የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን የከተማውን የትራንስፖርት እጥረት ለማቃለል ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ትዕዛዝ ከሰጣቸው 850 አውቶብሶች 700ዎቹን እስካሁን አልተረከበም ተባለ፡፡ ለአውቶብሶቹ 3.4 ቢሊዮን ብር ተከፍሏል ተብሏል፡፡

የባለስልጣን መ/ቤቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ ወ/ሮ እፀገነት አበበ ዛሬ ለሸገር ሲናገሩ፣ ከሜቴክ ጋር የአውቶብሶቹን ስራ ውል የገባነው በሰኔ ወር 2009 ዓ/ም ሲሆን አውቶብሶቹን መረከብ የነበረብን ሰኔ 2010 ነበር ብለዋል፡፡

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አውቶብሶቹን በቃሌ መሰረት ያላስረከብኩት በውጪ ምንዛሬ ችግር ነው ብሎናል ያሉት ወ/ሮ እፀገነት ከዚህ ወር ጀምሮ ግን ቀስ በቀስ ቀሪ 700 አውቶብሶቹን ሊያስረክበን ቃል ገብቶልናል ብለዋል፡፡

ሜቴክ ለአውቶብሶቹ መስሪያ የሚያስፈልገውን እቃዎች አስቀድሞ ገዝቷል፣ በተባለው ጊዜም ያደርስልናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ሲሉ ወ/ሮ እፀገነት ተናግረዋል፡፡

(ወንድሙ ኃይሉ)

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ.ኤም

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *