የአማራ ብሄራዊ ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ ምርጫ ትኩረት የሳበው “ሕዝብ በማይፈልጋቸውና በትክክል ሊወክሉት የማይችሉ አመአርሮች የተሰገሰጉበት ነው” በሚል ተቃውሞ ባየለበትና ፓርቲው አፈጣጠሩን ሙሉ በሙሉ የቀየረበት ወቅት በመሆኑ ነበር። ይህንኑ መነሻ በማድረግ በተለያዩ የማህበራዊ ገጾች የስም ዝርዝር እየተለቀመ እንዲሰናበቱ ዘመቻ ሲካሄድም ነበር።

ፓርቲው ይፋ ባደረገው መሰረት አስራ ሶስት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት  ለምርጫ ሳይቀርቡ እንዲሰናበቱ ለጉባኤው አቅርቧል። የተለያዩ ምክንያቶችን በመንተራስ በቀረበው ዝርዝር መሰረት ጉባኤው ከውስጥ፣ ህዝብ ከውጭ ባደረጉት ጫና አቶ ደመቀ መኮንን በነበሩበት እንዲቀጥሉ ተወስኗል።

የተቀሩት አስራ ሁለቱ ግን ” ባይወዳደሩ” በሚል ፓርቲው ባቀረበው ሃሳብ ላይ ጉባኤው ያለማቅማማት ውሳኔ አሳልፏል። በውሳኔው መሰረት ፓርቲውን ለረዥም ዓመታት ሲመሩ የነበሩት ለአዲሱ ምርጫ እንዳይወዳደሩ ተወስኖባቸዋል። 
በትምህርት ላይ የሚገኙና የተሰናበቱ:- 

• አቶ ዓለምነው መኮንን
• አቶ ለገሰ ቱሉ 
• አቶ ጌታቸው ጀምበር
• አቶ ኢብራሂም ሙሀመድ
• አቶ ደሳለኝ አምባው እና 
• ወይዘሮ ባንቺ ይርጋ መለሰን ባይወዳደሩ ብሎ መነሻ አቅርቧል፡፡
በክብር የተሰናበቱ፡-

• አቶ ከበደ ጫኔ
• አቶ መኮንን የለውምወሰን
• ወይዘሮ ፍሬህይወት አያሌው እና
• አቶ ጌታቸው አምባየን በክብር ቢሰናበቱ ብሎ አቅርቧል፡፡
በአምባሳደርነት እያገለገሉ ያሉ እና የተሰናበቱ፡-
• አቶ ካሳ ተክለብርሀንና 
• ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰን ከውድድሩ ውጭ ቢሆኑ ብሎ መነሻ አጸድቋል፡፡
ከውድድር ውጭ የሆኑት የቀድሞው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትም ከአሁን በኋላ በመንግስት የስራ ኃላፊነት እንደማይቀመጡ ተወስኗል፡፡
ጉባኤው ዛሬ ጠዋት 1፡30 የተሰየመ ሲሆን 65 አባላት ያሉትን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *