አድብተው ጥፋት ለመፈጸም ዝግጅት የደረግበታል የተባለ  ካምፕ ሙሉ በሙሉ ወደም። ወታደራዊ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ ሃምሳ አንድ ምልምሎች ተያዙ። ከሰልጣኞቹ መካከል የአስራ ሶስት ዓመት እድሜ ያላቸው ታዳጊዎች ይገኙበታል። መጠኑ ያልታወቀ ሃይል ሸሽቶ ወደ ጎረቤት አገር መግባቱም ታውቋል።

የቢኒሻንጉል ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር  ሰይፈዲን ሃሩን  ለመንግስት ሚዲያዎች እንዳስታወቁት፣ አሶሳ ዞን በገንገን ቀበሌ ልዩ ስሙ ዛላን ወንዝ አካባቢ በሁለት ሄክታር ላይ የተሰራው ህገወጥ ማሰልጠኛ ሙሉ በሙሉ ወድሟል።  በአሰሳው ሰላሳ አንድ የሚሆኑት ሲያዙ፣ ሃያ የሚሆኑት ደግሞ እጅ የሰጡ ናቸው። የተቀሩት ወደ ጎረቤት አገር እንዳመሩ ከኮሚሽነሩ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።ግለሰቦቹ የተያዙት ኅብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ የክልሉ ልዩ ኃይል ሰሞኑን በአሶሳ ዞን ባደረገው አሰሳ ነው፡፡

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

የተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች፣ ፓስፖርቶች፣ እንዲሁም የተለያዩ የመታወቂያ ካርዶች መገኘታቸውን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። ምልምሎቹ ራሱን የበርታ ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ (በህነን) ብሎ ከሚጠራው ኃይል ተለይተው የወጡ ቡድን አባላት ሊሆኑ እንደሚችሉ ኮሚሽነሩ ግምታቸውን ስጥተዋል።

ከአንድ ወር በላይ ስልጠና ሲከታተሉ መቆየታቸውንና ዓላማቸው ህዝብ ላይ ጉዳት ማድረስ እንደሆነ ያመለከቱት ኮሚሽነሩ፣ በክልሉ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ከአገር መከላከያ ሠራዊትና ከፌዴራል ፖሊስ ጋር ተቀናጅተው በመሥራት ላይ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። ሕዝብ በክልሉ ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ድጋፉን እንዲያጠናክር ኮሚሽነር ሰይፈዲን ጥሪ አቅርበዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ፎቶ – ፋና

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *