. (መንበር ዓለሙ ዘ ላልይበላ)

ሰሞኑን  ገዱ አንዳርጋቸው እና  ንጉሱ ጥላሁን ላይ የሚደረግ ዘመቻ በአርምሞ ተመለከትሁ። አሁን ግን ሚስጥሩን ለመግለፅ ትክክለኛው ስዓት ላይ ነኝ። አንድ ወዳጀ የአዴፓን ሙሉ ሚስጥር አጫውቶኛል። ሳልጨምር እና ሳልቀንስ እንደወረደ ላቀርበው ተገድጃለሁ።
.
የአዴፓ ብልሽት የተፈጠረው የብዓዴን ጉባኤ ጊዜ ነው። በወቅቱ እኔ ደመቀ መልቀቅ አለበት ብየ ተከራክሬ ነበር። በfacebook ማለቴ ነው። ነገር ግን facebook መንደሩ ላይ ብዙ ትችት በዝቶብኝ ነበር። ለማንኛውም በወቅቱ ብአዴን አስቦ የነበረው ዶ/ር አምባቸው መኮነን የአዴፓ ሊቀመንበርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ለማድረግ ጨርሶ ወደ ጉባኤው ገብቶ ነበር።
ጉባኤው እንደታሰበው ሳይሆን መሬት ባለመሸጡ እና ጠቅላይነቱን ለአብይ በመስጠቱ ምክንያት ብቻ ደመቀ ካልሆነ ብሎ አቋም ያዘ። አዴፓ ነገሩ ሁሉ ሞተበት ተምታታበት። ከዚህ በኋላ ሀዋሳ ላይ ደመቀ እንዲቀጥል ታግለው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር እንዲሆን አድርገው ጉባኤው ተጠናቀቀ።
.
ከኢህአዴግ ጉባኤ ማግስት አዴፓ ስብሰባ ተቀምጦ መከረ። ዶ/ር አምባቸው የክልሉ ኘሬዝዳንት እንዲሆን ገዱ እራሱ ለምኖታል። ዶ/ር አምባቸው ግን እምቢ አለ። እውነቱ ይሄ ነው። ገዱ ለኔ የሚል ስግብግብ አይደለም። ዶ/ር አምባቸውን የድርጅቱ ሊቀመንበር ለማድረግ የብአዴን ጉባኤ ላይ ባህርዳር ተረጋጉ ደመቀ መቀጠል የለበትም ለድርጅቱም አይጠቅምም ለሱም እራስምታት ነው በብስለት የታየነው ብሎ ነበር።
.
ዶ/ር አምባቸው የፈለገውን ሚኒስቴር እንዲሆን አዴፓ ቢጠይቀውም ግልፅ መሆን እንዳልቻለ እና በመጨረሻ
“ዶ/ር አምባቸው ፕሬዚዳንት ለመሆን ጥያቄውን ያቀረበው ራሱ ነው። ጥያቄውን እንዳቀረበ አቶ ገዱና አቶ ደመቀ በጽኑ ተቃውመዋቸዋል።
.
ቃል በቃል ገዱ አንዳርጋቸው ዶ/ር አምባቸውን አንተ በዚህ ስዓት ለአማራ የምታስፈልግ ነህ እንግዳ ተቀባይ አላደርግም እኔን ተካ ብሎ ጠይቆታል። ገዱ በበኩሉ ሚኒስቴር እሆናለሁ ወይም የክልል ቢሮ ኃላፊ ሆኘ ትግሉን እና ለውጡን አስቀጥላለሁ። የአማራ ችግር ውስብስብ በመሆኑ በጋራ ጠንክረን የምንሰራበት ስዓት ነው ብሏል። እውነቱ ይሄ ሆኖ ሳለ በመንደር የተሰባሰቡ activistoch #የገዱ እና #የንጉሱ_ጥላሁንን ስም ለማጥቆር የሚሄዱበት አባዜ ግለሰብን ወደ ስልጣን ለማምጣት ገዱን እና ንጉሱን ማንቋሸሽ ተገቢነት የለውም።
.
ገዱ አንዳርጋቸው፣ ዶ/ር አምባቸውም ሆኑ ንጉሱ ጥላሁን ለአማራ ህዝብ መስዋት እየከፈሉ ያሉ ትንታጎች ናቸው እንጅ።የfacebook መንደሩ እንደሚያወራው #መንደርተኛ አይደሉም።
.
የአዴፓ ጉዳይ ይህ ነው። ገዱ አንዳርጋቸው ለአማራ ህዝብ ትግል ጎህ የቀደደ ነው እንጅ ለስልጣን የሚኖር አይደለም። ከዚህ በኋላ ገዱ ላይም ሆነ ንጉሱ ጥላሁን ላይ የሚደረግ ዘመቻ አንታገስም።
ለማንኛውም አሁን ባለው መረጃ ዶ/ር አምባቸው ሰኞ ኘሬዝዳትነቱን ሊቀበል የነበረ ቢሆንም አዴፓወች ለምነው ሀሳቡን እንዳስቀየሩት እና ዶ/ር አብይ ተነግሮት የኘሬዝዳትነቱ ምርጫ ውስጥ እንደማያስገባው ተረጋግጧል። #ጃንጥራር አባይ በበኩሉ እኔ ለመታገል ዶ/ር አምባቸው አብሮኝ መኖር አለበት በማለት እንቅጩን ተናግሯል ተብሏል። አለበል መላኩ በምክትል ር/መስተዳደር ማዕረግ የክልሉ ንግድ ኃላፊ፣ላቀ አያሌው ምክትል ር/መስተዳደር የመሆን እድሉ ቢሰፋም አሁን ግን የዶ/ር አምባቸው ሚኒስቴር እሆናለሁ ማለት እንደገና ሹመቱን ሁሉ ሊያቀያይረው ይችላል ተብሏል። የዳግማዊት ሞገስ ትራንስፖርት ሚኒስቴርነት በራሱ ሌላ አጀንዳ ሆኗል። እሷን የሚተካ ሁነኛ ሰው እንዳልተገኘ እና ጃንጥራርን ለማስገባት አስበው እንደነበር ወዳጀ አረጋግጦልኛል።
..
እኔ በበኩሌ #ጃንጥራር_ዓባይ የያዘውን ሚኒስቴርነት በብቃት መምራት የሚችል ብቻ ሳይሆን የተሻለ ብቃት ያለው ወጣት በመሆኑ ከተቻለ የተሻለ ቦታ ሊሰጠው ይገባል ባይ ነኝ። በአዲስ አበባ ከንቲባነት የዳግማዊት ቦታ ሌላ አስተማማኝ ሰው ሊሸፍን ይገባል።
..
#የሰኞው_የአዴፓ ውሳኔ በራሴ #ሳይንቲፊክ_መላ ምት ላስቀምጥ…የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱ ጥቅምት 13 እና 14/2011 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ይወያያል።
1ኛ.ዶ/ር አምባቸው አንድ ሚኒስቴር ሊሆን ይችላል ይህን ማደረግ የሚቻለው በአዴፓ ጥንካሬ ነው።
2ኛ. ዶ/ር አምባቸው የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ኘሬዝዳንት ከሆነ እና ዶ/ር ሙላቱን ከተካ ግን ህጉ ተሻሽሎ የኘሬዝዳንቱ ስልጣን ስራ ተጨምሮበት አጋዥ እንዲሆን ይደረጋል።
3ኛ. የመጨረሻው ዕድል ዶ/ር አምባቸው የአብክመ ኘሬዝዳን ሊሆን ይችላል። ይህ የሚሆነው የገዱ ፍላጎት ስለሆነ እንጅ ካቢኔውም ሆነ CC ኮሚቴው በገዱ ያላቸው እምነት ከአለት የጠነከረ ነው። ገዱ አንዳርጋቸው ስለደከመው እና ዶ/ር አምባቸውን መተካት ስለሚፈልግ ብቻ እንጅ ገዱ በካቢኔው ድጋፍ አጥቶ ወይም አቅም አንሶት አይደለም በዚህ ደግሞ ሁሉም ያምኑበታል። ነገር ግን ገዱ እራሱ አምባቸውን የመተካት ሙሉ ፍላጎት አለው ይህ የሚያሳየው ገዱ በአምባቸው ይተማመንበታል ማለት ነው። የአንድ ሰፈር Activistoch እንዳሉት ገዱ አንዳርጋቸውም ሆነ ንጉሱ ጥላሁን ስልጣን ሙጥኝ የሚሉ አይደሉም። #አዴፓ ተከፈለ የምትሉ የገዱ እና የአምባቸው ቡድን የሚል አሉባልታ የምታወሩ ሰወች አማራን ትበትናላችሁ አደብ ግዙ። ከሰፈር ውጡ???? ቡድን የለም አንድ ናቸው። የህውሀት አስፈፃሚ አትሁኑ። አዴፓን መተቸት ግን ጠቃሚ በመሆኑ በብስለት ተቹ።
#ገዱ_አንዳርጋቸው የአማራን ትግል ፈር የቀደደ፣ የህውሀትን እብሪት ያስተነፈሰ እዩኝ እዩኝ የማይል ጀግና ነው!!
#ንጉሱ_ጥላሁን የማይደፈረውን ህውሀት የተጋፈጠ የአማራ ቀንዲል ነው!!
ማንም አፉን ሊከፍትባቸው አይገባም???
Viva ገዱ&ንጉሱ!!!!!!

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *