ በምንም መንገድ አምባገነን ሊሆን አይችልም። የተፈጥሮ ባህሪው አይፈቅድለትም። ችግሩ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ ብቻ ነው።

እንግዲህ እርስበርሳችሁ የምትወነጃጀሉት የአዲስ አበባ ወጣቶች (ኦሮሞና አማራን ጨምሮ) ሴራውን ተረድታችሁ ተግባብታችሁ በፍቅር እና በአንድነት ቁሙ እንጂ እርስበርሳችሁ አትወነጃጀሉ፤ እንዲሁም አትጋጩ።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *