– ሚሊዮን ዘአማኑኤል

Grand Ethiopian Renaissance Dam   ለዶክተር ቅጣው እጅጉ መታወሻ ትሁን
የምበላው ሳጣ፣ ልጄ ጥርስ አወጣ!!!  በገዛ ዳቦዬ፣ልብ ልባን አጣኃት!!!
ጂብቲና ሱዳን ቤት መብራት፣ ኢትዮጵያ ቤት ላንባ!!!
ከጂቡቲና ሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 87 ሚሊዮን ዶላር ተገኘ፣በ2010 ዓ/ም!!!

በኤሌክትሪክ አገልግሎት ተመን ላይ ማሻሻያ ተደረገ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተመን ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ። የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፥ አዲሱ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተመን ከፊታችን ታህሳስ ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ነው።  የዋጋ ንረትና አለም ላይ ያለው የሃይል ተመን ለማሻሻያው ምክንያት መሆናቸውንም ዋና ስራ አስፈጻሚ ተናግረዋል። አሁን በተደረገው ማሻሻያ መሰረትም ተጠቃሚው ከ12 አመት በፊት በነበረው የሃይል ዋጋ ተመን መሰረት የሚከፍል ይሆናል ነው ያሉት። በተመኑ መሰረት ተጠቃሚው የወጭውን 25 በመቶ ሲሸፍን ቀሪው 75 በመቶ ደግሞ በመንግስት ድጎማ የሚደረግበት ነው ተብሏል። ማሻሻያው በሰባት እርከኖች የተከፈለ ሲሆን፤ እርከን 1:  እስከ 50 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በነበረው ክፍያ በኪሎ ዋት 0 ነጥብ 2730 ብር ይቀጥላል፤ እርከን 2: እስከ 100 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 0 ነጥብ 6644 ብር የነበረው በአዲሱ ተመን 0 ነጥብ 7670 ብር፤ እርከን 3:  እስከ 200 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 1 ነጥብ 3436 ብር የነበረው በአዲሱ ተመን 1 ነጥብ 6250  ብር፤ እርከን 4:  እስከ 300 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 1 ነጥብ 6375 ብር የነበረው በአዲሱ ተመን 2 ብር፤ እርከን 5: እስከ 400 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 1 ነጥብ 7917 ብር የነበረው በአዲሱ ተመን 2 ነጥብ 2000 ብር፤ እርከን 6: እስከ 500 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 1 ነጥብ 9508 ብር የነበረው በአዲሱ ተመን 2 ነጥብ 4050 ብር እንዲሁም እርከን 7: ከ500 ኪሎ ዋት በላይ ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 2 ነጥብ 0343 የነበረው በአዲሱ ተመን 2 ነጥብ 4810 ብር ይሆናል።››5

የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን አዲስ የዋጋ ታሪፍ ጭማሪ ማስተካከያ ከፍተኛ የኤሌትሪክ ፍጆታ ተጠቃሚዎች በአዲሱ ተመን እስከ 350 በመቶ ጭማሪ ክፍያ ይጠየቃሉ። ድርጅቱ እዚህ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ አስቀድሞ ከኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት (EEU)፣ ከኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ፓወር (EEP)፤ ከውሃ፣ መስኖ እና ኤሌትሪክ ባለስልጣን መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን ጥናቱን ማድረጉን አስታውቋል። በአዲሱ የዋጋ ማስተካከያ መሰረትም በፊት ድርጅቱ ከሚያገኘው ከ7 እስከ 10 ቢሊዮን ብር ገቢ ወደ 35 ቢሊዮን ብር ያስገባል ተብሎ ታቅዷል። የዋጋ ማስተካከያው ከ13 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መደረጉን ታውቆል። በአጠቃላይ 2.5 ሚሊዮን ደንበኞች አሉን። ከእነዚህ ውስጥ 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑት ከ50 ኪሎ ዋት በታች ተጠቃሚዎች ናቸው። በዚህ ጥናት መሰረትም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ታሳቢ ያደረገ ነው። ለከፍተኛ የኤሌትሪክ ፍጆታ ተጠቃሚዎች ለሆኑት በፊት በአንድ ኪሎ ዋት በዶላር 7 ሳንቲም የነበረው ወደ 1.8 የአሜሪካ ዶላር ከፍ ይላል። የዋጋ ተመኑ በዓለም ላይ ዝቅተኛ ክፍያ ዝቅተኛ መሆኑ ታውቆል።

የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን በተደጋጋሚ ጊዜያት የመብራት መቆራረጥ ችግሮችን በመፍጠር ደንበኞቹን እያማረረ ያለ ድርጅት ነው። ይህንን መሰረታዊ ችግሩን ከመቅረፍ ይልቅ የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ መሽቀዳደሙ አጃይብ አሰኝቶል። በኢንዱስትሪው ዘርፍ በውጭ ምንዛሪ ችግር የጥሬ እቃዎች አቅርቦት እጥረት እየተዳከመ የመጣው የኢንቨስትመንት ፍሰት ላይ የተደረገው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ተግባራዊ ከሆነ ጫና ሊፈጥር ይችላል ተብሎም ተሰግትዋል። የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሠማሩ ባለሃብቶች አንድም በኤሌትሪክ መቆራረጥ ምርታማነታቸው ተገትቶል፣ ሁለትም በውጭ ምንዛሪ እጥረት የተነሳ ጥሬ እቃዎች ማስገባት ባለመቻላቸው ለኪሳራ የተዳረጉበት አመታት ሊጤን ይገባል እንላለን፡፡ በሌላ በኩል በውጭ ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንፖርተርስ የውጭ ምንዛሪ የሚያገኙት የድሮዎቹ በተለይ የዘይት ምርት በማስገባት የሚታወቁት አልሣም፣ በላይነህ ክንዴ፣ ደብሊው ኤ፣ አህፍ እና የፓርቲ የንግድ ‹ኢንዶውንመንት. ድርጅቶች በርካሽ ያሰገቡትን ዘይት በብዙ እጥፍ በመሸጥ ደሃውን ህዝብ ይመዘብራሉ፡፡ ከኤሌትሪክ ኃይል የተገኘ የውጭ ምንዛሪ ለዘራፊ ባለሃብቶች ተዳርጎል፣ ዜጎቹን በጨለማ የሚያኖር መንግሥት ፍህታዊ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያና ኤርትራ የድንበር ንግድ ህጋዊ ሥርዓት ባለመያዙ ህብረተሰቡ ኑሮ እንዳይናጋ አስፈላጊው ትኩረት ሊደረግ ይገባል፡፡ የውጭ ምንዛሪ አሰጣጥ አሁንም በባንኮችና በፓርቲዎች የንግድ ድርጅቶች መቀጠሉ ለውጡ ግልፅነት የጎደለውና የንግዱ ህብረተሰብ በነፃነት እንዳይሰራ እምነት እንዲያጣ ስላደረገው የዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት አስፈላጊውን እርምት ማድረግ ይኖርበታል እንላለን፡፡ ህብረተሰቡ በኑሮ ውድነት፣ በምግብ ፍጆታ በሁለት አሃዝ ጭማሪ እየተሰቃየና በኤሌትሪክ መቆራረጥ መስራት ባለመቻሉ ለውጡን እንዳያማርር ትኩረት ያሻል፡፡ በየቀበሌዎች የተሠገሰጉ የፖለቲካ ድርጅት ሰላይ ካድሬዎች፣ የውኃ ልማት ጥፋት ባተሌዎች፣ ቴሌኮሙኒኬሽን መስሪያ ቤት ፊርማቶሪዎች፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን በሙስና ሌብነት መረብ የተጥለፈለፉና የተሳሰሩ የድለላ ድርጅቶች ለመሆናቸው ምስክር አያስፈልግም፡፡ የህብረተሰቡ እሮሮ ገሃድ ምስክር ነውና፡፡ በአዲሱ ለውጥ የተጠመቁ የውሸት ካድሬዎች በየቀበሌዎቹ፣ የውኃ ልማት፣ ቴሌኮሙኒኬሽን መስሪያ ቤት፣ የኤሌትሪክ ተጠቃሚው ህብረተሰብ ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠራቸውን ህብረተሰቡ በማማረር ላይ ይገኛል፡፡ ህዝብ ደሞዝ እንደሚቆርጥላቸውና ቀለብ እንደሚሰፍርላቸው ያልተረዱ ጉቦ ተኮር ሙያተኞች በህግ ሊጠየቁ ይገባል፣ የስነምግባር ተሃድሶና ቀልጣፋ አስራር፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት በተግባር እንዲገለፅ ሠራተኞቹ ፎቶቸውና ስማቸው ያለበት መታወቂያ ማድረግ እንዳለባቸው እናሳስባለን፡፡ ህብረተሰቡን የሚያሰቃዩ በነዚህ ድርጅቶች  ጉቦ ተኮር ሙያተኞች ለውጡን ለመቀልበስ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ መንግሥት ህብረተሰቡን በማነጋገር እርምጃ ይውሰድ፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ፣ ከጂቡቲና ለሱዳን ከተሸጠ የኤሌክትሪክ ኃይል 87 ሚሊዮን ዶላር በ2010 ዓ/ም ሲገኝ ወደፊት ደግሞ ከኬንያ 252 ሚሊዮን ዶላር በአመት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡  Ethiopia exporting 170 MW electricity to neighboring countries     “The Ethiopian Electric Service (EES), a company leading the service delivery, said the nation is currently exporting 170MW power to neighboring countries. Sudan, Djibouti and Kenya are the three countries being provided with 100MW, 60MW and 10MW of electricity respectively, EES Executive Officer, Biteweded Gebrealif, told Walta Information Center. Ethiopia’s current cumulative power generation capacity stands at 2370MW, which according to the officer is enough to meet the national demand. The power disconnection that occurs in the country is not because of power shortage but due to problems in the installation of power carrying grids, he said. The power is being exported at night, a time with no peak power requirements, and on the basis of a program designed not to jeopardize local consumption, he indicated. In addition to generating foreign currency, the power export would further cement Ethiopia’s economic ties with neighboring countries, according to Biteweded. Ethiopia began export of energy to Djibouti in May 2011 and Sudan in November 2012.”6

አፍሪካ አገራቶች በ2012 እኤአ ዓመታዊ  የነፍስ ወከፍ የኤለትሪክ ፍጆታ ኪሎዋት በሰዓት  ድርሻ፤ በኢትዮጵያ 57፣ ኬንያ  153 ኪሎዋት በሰዓት፣  ሱዳንና ደቡብ ሱዳን 165፣  ኪሎዋት በሰዓት ነው፡፡ ስለዚህ የኢትጵያ ከ100 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ 3 ሚሊዮን ህዝብ ብቻ የቤት ውስጥ መብራት ተጠቃሚ በሆነበት አገር ወደ  ጎረቤት አረጋት በርካሽ ዋጋ የኤሌትሪክ ኃይል መሸጥ ፍትሃዊ አሰራር አይደለም፡፡ የውጪ ምንዛሪ ለማግኘት ሲባል ዜጎችን በጨለማ ውስጥ እንዲኖሩ ማድረግ የኢኮኖሚ ነፃነት፣  በሌለበት ሃገር የፖለቲካ ነፃነት የለም፡፡ ለእራስህ ማድረግ የማትፈልገውን ለሌሎች እንዲደረግባቸው ማድረግ ኃጢዓት ነው፡፡ የእንጀራ እናት ጡጦ ማለት  ዜጋህን በጭለማ እያኖርክ፣ የእምዬን ጡቶች እየጠቡት  ጎረቤቶች በመብራት ሲቦርቁ፣ ሲማሩ ሲያነቡና ሲፅፉ ማለት ነው፡፡ የአንድ መንግሥት ፍህታዊ አሰራር የሚለካው የብሄራዊ ዶቦ ጥያቄን፣ የኢኮኖሚ ጥያቄን፣ የሥራ ዕድል፣ ፍህታዊ የሃብት ክፍፍል፣ የክልሎች ፍህታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ያለ አንዳች አድሎ ሲተገበርና ክልሎች የክልላቸውን ኃብት ተጠቃሚ ሲሆኑ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ህገመንግሥታዊ መብታቸው መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ‹‹ Ethiopia earns over $49mln from electric power sales to Djibouti, Sudan፤- “Ethiopia earned more than 3.8 billion birr from electric power sold during the past 10 months. The plan was to generate 4.7 billion birr, said Bizeneh Tolcha, public relations head at the Ministry of Water, Irrigations and Electricity (MoWIE). More than 49.4 million US dollars of the total revenue was made from power exported to Sudan and Djibout, he said. In addition to meeting local demands, Ethiopia has a plan to sell electric power to neighboring countries once the power projects being built are completed. Ethiopia and Tanzania had already signed power purchase deal which allows the latter to buy 400MW from the east African nation. Kenya also showed interest to buy 200MW and works on the construction of power transmission line project has been launched by the Chinese firm China Electric Power Equipment and Technology (CET). Expected to cost over 1.2 billion US dollars, the transmission line is financed by the African Development Bank (AfDB). It runs about 1,045km, of which 445km is within Ethiopia’s territory and the rest in Kenya. Sudan and Djibouti have also showed interest to buy addition power from Ethiopia. Ethiopia is investing billions of dollars to construct a number of power plants including what would be Africa’s largest dam, the Grand Ethiopia Renaissance Dam (GERD). GERD is currently over 58 percent complete and will have power generation capacity of 6,450 MW once it is completed. The construction of the dam will transform the country’s vision to become a leading power exporter in the East African region hub for the renewable energy in Africa.Ethiopia’s hydropower, geothermal, wind and solar energy potentials are estimated up to 60,000 MM.”7

የኢትዮ ኬንያ ኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ በኢትዮጵያ በኩል ተጠናቀቀ፣ ኢትዮጵያ በወር 21 ሚሊዮን ዶላር የሚያስገኝላትን የኤሌክትሪክ መስመር ግንባታ ስታጠናቅቅ፣ ኬንያ በበኩሏ ፕሮጀክቱን 70 በመቶ ማድረሷ ታወቀ፡፡ በ2008 ዓ.ም. የተጀመረው የኢትዮ ኬንያ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት፣ በኢትዮጵያ በኩል በሦስት ምዕራፎች ተከፋፍሎ እየተካሄደ ነበር፡፡ በአጠቃላይ 1‚055 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ባለ 500 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ በኩል የሚገነባው 433 ኪሎ ሜትር ተጠናቋል፡፡ በኢትዮጵያ በኩል የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ የኢንጂነሪንግ ሥራዎች፣ የተለያዩ ዕቃዎች ማምረትና ማጓጓዝ የቁፋሮና የፋውንዴሽን ሥራዎች፣ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች ተከላና የመስመር ዝርጋታ ሥራዎች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸው ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ በወላይታ ሶዶ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በመገንባት ላይ እንደሚገኝ አቶ ምስክር ገልጸዋል፡፡ ይህንን ግዙፍ ግንባታ በ2.4 ቢሊዮን ብር እያካሄደ የሚገኘው የቻይና ኤሌክትሪክ ፓወር ኢኪዩፕመንት ኩባንያ ነው፡፡ ለሁለቱም አገሮች የፕሮጀክቱን ወጪ የሸፈነው የአፍሪካ ልማት ባንክ መሆኑ ታውቋል፡፡ በኬንያ በኩል የሚገነባው 622 ኪሎ ሜትር ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ደግሞ 70 በመቶ መድረሱ ታውቋል፡፡  ኢትዮጵያና ኬንያ 400 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለመገበያየት ተስማምተዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ዕውን ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በወር 21 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደምታገኝ አቶ ምስክር ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት 4‚260 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም ላይ የደረሰችው ኢትዮጵያ፣ በሚቀጥሉት ዓመታት ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል የምታገኝባቸውን ፕሮጀክቶችን በማካሄድ ላይ ትገኛለች፡፡ ለአብነት የገናሌ ዳዋ የኃይል ማመንጫ ግንባታ 96 በመቶ፣ የህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጫ 68 በመቶ፣ የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ 22 በመቶ፣ የኮይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ 21 በመቶ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ከውኃ 50 ሺሕ ሜጋ ዋት፣ ከነፋስ 1.3 ሚሊዮን ሜጋ ዋት፣ ከጂኦ ተርማል አሥር ሺሕ ሜጋ ዋት፣ ከዚህ በተጨማሪ በቅርቡ በተካሄደ ጥናት የአገሪቱ 70 በመቶ መልክዓ ምድር ከፍተኛ የፀሐይ ኃይል ማመንጨት እንደሚያስችል ተረጋግጧል፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት ለጂቡቲና ለሱዳን ከተሸጠ የኤሌክትሪክ ኃይል 87 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን ያስታወሱት አቶ ምስክር፣ ኢትዮጵያ ከታዳሽ ኃይል ዘርፍ ብዙ ጥቅም ታገኛለች ተብሎ እንደሚታሰብ ጠቁመዋል፡፡ አቶ ምስክር ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤት አገሮች የምትሸጠው የራሷን ፍጆታ ስታሳካ ነው ብለዋል፡፡››8

ለተጓተተው የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግንባታ ብድር እንዲፋጠን ተጠየቀ ለኮይሻ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግንባታ ፕሮጀክት የሚያስፈልገው የኃይድሮና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ግዥ መዘግየት አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ በመሆኑ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ከቻይና መንግሥት ጋር በመነጋገር በፍጥነት የኮንሴሽናል ብድር እንዲያመቻች ተጠየቀ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ለገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር በጻፉት ደብዳቤ፣ የኮይሻ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የኤሌክትሮ ሜካኒካልና የኃይድሮ ሜካኒካል ሥራዎች በመዘግየታቸው በሲቪል ምሕንድስና ሥራ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ከመፍጠሩ ባሻገር፣ በአጠቃላይ የፕሮጀክቱ እንቅስቃሴም እንዲዘገይ እያደረገ ስለሆነ ፕሮጀክቱ ለተጨማሪ ወጪና ተጨማሪ የክፍያ ጥያቄ እያስከተለ ነው ብለዋል፡፡ ‹‹የተጀመረው የብድር ጥያቄ የኮንሴሽናል ብድር መሥፈርቶችን ያሟላ መሆኑ እንዲረጋገጥና ስምምነቱ የሚፋጠንበት ሁኔታ ተመቻችቶ ውጤቱ ይገለጽልን፤›› ሲሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚው በደብዳቤያቸው ጠይቀዋል፡፡ በጊቤና በኦሞ ወንዞች ላይ የሚገነባው አራተኛው ኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ 2,200 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ማመንጨት አቅም የሚኖረው ሲሆን፣ ለግንባታው 2.5 ቢሊዮን ዩሮ ይፈለጋል ተብሏል፡፡  የዚህ ፕሮጀክት ዋና ሥራ ተቋራጭ ሆኖ ውል የገባው የጣሊያኑ ግዙፍ ኩባንያ ሳሊኒ ኢምሪጂሎ ኤስፒኤ ቢሆንም፣ በፋይናንስ ችግር ምክንያት የኤሌክትሮና የኃይድሮ ሜካኒካል ሥራው ከሳሊኒ ተነጥሎ ወጥቷል፡፡ የኤሌክትሮ ሜካኒካልና የኃይድሮ ሜካኒካል ሥራው ከሳሊኒ ጋር ተካሂዶ ከነበረው ስምምነት ተለይቶ ሲወጣ፣ ወደፊት ክርክር እንዳያስነሳ ጥንቃቄ እንዲደረግ የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር መመርያ መስጠቱ ታውቋል፡፡ ሳሊኒ ይህንን የኮይሻ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የተረከበው ያለ ጨረታ ቢሆንም፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካልና የኃይድሮ ሜካኒካል ሥራዎችን የሚያካሂድ ኩባንያ ለመምረጥ ጨረታ ወጥቶ የኮንሴሽናል ብድር ማምጣት እንችላለን ያሉ ሰባት ኩባንያዎች ተወዳድረው ነበር፡፡ ከሰባቱ ኩባንያዎች ውስጥ በጊቤ ሦስትና በኮይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ውስጥ የተሳተፈው የቻይና ግዙፍ ኩባንያ ዶንግ ፋንግ ኤሌክትሪክ ኢንተርናሽናል ኮርፖሬሽን አሸንፏል፡፡ የኤሌክትሮና የኃይድሮ ሜካኒካል ሥራዎች በአጠቃላይ 460.8 ሚሊዮን ዶላር የሚፈልጉ መሆኑን፣ በቀጣይ በሚኖሩ ድርድሮች ዋጋው ሊቀንስ እንደሚችል በአብርሃም (ዶ/ር) የተጻፈው ደብዳቤ ያመለክታል፡፡ ነገር ግን ይህ ከቻይና የሚገኘው ብድር በኮንሴሽናል ብድር ሥሌት መሆን ስላለበት፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ይህንኑ በፍጥነት እንዲያመቻች ተጠይቋል፡፡ የኮይሻ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በደቡብ ክልል በዳውሮና በወላይታ ዞኖች፣ እንዲሁም በኮንታ ልዩ ወረዳ መካከል ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱ የሲቪል ምሕንድስና እየተካሄደ ቢሆንም፣ የኤሌክትሮና የኃይድሮ ሜካኒካል ሥራዎች ጎን ለጎን እየተካሄደ ባለመሆናቸው፣ በፕሮጀክቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ተብሏል፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ የኤሌክትሪክ ማመንጫ እምብርት ለመሆን እየሠራች ያለችው ኢትዮጵያ ከውኃ 50 ሺሕ ሜጋ ዋት፣ ከንፋስ 1.3 ሚሊዮን ሜጋ ዋት፣ ከእንፋሎት አሥር ሺሕ ሜጋ ዋትና ከፀሐይ 100 ሺሕ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ነገር ግን የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በዕቅድ መሠረት እየተጓዙ ስላልሆኑ፣ አሁን በማመንጨት ላይ የሚገኘው 4,260 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ብቻ ነው፡፡››9

ምንጭ Source:

{5} አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) November 2, 2018 | by ethioexploreradmin (በባሃሩ ይድነቃቸው)|

{6} By Curated Content on Friday, September 19, 2014/ (Nesru Jemal) Originally published on EBC on Sept. 18, 2014

 {7} Addis Ababa, May 18, 2017 (FBC) {8} ሪፖርተር ጋዜጣ 5 August 2018 ውድነህ ዘነበ  {9} ሪፖርተር ጋዜጣ 21 October 2018  ውድነህ ዘነበ  

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *