በሰኔ አስራ ስድስት ተካሂዶ በነበረው የቦንብ ጥቃት የኦነግ እጅ እንዳለበት የሚያሳይ ክስ ሲመሰረት፣ የግድያው ዋና አቀነባባሪ ኬንያ የምትገኝ የኦነግ አባል መሆኗ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል። በተለይም ዋና የጉዳዩ ባለቤት በሆነው ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ክስ አለመስረቱም ጥያቄ የስነሳ ጉዳይ ሆኖ ከርሟል።

አቃቤ ህግ በአምስት ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ሲመስርት ካቀረበው ዝርዝር የክስ ጭብጥ በተጨማሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ  የሰኔ 16 የቦምብ ጥቃትን በመሩ፣ ባቀነባበሩና የፋይናንስ ድጋፍ ባደረጉ ግለሰቦች ላይ ሲያካሂድ የቆየውን ምርመራ ማጠናቀቁን ለፋና ብሮድካስቲንግ ይፋ አድርጓል።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

የመጀመሪያውን ክስ ጭብጥ በመስማት ራሳቸውን ነጻ ያወጡ፣ ስማችን ጠፍቷል በይፋ ይቅርታ ልንጠየቅ ይገባል፣ ባልሰራነው ተጠርጥረናል ሲሉ ከፍተኛ ዘመቻ ሲያካሄዱ ለሰነበቱ ይህ ዜና መርዶ እንደሚሆን ይገመታል። አቃቤ ህግ ብስም ጥቅሶ ማንነታቸውን ይፋ የሚያድርጋቸው ግለሰቦች ምንነትና ማንነት፣ ከጀርባቸው ያዘሉት አላማና ተልዕኮ ለግድያው ሙከራ ሴራ ግልጽ ምላሽ የሚሰጠው ይህ የጠቅላይ አቃቤ ህግ ምርመራ ሪፖርት በዚህ መነሻ እጅጉኑ የሚጠበቅ ሆኗል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በዚህም መሰረት ጥቃቱን በማቀነባበር፣ በመምራትና በፋይናንስ በመደገፍ የተሳተፉ ግለሰቦች ማንነትና የምርመራ ውጤቱን አስመልክቶ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በሚቀጥለው ሳምንት መግለጫ እንደሚሰጥና ይፋ እንደሚያድርግ ቃል ገብቷል። መግለጫው የኢህአዴግ ጉባኤ ከመካሄዱ በፊት መሆኑም ታውቋል። የሰኔ 16 የቦምብ ጥቃት ፈጽመዋል በሚል በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ባለፈው ሳምንት ክስ መመስረቱ ይታወሳል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *