ሞተራይዝድ ዊልቼሮቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዕርዳታ ያገኟቸው ሲሆን፥ በዛሬው ዕለት ለ36 ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ለአካል ጉዳተኞች በስጦታ ማበርከታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በማህበራዊ ድረ ገጻቸው አስፍረዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቀጣይም ለሌሎችም ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የአካል ጉዳተኞች አቅም በፈቀደ መጠን ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸው ነው የተገለጸው።

የግል ባለሃብቶች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የእምነት ተቋማትና የተለያዩ አደረጃጀቶች ለአካል ጉዳተኞች ድጋፍ እንዲያደረጉ ጥሪያቸውንም ማስተላለፋቸውን ነው አቶ ፍጹም በማህበራዊ ድረ ገጻቸው የገለጹት።

እስካሁንም ድጋፍ እያደርጉ ለሚገኙ አካላትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከልብ የመነጨ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውም ነው የተገለጸው።

(ኤፍ.ቢ.ሲ) 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *