አዲስ አበባ ቦሌ መንገድ ድንገት በተሰማ የተኩስ ልውውጥ ነዋሪዎች ተደናግጠው ነበር። በተለምዶ ወሎ ሰፈር በሚባለው አካባቢ አንድ በአልኮል ተበረዘ የተባለ የፌደራል ፖሊስ ሁለት ባልደረቦቹን በጥይት አጥፍቷል። አምስቱን አቁስሏል። ይህንኑ ተከትሎ በተከፈተ የተኩስ ልውውጥ ከፍተኛ የትራፊክ መስተጓጎልና ድንጋጤ ተፈጥሮ ነበር። ለኢቲቪ መገለጫ የሰጡ ኢንስፔክተር ለግጭቱ የሚረባ ምክንያት የለም ብለዋል። አለቃቸው ደግም ስካር እንደሆነ አስታውቀዋል።

ስሙም ሆነ ድርጊቱን የፈጸመበት ምክንያት በውል ያልተገለጸው የፌደራል ፖሊስ አባል ሁለት ባልደረቦቹን ከገደለና አምስቱን ካቆሰለ በሁዋላ ለተጨማሪ ጥቃት ሲንቀሳቀስ መገደሉ ታውቋል።የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት አባሉ ሰክሮ ነበር ሲሉ ግድያው መፈጸሙን አረጋግጠዋል።ፖሊስ ጥቃቱን ለማስቆም በወሰደው እርምጃም ጥቃቱን የፈፀመው የፌደራል ፖሊስ አባል ህይወቱ ማለፉን ኮሚሽነር ጀነራሉ አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅም በስፍራው ተስተጓጉሎ የነበረው የትራፊክ እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ወደ መደበኛ ሁኔታቸው መመለሳቸው የታወቀ ሲሆን አንዳንድ የማህበራዊ ገጽ አክተሮች፣ በፓርላማ ተመራጮች መኖሪያ ውስጥ እርስ በእርስ ተታኩሰው ተጫረሱ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ተጋደሉ፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቡድን ለይተው እየተታኮሱ ነው… የሚሉና የሚያሸብሩ መረጃዎችን ሲያሰራጩ ታይቷል። 

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *