“የተሰራጨው የማህበራዊ ሚዲያ ወሬ ሙሉ በሙሉ ሃሰት ነው” ሲል አስተያየቱን የሚጀምረው ያዕቆብ ሃይሌ ነው። እውነት እንደተባለው ችግር እንኳን ቢፈጠር በዚህ መልኩ ማራገብ ማንንም ተጠቃሚ እንደማያደርግ ይናገራል። ተመርጦ አቶ ደመቀ መኮንን ታፍነዋል መባሉ ሆን ተብሎ የተሰላ ስሌትም እንደሆነ ይክላል። ሌሎች ደግሞ “ይህ ሁሉ ሲሆን የሰራዊቱ አባላት ይህንን ሁሉ ሲያደርጉ ከፍተኛ መኮንኖች የት ነበሩ?” የመከላከያ አባልት በበኩላቸው ” መሳሪያ ይዘን መምጣታቸን ስህተት ነው። ግን ልንታመን ይገባል” ብለዋል። 

ብዛት ያላቸው የመከላከያ ልዩ አባላት ቤተ መንግስት መታየታቸውን ተከትሎ አስደንጋጭ ዜናዎች ሲበተኑ ነው የዋሉት። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ ታግተው እንደነበርና በቤተመንግስት ጥበቃ አማካይነት ከእግት መለቀቃቸው ምንጮች ነገሩን በሚል ሃላፊነት የጎደላቸው የሚለኩሱት ወሬ ነው ተባራሪውን ዜና ያጋመው።

በስተመጨረሻ ጠቅላይ ሚኒስትር አሕመድ ነገሩን አቃለውና ወሃ አፍሰውበት ” እኔን ማግኘትና በኔ መሰማት ፈልገው ነው” ሲሉ መግለጫ ሰጡ። ከቡራዩ አሳዛኝ ቀውስ ጋር በተያያዘ በግዳጅ ላይ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት ልዩ ሃይል አባላት በደቦ ቤተመንግስት የሄዱት በመኪና ተጭነው ነው። ጉዳዩ ግራ ያጋባቸው እንደሚሉት ከምንም ነገር በላይ የሚገርመው የሰራዊት አባላቱ ወደ ቤተመንግስት እንዲሄዱ ማን መኪና መደበ? የሚለው ነው። በሌላም በኩል አለቆቻቸው እንዴት አላወቁም ? የሚለው ጥያቄ ከምንም በላይ ነው።

የእዝ ሰንሰለታቸውን ጠብቀው አግባብነት ባለው መልኩ ለምን ጥያቄያቸውን እንዳላቀረቡ በይፋ የተባለ ነገር ባይኖርም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም በውስጣቸው ስለለው በርካታ ጉዳዮች እንዳጫወቷቸው መናገራቸው ትርጉም አለው። አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት መከላከያ ሰራዊት ውስጥ የማጥራት ስራ በወጉ ሊሰራ ይገባል።

ቀይ መለዮ የለበሱት የሰራዊቱ አባላት ባልተጠቀሰ አካል ገፋፊነት መፈንቅለ መንግስት ሊያደርጉ እንደነበር ጫፍ ይዘው ነገሩን ያጦዙት ክፍሎች አይናቸውን አጥበው አሁን ድረስ ይቅርታ ያልጠየቁበት ድራማ ሲጀመር የሰራዊቱን አባላት የጫኑ ተሽከርካሪዎች ቤተመንግስት ደርሰው ቆሙ። የታጠቁ አባላት ከተሽከርካሪዎቹ ወርደው መንገድ ዘጉ። የዛኔ መተራመስ ነገር ተፈጠረ። አቶ ደመቀን አነጋገረው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለመነጋገር ፈቃድ አገኙ።

በስብሰባው ላይ የመከላከያ አባላቱ ትጥቅ ይዘው መምጣታቸው ስህተት እንደሆነ ተናግረዋል። ግን ” ልንታመን ይገባል” በለዋል። አንድም ጥይት ሳያጮሁ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማናገር የችግራቸው ብዛት እንደገፋቸው አስታውቀዋል። በሄዱበት ህዝብ እየቀለባቸው ግዳጃቸውን እንደሚወጡ ያመለከቱት የሰራዊቱ አባላት ውስጣቸው እንዲሸነፍ፣ በርካታ መረጃም መስጠታቸው ተመልክቷል። ለሰሩት  ጥፋት ወታደራዊ ቅጣት ተቀጥተዋል።  ፑሻፕ ሰርተዋል።

ያዕቆብ ሃይሌ እንደሚለው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከሰጡት ምላሽ ይልቅ ቀልቡን የሳበው በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያሉ ከፈተኛ አመራሮች ጉዳይና ይህንን ዜና ” ሰበር” እያሉ ሲያሰራጩ የነበሩ ክፍሎች ናቸው። ዜናውን ስጋና ደማቸውን በሚያስደስት መልኩ ማሰራጨታቸው ሃላፊነት የጎደለውና ተራ ወሬ ለቃቃሚነት እንደሆነም ጠቁሟል። 

“በዚህ የሃሰት ዜና  ሕዝብ ቢጫረሥሥ” ሲል የጠየቀው ያዕቆብ፣ ጉዳዩን ሕዝብ በሰከነ መንገድ ሊከታተለውና እንዲህ ያለውን አካሄድ ሊገታ እንደሚገባ ይመክራል። ነገ በተመሳሳይ ብዙ ሊባል እንደሚችል በማሰብ አውዳሚ ወሬዎችን መጠየፍ፣ እንዲህ አይነት የሰራዊት አካሄድንም በጥንቃቄ ማየትና ከስረ መሰረቱ መመርመር ግድ መሆኑንን አክሏል።

 

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

mereja ሰጥተውኛል. ውስጣቸው እንዲፈተሽ፣ ዋናው ዓማቸው እኔን ማገኘት ነው

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *