ተባረው፣ ተሰድበው፣ ተፈርጀው፣ ታስረው፣ ተንገላተው፣ ተሰደው… የነበሩ ሁሉ ኢህአዴግ ጉቤ ላይ የመሰየም አጋጣሚውን አግኝተዋል። ሊታመን በማይችል ደረጃ ሕዝብ ኢህአዴግ ውስጥ የለውጥ ሃይሎች እንዲወለዱ አድርጎ እዚህ ደረጃ ተደርሷል። ይህ አስደናቂ የፖለቲካ ፈውስ ወደ መልካም አጋጣሚ ተለውጦ በመግባባት አገሪቱን ወደ ዴሞክራሲ ጎዳና መምራት ቀላል ሆኖ ሳለ፣ አሁን የሚታየው የመንጋ ዝላይና የሸር ፖለቲካ አገሪቱን ሲንጣት ማየት የበርካታ ቀና ዜጎችን አንገት አስደፍቷል። ይህንን ታላቅ አጋጣሚ በመጠቀም መወቃቀስንና መፈራረጅን በማቆም በኩል አሸናፊነት ስሜት ከመጓዝ ይልቅ የሸር እጆች ድሃው ህብረተሰብ ላይ ያሳረፉት ጥቁር አሻራ ምንግዜም የሚረሳ አይሆንም። ከዚህ ጉባኤ በሁዋላስ…

ኢህአዴግ በጉባኤው ለውይይት ከያዛቸው አጀንዳዎች ውጭ በርዕዮተ ዓለምም ሆነ በመስመር ጉዳይ ላይ የሚደረግ ውይይት እንደማይካሄድ  አቶ ፍቃዱ ተሰማ የ11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ቃል አቀባይ አስታወቁ። ጉባኤው በመክፈቻው ከወትሮው በተለየ አገራዊ አንድነትን በማጉላት አሳይቷል። የድርጅቱ ሊቀመንበር ለልብ የሚሆንና በድርጅቱ ባህል አዲስ የተባለ ንግግር አድርገዋል።

አቶ ፍቅዱ የድርጅቱ አስራ አንደኛ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ መጀመሩን ለመገናኛ ዘዴዎች ሲናገሩ ነው ይህንን ያስታወቁት። አቶ ፍቃዱ ጉባኤው ከተጀመረም በሁዋላ በመካከሉ የርዕዮተ ዓለምም ሆነ የመስመር ጉዳይን አስመልክቶ የሚያዝ አጀንዳም እንደሌለ ነው ይፋ ያደረጉት።

በስብሰባው ላይ የርዕዮተ ዓለምና የመስመር ልዩነት ጉዳይ ኢህአዴግን ሊያፈረው እንደሚችል፣ ሶስቱ እህት ድርጅቶች ከህወሃት በቀር  ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ መርህ ውጪ እየሆኑ መምጣታቸው በስፋት በምሁራን ሳይቀር ማብራሪያ ሲሰጡበት ሰንበተው ነበር።  ይሁን እንጂ አቶ ፍቃዱ እንዳሉት በዚህ ደረጃ የሚነሳ ጉዳይ ከሌለ የተጠበቀው ልዩነት አይከሰትም። 

በጉባኤው በድምጽ ከሚሳተፉት መካከል ዘጠና ዘጠኝ ከመቶ የሚሆኑት በጉባኤው ላይ መገኘታቸውን ያመለከቱት በአንድ ከመቶ ስሌት ያልተገኙት አባላት እነማን እነደሆኑ ይፋ አላደረጉም። በይፋ ባይገለጽም አቶ ጌታቸው ረዳ የቀድሞው የድህንነት ሃላፊ የነበሩትና ከፍተኛ ተቃውሞ የሚሰነዘርባቸው አቶ ጌታቸው አሰፋ የመገኘታቸውን ጉዳይ አሻሚ በሆነ መልኩ ” እዛ ሳገኛቸው እነግራችኋለሁ” ሲሉ በራሳቸው የጉዞ እቅድ መሰረት እንደሚገኙ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል ከጉባኤው ቀድመው ተናግረዋል። የክልሉ የስብሰባ ተሳታፊዎች ተለይዝይተው እንደሚሄዱም አመልክተዋል።

ኢትዮጵያዊነትን በልዩ መስተጋብሮቿ አስውበው ንግግር ያቀረቡት የድርጅቱ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በሞራል፣ በስነምግባር፣ በሞራል ልዕና መታነጽና እንዲህ ያለውን ትውልድ መፈጠር የማይችል አመራር ዋጋ እንደሌለው አበክረው መናገራቸው ፣ አገሪቱ በሚመሯት መሪዎቿ ደረጃ የገባችበትን የሞራል ዝቅተት በአግባቡ ያሳየ ትብሏል።

አገሪቱ ካለችበት እጅግ አሳሳቢ ቀውስ አንጻር እጅግ የከረረ ንግግር አላደረጉም በሚል አስተያየት የሰጡ ቢኖርም፣ እሳቸው ተስፋን ያነገበ፣ ለልብ የሚሆን ዲስኩር ማቅረባቸውን የወደዱላቸው እጅግ ይበዛሉ። 

ከጉባኤው በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” አገር መምራት አልቻሉም ይውረዱ” ሲሉ የነበሩ አካላት ከዛሬው ንግግር በሁዋላ ” የፈረሰች  አገር ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሆን፣ የክልል ሊቀመንበር መሆን ይሻላል” በሚል በስፋት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲወራጩ ተስተውሏል። 

ሌብነትን የዳቦ ስም በማውጣት ሙስና፣ ኪራይ ሰብሳቢ እያሉ መጥራት እንደማይገባ፣ ይልቁንም ያለምንም ቁልምጫ ” ሌቦች” ሊባሉ እንደሚገባ የተናገሩት ዶክተር አብይ፣ በማይፈልጉቸው አካላት የሚሰማባቸው ነቀፌታ ንግግራቸው ላይ የተመሰረተ ትችት ሳይሆን በጅምላው ” ይውረድ” የሚል ነው።

ይህንኑ አስመልክቶ በዛሬው ጉባኤ እንደታየው ጠላይ ሚኒስትር አብይን የሚያንገራግጭ ጉዳይ የለም። አጋር ፓርቲዎችም ከአፋር በስተቀር ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጡ አረጋግጠዋል። ብዙ የሚታሙት የቤኒሻንጉሉ ተወካይ ምንም እንኳን የመቀላቀል ጉዳይ ቢታይባቸውም፣ አሁን እየደረሰ ያለውን መፈናቀል አውግዘው ከድርጊቱ ጀርባ ያሉ አካላት ሊጠየቁ እንደሚገባ አሳስበዋል። ጉቤውም እዚህ ላይ አቋም እንዲይዝ ጠይቀዋል።

ከሽግግሩና ከለውጡ ጋር በተያያዘ በሶማሌ ክልል ተጀምሮ፣ ሃዋሳ ላይ ቀጥሎ ወደ ቡራዩና  ቤኒሻንጉል ያመራው ቀውስ በርካታ ዜጎችን ያሳሰበ ጉዳይ በመሆኑ ጉባኤው ምን አቋም እንደሚያዝ በጉጉት የሚጠበቀ ሆኗል። 

ጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴም ከውጭ ሃገር ሃያ አቻ ፓርቲዎች የተጋበዙበት ሲሆን በዛሬው የከሰዓት ውሎም የ11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ እና የኢህአዴግ ቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚጠቁም ሪፖርት መቅረቡ ታውቋል።በነገው ዕለትም ጠዋት ላይ ተሳታፊዎቹ በቡድን በመሆን ዛሬ በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ ይወያያሉ። በቀጣይም  በሪፖርቶቹ ላይ በሃይል መድረክ እንደሚወያዩም ለማወቅ ተችሏል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *