(ኤፍ ቢ ሲ) የህፃናት ማቆያ አገልግሎት የሚጠቀሙ ሴት የመንግስት ሰራተኞች ከልጆቻቸው ጋር የፐብሊክ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲጠቀሙ መፈቀዱን የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ፥ ሴት የመንግስት ሰራተኞች ልጆቻቸውን ወደ ህፃናት ማቆያ ይዘዉ ሲመጡ ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር ስለሚያጋጥማቸውና ለከፋ እንግልት እንደሚዳረጉ ከግምት ዉስጥ በማስገባት የትራንስፖርት አገልግሎት ከህፃናት ልጆቻቸዉ ጋር እንዲያገኙ ግፊት ሲያደርግ እንደቆየ አስታውሷል።
በመሆኑም የመንግስት ሰራተኛ የሆኑ ወላጆች፥ መስሪያ ቤታቸው የሕፃናት ማቆያ መቋቋሙን የሚገልጽ ደብዳቤ፣ የሕጻኑ/የሕጻንዋ የልደት ሰርተፍኬት ፎቶኮፒ እና ሌሎች በዝርዝር የተቀመጡ መስፈርቶችን በሟሟላት አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።