አዲሱ የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት ሙስጣፋ ዑመር በአማራ ላይ የተነዛዉ ፕሮፖጋንዳ ትክክል አይደለም ማለቱ ይበል የሚያስብል ነዉ፡፡ የልኡካን ቡድንም ወደ ወቅቱ የፖለቲካ ሴንተር ወደሆነችዉ (ባህርዳር) ይዘዉ እንደሚጓዙ ተናግረዋል፡፡ አማራ ላይ የተነዛዉ ፕሮፖጋንዳ ኢትዮጵያ ብቻ አይደለም ለአዉሮፓዉያን እና አሜሪካዉያን ሁሉ የተሰበከ ጉዳይ ነዉ፡፡ እኛም ይሄን በህዝባችን ላይ የተነዛዉን ዉንጀላ ለመቀልበስ እየሰራን ነዉ፡፡

አቶ ሙስጣፋን ከቃል ባለፈ ግን ግን በአስቸኳይ እንዲሰሯቸዉ የምንፈልገዉ ጉዳይ አለ፡፡
1. የሶማሌ ህዝብን ቀን ተሌት ደከመን ሳይሉ ሲያገለግሉ የነበሩ ባለሙያ አማሮች ተፈናቅለዉ ባህርዳር ላይ ይገኛሉ፡፡ በቁጥር አንድሽህ የሚነሆኑ አስተማሪዎች፤ ሃኪሞች፤ ኢንጅነሮች ናቸዉ፡፡ የሶማሌን ህጻናት ሲያስተምሩ የነበሩ፤ ለህዝቡ የጤና አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ናቸዉ፡፡ በርሃማ ነዉ፤ቋንቋዉን አንችለዉም ምናምን ሳይሉ በሙያቸዉ ለሶማሌ ክልል ህዝብ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መሻሻል አስቷጽኦ አድርገዋል፡፡ በመሆኑም ባህርዳር ሲመጡ እኒህን ፕሮፌሽናሎች አብረዉ ይዘዋቸዉ ወደ ሶማሌ ክልል ቢመልሷቸዉ እና ስራቸዉን ቢጀምሩ፡፡

2. በአማራ ህዝብ ላይ ፕሮፖጋንዳ ብቻ ሳይሆን የተነዛዉ በህገመንግስቱ፤ በፖሊሲወች፤ በሀገሪቱ governance system (ethnic federalism) እንዲሁም በአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ሁሉ ተጽፎ የተቀመጠ እና ተግባራዊ እየተደረገ ያለ ነዉ፡፡ የሶማሌ ክልል ህገመንግስትም በመግቢያዉ ላይ በጨቋኞች እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረን የሚል ሁሉ አለዉ፡፡ ስለዚህም የህገመንግስት ማሻሻያ በማድረግ አሁን ያሉትን ነገር በተግባር ማሳየት ይችላሉ፡፡
3. አማሮችም ሆነ ሌሎች የሶማሌ ክልል ነዋሪች ከቀበሌ እስከ ክልሉ ምክር ቤት የሚወከሉበትን ስርአት መዘርጋት፡፡ በነገራችን ላይ በአንድ ክልል ያሉ ዜጎችን በፖለቲካ ተሳትፎ እንዲኖራቸዉ ማድረግ የክልሉን ህዝብ እና ኢኮኖሚ ነዉ የሚጠቅመዉ፡፡ የተረጋጋ ክልል እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አድግት ይበጃል፡፡ ኢንቨስተሮችን ይስባል፤ Innovation and entrepreneurship (the engine of economic growth) ይጨምራል፡፡

4. አማረኛን ከሶማሌኛ ጎን ለጎን የክልሉ መንግስት የስራ ቋንቋ ማድረግ፡፡ ይሄም አንደኛ በሶማሌ ክልል ዉስጥ ለሚኖሩ ሌሎች ብሄሮች ጥሩ ይሆናል፡፡ ሁለተኛ የሶማሌ ተወላጆም ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ጋር በበለጠ እንዲተሳሰሩ እና ከሃግሪቱ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ አማረኛ የሀገሪቱ የቢዝነስ እና የፖለቲካ ቋንቋ ነዉ፡፡ሰለዚህም ከአማረኛ በራቅን ቁጥር ከሀገሪቱ የምናገኘዉን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚዊ ጥቅም ይቀንሳል፡፡

ባሀርዳር ያላችሁ ሰወችም ሰዉ ሲሄድ ሲመጣ የፎቶ ኤቨንት ብቻ ከማድረግ እንደዚህ ኮንክሪት በሆኑ ጉዳዮች ላይ መወያየት ይኖርባችኋል፡፡ አ ዴ ፓም የሶማሌ ህዝብ በፌደራሉ መንግስት በደንብ እንዲወከሉ፤ ከሀገሪቱ ሃብት ተቋዳሽ እንዲሆኑ እና በቂ በጀት እንዲመደብላቸዉ ያለዉን ፓለቲካል ፓወር ተጠቅሞ እንደሚያግዛቸዉ ቃል መግባት ብሎም መፈጸም አለበት፡፡

የአማራ ፖለቲከኞች ወይም ብሄርተኞች ደግሞ አንድ ሰዉ አንድ ነገር ባለ ቁጥር ሰማይ መስቀል እንዲሁም ሌላ ግዜ የሆነ ነገር ካለ መሬት ማወረዱን እንተወዉ እና more critical በመሆን የተባለዉ ነገር ተግባራዊ እንዲደረግ ተጽእኖ ማድረግ ነዉ የሚሻለዉ፡፡

በተረፈ የሶማሌ እህት እና ወንድሞቻችን እንኳን በሰላም ወደ ባህርዳር መጣችሁ፡፡ Enjoy Your stay.

ፎቶ  -ሪፖርተር

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *