የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቶ አብርሃ ደስታን ብቻ አነጋግሮ ይህንን የሚያክል ጉዳይ ማቃለሉ አግባብ አይደለም፡፡ አቶ አብረሃን ሳይሆን የክልሉን መሪ በማነጋገር ፣ ህዝብ የሚለውን በማከል፣ የአማራ ክልል ሃሳብ ካለው ተጠይቆ ሊቀርብ የሚገባውን ታላቅ ጉዳይ አርመጥምጦ ማቅረብ አሁን ከሚታየው የሚዲያ አሰራር አኳያ ግራ የሚያጋባ ነው፡፡

ሲጀመር ጉዳዩ የአቶ አብርሃና የራያ ህዝብ ሳይሆን፣ አጀንዳው የትግራይ ክልል የበላይ ሃላፊዎች፣ ሰራዊት አዝምተው ጥይት በሚያስተኩሱት ባለስልጣኖችና በራያ እንዲሁም በፍትህ ናፋቂ ህዝብ መካከል መሆኑ አሌ አይባልም፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዲህ ያለውን ሚዛን የጎደልው ተግባር በማከናወኑ በይፋ ሊወቀስ ይገባል፡፡ 

እየሞተ ያለው ሰው ነው፡፡ ጥያቄ እያቀረበ ያለው ሰው ነው፡፡ ልጅ አልባ የሆኑ እናቶች ሰው ናቸው፡፡ ድርጅትን ወይም ግለሰቦችን ግንባር  በማድረግ የሰዎችን ደም መቀለጃ ማድረግ አግባብ አይሆንም፡፡ ህወሃትም ሆነ አዴፓ በወኪልና በግለሰብ ደረጃ እንኪያ ሰላምቲያ ሲያሰሙ ማስተናገድ አገሪቱ ይዛዋለች ከሚባለው ለውጥ አኳያ አያስኬድም፡፡ 

ሚዲያዎች ይህንን ጉዳይ መዘገብ ያለባቸው የችግሩን ሰለባ በማነጋገር ፣ እውነታውን ለህዝብና ለህሊና ፍርድ እንዲያመች በማድረግ እንጂ እንደቀድሞው የአንድ ወገን መፈንጫ በመሆን ሊሆን አይገባም፡፡ ጥያቄው የዝብ ከሆነና ህዝብ መብቴ ይከበርልኝ ካለ አለ ነው፡፡ መፍትሄውም ጥያቄውን አድምጦና አክብሮ አግባብነት ያለው በህግ የተቀመጠ መልስ እንዲሰጥ ሚዲያዎች ከተራ አራጋቢነት በመላቀቅ ህዝባዊ ወገንተኛነታቸውን ማሳየት ይገባቸዋል፡፡

ከታች አቶ ንጉሱ የሰጡትን መልስና አቶ አብርሃም ደስታ የትግራይ ክልልን በመወከል የሰጡትን አስተያየት አትመነዋል፡፡

ዛሬ የአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉአላዊነት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብረሀ ደስታ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ በትግራይ እና በአማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ለሚፍእጠረው ችግር ምክንያቱ የአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት እና መሪ ፓርቲው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ ነው ሲሉ ከሰዋል::
===================================

በአቶ አብርሀ ውንጅላ በኦሮሚያ እና አማራ ክልል የለውጥ መንፈስ እየታየ ሲሄድ መንግስቱም ሆነ ፓርቲው ከስልጣን እንዳይባረር እንደሚሰጋ ገልፀዋል :: እዚህ ላይ አቶ አብርሀ “የእምዬን ወደ አብዬ ” እንዲሉ ካልሆነ በስተቀር በአማራ ክልል ለውጡን ማን የመራው ይመስላቸው ይሆን ? ብለን ብንጠይቅ መልሳቸው መቼም አረና እንደማይሆን፤ ቶሎ አፋቸው ላይ የሚመጣው ብአዴን/ አዴፓ እንደሚሆን ሆዳቸው ያውቀዋል::

አሁን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲም ሆነ የክልሉ መንግስት ዋና ስራቸው ለውጡን ማስቀጠል፤ ሰላም እና መረጋጋትን ማረጋገጥ፤ የአማራን ትክክለኛ መብቶች ማስጠበቅ፤ የአማራን ዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት መገንባት፤ ከአጎራባች ክልሎች እና ከሀገራችን ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጋር በመከባበር፣ በመቻቻል፣ በሰላም እና በፍቅር መኖር መሆኑን በይፋ ገልፀን ወደ ስራ ገብተናል::

የማንነትን ጥያቄዎች በተመለከተ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲም ሆነ የአማራ ክልል መንግስት ይፋ አቋም ጥያቄ ያላቸው ዜጎች ማንነታቸውን በተመለከተ ሌላ ሰው ሳይሆን የሚመለከታቸው ዜጎች ራሳቸው ይወስኑ፤ እነሱ ይደመጡ፤ ውሳኔያቸው ይከበር ነው ፡ ፡ ይህንን ደግሞ በቅርቡ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በጉባኤው በግልፅ ያስቀመጠው መሆኑን ልብ ሊሉት ይገባል ፡ ፡

የአማራ ክልል ደግሞ በዚህ ረገድ የሚያኮራ ልምድ ያለው መሆኑን አቶ አብርሀ ይጠፋቸዋል ማለት ፖለቲከኛነታቸውን ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል:: የአማራ ክልል የኦሮሞ፣ የአዊ፣ የዋግ ኽምራ፣ የአርጎባ እና የቅማንትን የማንነት ጥያቄዎች በሚገባ የመለሰ፣ ቋንቋቸውን እና ባህላቸውን እንዲያሳድጉ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ እንዲሁም በብሄረሰብ አስተዳደር ተደራጅተው የራሳቸውን ምክር ቤቶች አደራጅተው መብቶቻቸው ተክብሮ የሚኖሩበት ክልል መሆኑን ልብ እ ዲሉት እንመክራለን::

አቶ አብርሀ እንዳሉት የትግራይ እና የአማራ ህዝቦች ወንድማማች እና እህትማማች ህዝቦች መሆናቸውን እንዲሁም ለዘመናት ተሳስረው የኖሩ ናቸው:: አሁንም ህዝብ ትክክልእኛ ዳኛ በመሆኑ አይጋጭም:: መሠረታዊው ጉዳይ ህዝብን ማዳመጥ እና መብቱን ማክበር እንዲሁም እኔ አውቅልሀለሁ ከማለት ኇላ ቀር አስተሳሰብ መላቀቅ ነው::

አቶ አብርሀ ለውጡን በተመለከተ ስለ አማራ ህዝብ ያላቸው ግምገማ የተሳሳተ ስለሆነ ወይ ቢጠይቁ አለዚያም ጉዳዩን ሳይነኩት ቢተውት ይሻላቸዋል :: ምክንያቱም የአማራ ህዝብ ለውጡ የራሱ የህዝቡ እና ይህንን የመራው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሆናቸውን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያምን እና ፓርቲውም ወደ ትክክለኛው የአማራ ወኪልነቱ እየተሸጋገረ መሆኑን እየገለፀ መሆኑን ስገልፅልዎት በዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራር መሆኔን ስገልፅልዎ በታላቅ ኩራት ነው::


 ዋልታ ዜና
“በትግራይ እና አማራ ክልል መካከል ለሚፈጠሩ አለመግባባቶችና በህዝቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ ያለው በአዴፓ ነው”
አቶ አብርሃ ደስታ
የዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉዓላዊነት ሊቀ መንበር
Image may contain: 1 person, textበትግራይ እና አማራ ክልል መካከል ለሚፈጠሩ አለመግባባቶችና በህዝቦች
መካከል ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ ያለው በአዴፓ የሚመራው የአማራ ክልል
መንግስት መሆኑን አረና ገምግሟል፡፡ በአማራም ሆነ በኦሮሚያ ክልል የለውጥ
መንፈስ እየታየ ሲሄድ አዴፓ ከስልጣን እንዳይባረር በመፍራት በትግራይና
በክልሉ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ችግሮች እየፈጠረም መሆኑን የፓርቲው ሊቀ
መንበር አቶ አብርሃ ደሰታ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል፡፡
ሊቀ መንበሩ አክለው እንዳሉት በዚህም ወልቃይትና ራያን የአማራ ክልል ነው
ሲል ይደመጣል፡፡ በሁለቱ ክልሎች መካከል ለሚፈጠሩ አለመግባባቶችና
በህዝቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ ያለው በአዴፓ የሚመራው
የአማራ ክልል መንግስት ነው፡፡ ለችግሩም ዘላቂ መፍትሔን ለማምጣት
የፌደራል መንግስት በሁለቱም ክልሎች የሚገኙ ወንድማማች ህዝቦች መካከል
አለመግባባት እንዳይፈጠር ችግር ፈጣሪውን አካል እንዲታረም ሊያደርገው
ይገባል፡፡ የአማራ ክልል መንግስትም ከቦታ ወረራና ዜጎችን የማጥቃት ተግባር መቆጠብ ይኖርበታል፡፡ በሌላ በኩል ስለኢትዮጵያዊነት በስፋት እየተነገረ ባለበት በአሁኑ ወቅት አንድ ወረዳ ‹‹የእኛ ነው!›› ይባላል፡፡ በአንድ አገር ውስጥ እየተኖረ ‹‹ወልቃይት የእኛ ነው ከተባለ ዓዲግራት የእኛ አይደለም›› እንደማለት ነው፡፡ የእነዚህ ኃይሎች ዓላማ በትግራይ ላይ ችግር በመፍጠር ለአማራ ህዝብ እንደሚወግኑ ማሳየት ነው፡፡ ነገር ግን የሁለቱ ክልል ህዝቦች በጋብቻ የተሳሰሩ ወንድምና እህት በመሆናቸው ግጭቱ አትራፊ አይደለም፤ መጋጨትም የለባቸውም፤ ህዝቦቹም አይፈልጉም፡፡ ምክንያቱም አብሮ የኖረ ህዝብና ወደፊትም አብሮነቱ የሚቀጥል
ህዝብ ነው፡፡
በአንድ አገር ውስጥ እስከተኖረ ድረስ ትግራይ ክልል የአማራ ክልል ተወላጅ መብቱ ሊከበርለት እንደሚገባ ሁሉ የትግራይ ክልልም ተወላጅ በተመሳሳይ በየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ የመኖርና ሃብት የማፍራት መብቱ ሊከበርለት ይገባል፡፡ እነዚህ ጠብ አጫሪ የሆኑ ኃይሎች የሚያደርጉት ድርጊት አፍራሽና ለአገር አንድነት የማይጠቅም ነው፡፡ የአንድነት ሃሳብም የላቸውም፡፡ አንድነት መከባበር እንደሚጠይቅ በመገንዘብ ለህዝቦች ፍቅርን እንጂ ጥላቻን መስበክ ተገቢ ያልሆነና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር በመሆኑ ከዚህ መሰል እኩይ ተግባር መታቀብና የህዝቦችን ሰላም ለማረጋገጥ መስራት ይገባል፡፡
(ኢ.ፕ.ድ)

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *