ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌ የአማራ ክልል አስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸውን የክልሉ ሚዲያ አድረገ። በመንግስት ግልበጣ አሲረዋል በሚል ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር ታስረው የቆዩት ጀነራል በተለያዩ ሚዲያዎች የደረሰባቸውን ሲያስረዱ ክልላቸውን ለማገልገል ፈቃደኛ መሆናቸውን ሲገልጹ ነበር።

ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌ ሹመቱ የተሰጣቸው በጸጥታው ዘርፍ ያላቸውን የረዥም ጊዜ ልምድና ብቃትን ከግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑን የአማራ ማስ ሚዲያ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።

ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(አዴፓ) የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው መመረጣቸው የሚታወስ ሲሆን የሳቸው ሹመትና የብርጋዴር ጀነራል ከማል ሹመት የተገጣጠመ ሆኗል። 

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *