ክፍል ሁለት – (ሚሊዮን ዘአማኑኤል)

ለዶክተር ቅጣው እጅጉ መታወሻ ትሁን

የኢትዩጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን፣ ህዝብ ያስለቀሰና በብልሹ አሰራር ከሜቴክ ከሚፈነዱ ትራንስፎርመሮች ጋር  በመሥራት ህዝብ ያዘረፈ ድርጅት ሲሆን ሹሞቹ ጥራታቸውን ያልጠበቁ የኤሌትሪክ ጀነሬተሮች፣ የኤሌትሪክ ዥረት ተሸካሚ፣ አስተላላፊ ሽቦዎች፣ የኤሎትሪክ ሶኬቶች፣ ስቶቭ፣  ወዘተ በውጭ ምንዛሪ ተገዝተው የሚገቡ ጥራት የሌላቸው እቃዎችን  ሀገር ውስጥ በማስገባት፣ በሃገሪቱ የጥራት የሌላቸው የኤሌትሪክ እቃዎች በማስገባት በሃገር ኢኮኖሚ ድባቅ የከተተ ድርጅት አሁንም በዛው ሥራው ቀጥሎል በሙስና ሌብነት ተባባሪ በመሆን ህዝብ እያስለቀሱ መብራት እያቆራረጡ መኖር ለውጥ አይደለም፣ ከስር ያሉ የሃገር ነቀርሳዎች መነቀል አለባቸው እንላለን፡፡ የዶክተር አብይ ለውጥ ያልነካው በህዝቡ ዘንድ የኢትዮጵያ ኩራዝ አገልግሎት በመባል ይታወቃል!!!

ለዶክተር ቅጣው እጅጉ፣ ለአንድ አገር የኢኮኖሚ እድገት የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫዎች ትልቅ አስተዋፆኦ እንዳለው ጥናታዊ ፁሁፍ አዘጋጅተው ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መንግሥት ለማቅረብ አዲስ አበባ መጥተው ምክረ ሃሳባቸው ውድቅ ሆኖባቸው ወደ ፖለቲካው ዓለም እንደገቡ በጀርመን ድምፅ ዶቼቬሎ ሬዲዩ ቃለ መጠይቅ ከ15 አመታት በፊት አድርገው ነበር፡፡

የዶቼቬሎ ጋዜጠኞች በድጋሚ ብታቀርቡትና በኢንተርኔት ብትለቁት እኚህ እውቅ ሳይንቲስት ለሃገራቸው የነበራቸው ርዐይ በአሁኑ ትውልድ ዘንድ ይታወቅ ነበር እንላለን፡፡  የባለሙያዎች አስተያየት ውሰጥ 70 በመቶ የሚሆነው የሃገራችን ህዝብ በጨለማ ውስጥ እንደሚኖር ስንቶቻችን እናውቃለን፣ ሃገራችን የራሶን ልጆች ጨለማ ውስጥ እያኖረች ለጎረቤት ሃገራት ብርሃን በርካሽ ዋጋ መሸጦስ ሌላው የዶላር ርሃባችን ሲሆን ዶላሩ ለጌቶቻችን ዘመናዊ መኪኖችና፣ የቅንጦት እቃዎች ለማስገባት አይደለም የሚል ማን አለ፣ በሌላው ደሃ ዜጋ ኪሳራ አንዱን የእንጀራ ልጅ ይመስል በጨለማ ውስጥ እያኖሩ ለሌላው ብርሃን መፈንጠቅ የግፍ ግፍ ነው እንላለን፡፡ እንደባለሞያዎቹ ማ!.. ‹‹የኃይል ማመንጨት አጠቃቀም፣ የማከማቻው፣ የመቆጣጠሪያውና የማሰራጫ ሥራው በአስቸኮይ በዘመናዊ መልኩ ካልተከናወነ ትርፍ የሌለው ፕሮጀክት ነው፡፡››

‹‹ ብዙዎቹ የኃይል ማመንጫዎች ኃይል የሚያቀርቡት ወደ አዲስ አበባ  በመሆኑ፣ ኃይል ረዥም ርቀት ሄዶ ለተጠቃሚዎች ማድረሱ ብክነት በመሆኑ ሌሎችም የኃይል ማመንጫዎች አካባቢ ያሉ የከተማም ሆነ የገጠር አካባቢዎች የመነጨውን ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ ማቀድ ይገባል፡፡… ኃይል ርቆ ከሄዱ በተለይ የሰርጭት ገመድ መርዘም ብክነት ያስከትላል›› ‹‹ በአገሪቱ በ2003 ዓ/ም ከነበረው የ10 ሺ ኪሎ ሜትር የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ማስተላለፍያ መስመር፣ በ2009ዓ/ም 16ሺ 500 ኪሎ ሜትር ለማድረስ የተቻለ ቢሆንም  አሁን የሚመነጨውን ኃይል በሙሉ አገልግሎት ላይ ለማዋል የመስመር ዝርጋታ እድሳትን የማስፋፋት ሥራ  ከፍተኛ ሊሆን ይገባል፡፡››

በአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከ2010/11 እስከ 2014/15 የሚከናወኑት ውስጥ፤ የኃይል ማመንጫ ተቆሞች ግንባታ፣ከ2000 ወደ 10,000 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኃይል የሚያመነጭ መገንባት፤ የኤሌትሪክ ኃይል፣ 132,000 ኪሎ ሜትር አዲስ የኤሌትሪክ ኃይል መሥመር መዘርጋትና ማከፋፈል እንዲሁም በሃገሪቱ ውስጥ 75 በመቶ የኤሌትሪክ ኃይል ማዳረስ፤ ቴሌኮም፤ በሃገሪቱ ውስጥ 45 በመቶ የሞባይል ስልክ ድርሻን ለህዝብ ማዳረሰ እንዲሁም የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎችን ከ10 ወደ 40 ሚሊዩን ህዝብ ከፍ ማድረግ፤ የኤሌትሪክ ኃይል ልማት ለሃገሪቱ ኢንደስትሪ ልማት፣ አዲስና ተጨማሪ የኢንደስትሪ ዘርፍ አልባሳት፣ የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ፣ ሲሚንቶ፣ ማዳበሪያ እንዲሁም ለግብርና ዘርፍ ልማት  የአግሮ ኢንዱስትሪ ልማት፣ ስካር ፋብሪካዎችን ማስፋፋት ሲያደርግ በተመሳሳይ ለአገልግሎት ዘርፍ ለቱሪዝምና ሆቴሎች ልማት  ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

የኢነርጅ የኤሌትሪክ ኃይል ልማት ለአንድ ሃገር ዘርፈ በዙ የኢኮኖሚ ዘርፎች ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ አገልግሎት እድገት ወደር የለውም፡፡ ለአንድ አገር የኤሌትሪክ ኃይል ጥቅም ለኢንዱስትሪ ዘርፍ ለፋብሪካዎች፣ ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ወዘተ፣ ለግብርና ዘርፍ ለግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች፣ ለማዳበሪያ፣ ለጨው፣ ለእህል ወፍጮ፣ ለዱቄት፣ ለዘይት፣ ለመኮረኒ፣ ፓስታ፣ ዳቦ ፋብሪካዎች፣ ለትራንስፖርት ዘርፍ ለኤሌትሪክ ባቡር፣ ለኤሌትሪክ መኪናዎች፣ ወዘተ የኤሌትሪክ ኃይል በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ከተለያዩ የጉልበት ምንጮች የተለያዩ የጉልበት ዓይነቶች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የጉልበት ምንጮች ከሙቀት፣ ከፀሐይ ብርሃን፣ ከድምፅ፣ ከኤሌትሪክና የመሳሰሉት ዓይነቶች ናቸው፡፡ {1} የጉልበት ምንጮች ሃይድሮ ፓወር የሚሠጡት የጉልበት ዓይነቶች ኤሌትሪክ፣ ግፊት (እንቅስቃሴ) ድምፅ  {2} የጉልበት ምንጮች ጅዎ ተርማል የሚሠጡት የጉልበት ዓይነቶች የእንፋሎት ኃይል {3} የጉልበት ምንጮች ንፋስ የሚሠጡት የጉልበት ዓይነቶች ኤሌትሪክ፣ ግፊት(እንቅስቃሴ)ድምፅ {4} የጉልበት ምንጮች ፀኃይ የሚሠጡት የጉልበት ዓይነቶች ኤሌትሪክ፣ ጉልበት ሙቀት ብርሃን ናቸው፡፡

‘’460 ሜጋ ዋት የኃይል ብክነት” ‹‹የዓለም አቀፍ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥናት እንደሚያመለክተው፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ከሚመረተው የኤሌትሪክ ኃይል ውስጥ ከ20 እስከ 25 በመቶ የሚሆነው ይባክናል፡፡ በኢትዮጵያ ከሚመረተው ኃይል ደግሞ 20 በመቶ እንደሚባክን ከዓመት በፊት ይፋ የተደረገው ይሄው ጥናት ይጠቁማል፡፡ የብክነቱ መጠን በሜጋ ዋት ሲሰላም ከ400 ሜጋ ዋት በላይ ነው፡፡ ይህ ማለት የበለስ ወይም የግልገል ጊቤ 2 የኃይል ማመንጫ ከሚያመርቱት 460 ሜጋ ዋት ጋር የሚቀርብ ነው፡፡ …ለብክነት ዋነኛው መነሻው ከደረጃ በታች የሆኑ የኤሌትሪክ ቁሳቁስ ወደ ሃገር ውስጥ መግባት ነው፡፡

…በኢትዮጵያ እሰከ 37 በመቶ የሚሆነውን ኃይል የሚወስደው የቤት ውስጥ አገልግሎት ነው፡፡ በዚህ ረገድ ኤሌትሪክ ምጣድ የሚወስደው የኃይል ፍጆታ እጅግ ከፍተኛና አሳሳቢ ሲሆን፣ ምጣዶቹ ከመስመር ከሚወስዱት ኃይል ውስጥ ለሚፈለገው ግልጋሎት የሚውሉትም ከ50 እስከ 70 በመቶውን ብቻ ነው፡፡ ቀሪው ጥቅም ሳይሰጥ ባክኖ ይቀራል፡፡ላለፉት 40 ዓመታት ማሻሻያ ይደረግበት ቢባልም አልተቻለም፡፡ …ኤሌትሪክ ሞተሮቹ ከሚወስዱት ኃይል ጥቅም ላይ የሚውሉት 60 በመቶውን ብቻ ነው፡፡ ቀሪው 40 በመቶ ከመስመር ቢወጣም ለሚፈለገው አገልግሎት የማይደርስና ባክኖ የሚቀር ነው፡፡

ኢንዱስትሪዎቹ የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች/ሞተሮች/ችግር ያለባቸውና ደረጃቸውን ያልጠበቁ አባካኝ ናቸው፡፡… የዕቃዎቹ ማርጀትና በዘመናዊ እቃዎች አለመተካት እንዲሁም ቁጥጥር የማነስ ችግር ናቸው፡፡….ሌላው አሁን ያሉትን የማስተላለፍያ መስመሮች ያለውን የኃይል አቅም የሚሸከሙ እንዳልሆኑ ይጠቁማሉ፡፡ የመነጨውን ኃይል በአግባቡና ውጤታማ በሆነ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ ማሻሻያዎች ማድረግ፣ የአሠራር አቅምን ማጎልበትና ዘመናዊ መሆን የግድ ይላል፡፡ …የተለያዩ የኃይል ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችንና የኃይል አስተዳደርና ሌሎች መፍትሄዎችን መተግበር ቢቻል ከሚባክነው ከ75 በመቶ የሚሆነውን ኃይል ማዳን ይቻላል፡፡ ለመስመሮች እድሳትም የማድረግና ያረጁትንም የመቀየርና በዘመናዊ መተካት እንዲሁም ለኤሌትሪክ ቁሳቄስ የኃይል ፍጆታ ደረጃ ማውጣት ብክነትን በመቀነስና በመከላከል ረገድ የራሱ ፋይዳ አለው፡፡

መስመሮችን ለመቀየር ከሚደረግ ጥረት ይልቅ በተጠናና ነባራዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ማከፋፈያዎችን መትከል፣ ረጅም ርቀት ኃይል ተሸክመው የሚሄዱ ማስተላለፍያ መስመሮችን ማቀራረብና በመሃል ኃይል መመገብ ችግሩን ያቃልላል፡፡….በአጠቃላይ እንደ ኤሌትሪክ ማመንጨቱ ሁሉ ለስርጭቱ ትኩረት ባይሰጥም የማስፋፍ ሥራዎች መጀመራቸውን፣ የማከፋፈያ ጣቢያዎችና የመስመሮቹን አቅም የማሳደግ፣ እድሳት ማድረግና ያረጁትንም የመቀየር ሥራዎች ሊሠሩ ይገባል፡፡››

የልዕለ ኃያላን  የቻይናና የአሜሪካ መንግሥታት ፍጥጫ በአፍሪካ!!!

{1} የቻይና ‹‹የአንድ ሃር መንገድ››፣ የቻይና መንግሥት ለአፍሪካ አህጉር የሚያደርገው ድጋፍ መርሃ ግብር ውስጥ በዓለም አቀፋዊ የመሠረተልማት ግንባታ ማለትም በመንገድ፣ ባቡር፣ ወደብ እና ኤርፖርት ግንባታ ቻይና ‹‹የአንድ ሃር መንገድ›› የተሰኘው የቻይና መንግሥት 126 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት አውሮፓን ኤሽያንና አፍሪካን አህጉሮች ለማገናኘት እየጣረች ትገኛለች፡፡ የቻይና መንግሥት ለአፍሪካ አሀጉር ጋር የ60 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ እቅድ አለው፡፡

{2} የአሜሪካ ‹‹ፓወር አፍሪካ››፣ የአሜሪካ መንግስት ‹‹ለአፍሪካ ኃይል›› (Power Africa) በሚል የተዘረጋ መርሃ ግብር ዓላማ የመንግሥትና የግል ዘርፍ ኢንቨስተሮች በጋራ የኤሌትሪክ ኃይል የማመንጫ ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ አጋርነት መፍጠር ነው፡፡ በዚህም ዓላማ የአፍሪካ አህጉር ህዝቦች ተጨማሪ 30,000 ሜጋዋት የኤሌትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ለ60 ሚሊዮን አዲስ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ቤቶች የመብራት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተልዕኮ አለው፡፡

“According to Power Africa objectives and goal launched, public and private sector investors are to come together to work in energy sector in partnership increasing the number of people in the African continent with access to sufficient power. The goal, therefore, is to add more than 30,000 MW in addition to the existing one. Furthermore, the power generated should be of cleaner, more efficient generating capacity to serve 60 million new homes and business entities.”  

ፓወር አፍሪክ ፕሮጀክት 16 ቢሊዮን ዶላር መዋለ ንዋይ በመመደብ የአፍሪካ አህጉር ህዝቦች የኤሌትሪክ ኃይል ፍጆታ እጥረት ማቃላል ይሻሉ፣ ሆኖም ከአፍሪካ ኢትዮጵያ እስካሁን በዚህ ተጠቃሚ አይደለችም፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብ የኤሌትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች 27 በሞቶ ሲሆን ቀሪው 73 በመቶ በጨለማ ውስጥ ይኖራሉ፣ ሃገሪቱ በፓወር አፍሪካ ፕሮግራም በመጠቀም ችግሮቾን ማቃለል ትችልለች፡፡ የፓወር አፍሪካ ትራንዛክሽንና ሪፎርም ፕሮግራም የኢትዮጵያን ኤሌትሪክ አገልግሎት ካንፓኒን በመደገፍ በግሉ ዘርፍ ነፃ የኃይል አመንጪዎች (independent Power Producers (IPP) የኤሌትሪክ ኃይል እንዲያላሙ፣ በገንዘብ፣ በዲዛይን፣ በጨረታ፣ በግንባታ፣ በኮሚሽንና ኦፕሬሽን ሥራዎች እንዲሰማሩ ያደርጋል፡፡

“Power Africa initiative, will invest a total of $16 billion to tackle African’s crippling energy deficit. Although in Ethiopia, the population’s access to electricity has risen to 27 percent majority of the 100 million Ethiopians are still living in the dark and Ethiopia will have benefited on this power generation program. Power Africa Transactions and Reforms Program (PATRP) is supporting Ethiopian Electric Power Company (EEP) to identify independent Power Producers (IPP) that will develop, finance, design, procure, construct, commission, and operate in the country.” 1

የግሉ ዘርፍ ኢንቨስተሮች ያመነጩትን የኤሌትሪክ ኃይል ለኢትዮጵያን ኤሌትሪክ አገልግሎት ካንፓኒ በመሸጥ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ኢትዩጵያ ከውሃ 45 ሽህ ሜጋ ዋት፣ ከንፋስ 1.3 ሚሊዩን ሜጋዋት፣ ከእንፋሎት 10 ሽህ ሜጋ ዋት፣ ከካርቦን ኒውትራል እና ከሌሎችም ኃይል ማመንጫዎች ከፍተኛ ኃይል ለማምረት ዕምቅ አቅም አላት፡፡ ዓመታዊ  የነፍስ ወከፍ የኤሌትሪክ ፍጆታ ኪሎ ዋት በሰዓት ድርሻ ፤ የሚያሳየው  የአንድ ግለሰብ አማካኝ የኤሌትሪክ ፍጆታ ማለትም  ለቤት ውስጥ አገልግሎቶች የሚጠቀምባቸው  የኤሌትሪክ አንፑሎች፣ የምግብ ማብሰያ  (ስቶቨ)፣ የእንጀራ መጋገሪያ ምጣድ፣ የቡና መፍጫ፣ የሽንኩርት መፍጫ ና የጁስ መጭመቂያ ፣ የዕቃ ማጠቢያ ማሽን ፣ የአከላት መታጠቢያ ሻወርና ቦይለር፣ የልብስ ማጠብያ(ዋሸንግ ማሽን)፣  የልብስ መስፍያ ማሽን (ሴንጀር)፣ ካውያ፣ የጸጉር መተኮሻ ማሽን፣ የጸጉርና ጢም ማስተካካያ፣  ሪፍሬጄሬተር፣ ቴሌቪዝን፣  ራዲዮ፣ ኮንፒውተር፣ የቤት ማሞቂያ /ሂተር፣ የምንጣፍ መጥረጊያ፣  የተንቀሳቃሽ ስልክ ቻርጅ ማድረጊያ፣ የልጆች ጌም መጫውቻ፣ ወዘተ በአጠቃላይ ለአንድ ግለሰብ የኤሌትሪክ ፍጆታ ኪሎ ዋት በሰዓት ድርሻን መለኪያ ነው፡፡

በአፍሪካ አህጉር ዓመታዊ  የነፍስ ወከፍ የኤለትሪክ ፍጆታ ኪሎዋት በሰዓት ድርሻ በ2012 እኤአ፤ በኢትዮጵያ 57፣ ቡርኪ ናፋሶ 60፣ ሊቢያ 66፣  ኡጋንዳ 78፣ ቤኒን 91፣ ዴ/ሪ ኮንጎ 111፣ ጋምቢያ  122፣  ማላዊ 127፣ ናይጀሪያ 147፣ ቶጎ 147፣ ኬንያ  153፣  ሱዳንና ደቡብ ሱዳን 165፣  ኮንጎ 171፣ አንጎላ 233፣ ኮትዲቮር 238፣ ሞሪታንያ 254፣ ካሜሩን 255፣ ጋና 336፣  ሌሴቶ 345፣  ዚምባዌ  498፣   ሞዛንቢክ 448፣ ኬፕቨርዴ 577፣ ዛምቢያ 592፣ ስዋዚላንድ 1052፣ ጋቦን 1029፣ ቦትስዋና 1603፣  ናሚቢያ 1681፣ ሞሪሽየስ 1915፣  ደቡበ አፍሪካ 4047 ኪሎዋት በሰዓት ነበር፡፡ የሃብታምና የደሃ አገራቶች ዜጎች ልዩነታቸው በሚጠቀሙበት የኤሌትሪክ ዕቃዎች መገልገያ ዕቃዎችና ዓመታዊ  የነፍስ ወከፍ የኤለትሪክ ፍጆታ ኪሎዋት በሰዓት  ድርሻ የአንድ አገር የእድገት ምልክት ነው፡፡   በቀላሉ ለመረዳት፣ የስፔን አጠቃላይ የኤሌትሪክ ፍጆታ 243 ቢሊዮን ኪሎ ዋት በሰዓት ሲሆን 47 ሚሊዮን ህዝብ አላት ፡፡ በአንጻሩ የሰሃራ በታች ሃገራቶች አጠቃላይ የኤለትሪክ ፍጆታ 139 ቢሊዮን ኪሎ ዋት በሰዓት ሲሆን 860 ሚሊዮን ህዝብ አሎቸው፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ 150 ኪሎ ዋት በሰዓት የኤሌትሪክ ፍጆታን ለመጨረስ 961 ቀናቶች (2 አመት ከ6 ወር በላይ) ይፈጅበታል፡፡ በተመሳሳይ አንድ እንግሊዛዊ 150 ኪሎ ዋት በሰዓት የኤሌትሪክ ፍጆታን ለመጨረስ በ11 ቀናት ውስጥ ተጠቅሞ ይጨርሰዋል፡፡2

‹‹ የዓለም የፋይናንስ ኮርፖሬሽን 500 ሜጋ ዋት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ድጋፍ ሊያደርግ ነው   ከሁለት ቢሊዮንዶላር የድጋፍ ማዕቀፍ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ ትሆናለች ተብሏል፣ የዓለም ባንክ አባል ድርጅት የሆነው የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (አይኤፍሲ) የመካከለኛው ምሥራቅና የአፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ሚስተር ሰርጂዮ ፒሜንታ፣ በኢትዮጵያ 500 ሜጋ ዋት የፀሐይ ኃይል የሚያመነጩ ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው አስታወቁ፡፡ ሚስተር ፒሜንታ ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፣ ኮርፖሬሽኑ በአፍሪካ ልማት መስኮች ድጋፍ ከሚሰጣቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ ናት፡፡ በተለይም በፀሐይ ኃይል የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይልን ከማልማት እስከ ሥርጭት ባለው ሒደት ውስጥ የመንግሥት ተቆጣጣሪ አካላትን የቴክኒክና የቁጥጥር አቅም ከመገንባት ጀምሮ፣ እስከ ድርድር አቅማቸው ባለው ደረጃ ኮርፖሬሽኑ ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡ በአይኤፍሲ ድጋፍ በአፍሪካ ትልቁ የፀሐይ ኃይል ፕሮጀክት እንደሚሆን ይጠበቃል በማለት የገለጹት ይህ ዘርፍ፣ በመጀመርያው ምዕራፍ 250 ሜጋ ዋት ኃይል ለማመንጨት የሚፈልጉ ኩባንያዎች ፍላጎታቸውን እንዲገልጹ የሚያስችል ዝግጅት ተካሂዶ፣ ለማልማት የሚፈልጉ ኩባንያዎች በጨረታ እንዲሳተፉ የሚደረግበት ደረጃ ላይ ኮርፖሬሽኑ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ ኩባንያዎቹ በሚያቀርቡት ተወዳዳሪ ዋጋ መሠረት ጨረታው እንደሚካሄድና ለተጠቃሚዎች ርካሽ የኤሌክትሪክ ኃይል ከፀሐይ ምንጭ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በመንገድና በሌሎችም መሠረተ ልማቶች ኮርፖሬሽኑ እንደሚሳተፍና እስካሁን በአገልግሎት፣ በጤና፣ በትራንስፖርትና በመሳሰሉት መስኮች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡ ‹‹የዓለም ባንክ የልማት ቀኝ እጅ ከሆነው የዓለም የልማት ማኅበር ባለፈው ዓመት የ2.5 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ አግኝተናል፡፡ ኢትዮጵያ ከታዳጊ አገሮች ተርታ የዚህ ድጋፍ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችላትን ቅድመ ሁኔታ ስለምታሟላ ድጋፍ ታገኛለች፤›› ቢሉም፣ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ምን ያህሉ ለኢትዮጵያ ይደርሳታል የሚለው በሒደት እንደሚታወቅ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ለአገሮች ድጋፍ ይውላል ብለዋል፡፡ ይሁንና ከፍተኛ የሥጋት ተጋላጭነት የሚታይባቸውንና የግሉ ዘርፍ የሚሳተፍባቸውን ፕሮጀክቶች ለማገዝ የሚውል ድጋፍ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ እንደ አግሪ ቢዝነስና ማኑፋክቸሪንግ ያሉት ዘርፎች ከዚህ የድጋፍ መስኮት ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቅሰዋል፡፡… ምንም እንኳእስካሁን ባለው ሁኔታ ኮርፖሬሽኑ በኢትዮጵያ የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ላይ የተመሠረተ ተሳትፎ ባያደርግም፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ግን በመንግሥት ይፋ ከተደረጉ ፕሮጀክቶች መካከል በተለይ በፀሐይ ኃይል መስክ ‹‹ስኬሊንግ ሶላር›› የተባሉት ፕሮጀክቶች ላይ ኮርፖሬሽኑ ድጋፍ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል፡፡ በመንግሥት ይፋ ከተደረጉት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች መካከል፣ በአፋርና በሶማሌ ክልሎች እንዲገነቡ የታቀዱትና እያንዳንዳቸው 125 ሜጋ ዋት ኃይል የሚያመነጩ ሁለት የ‹‹ስኬሊንግ ሶላር›› ፕሮጀክቶች ይጠቀሳሉ፡፡ በአፋር ክልል በግል አልሚዎች ተገንብተው ለመንግሥት በመሸጥ የፀሐይ ኃይል እንዲያቀርቡ የታቀዱት፣ በአፋር ክልል ዲቼቶ ስኬሊንግ ሶላር የተሰኘውና በሶማሌ ክልል ጋድ ስኬሊንግ ሶላር ፕሮጀክት ይጠቀሳሉ፡፡ እያንዳንዳቸው 150 ሚሊዮን ዶላር በድምሩ 300 ሚሊዮን ዶላር እንደሚጠይቁ የተጠቀሱት እነዚህ ሁለት ፕሮጀክቶችን ጨምሮ፣ ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚወጣባቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ባለፈው ሳምንት መዘገባችን ይታወሳል፡፡›› 3

የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ዳይሬክተር ጄነራል ዶክተር ተሾመ ታፈሰ የ6.3 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚጠይቁ ከውኃ ኃይል 6ት ከፀሐይ ኃይል 7ት የሚለሙ 13 የኃይል ማመንጫዎችና 18 ሌሎች የኃይል ማስተላለፊያና የሰብስቴሽን ፕሮጀክቶች፣ እና 3 የፍጥነት መንገዶች ይፋ ተደርገዋል፡፡

በፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች፣  የኢትዮጵያ የመንግስትና የግል አጋርነት ፅህፈት ቤት ካፀደቃቸው 16 ፕሮጀክቶች መካከል 13ቱ በሀይል አቅርቦት ዘርፍ ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ 7ቱ በፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች 850 ሜጋዋት የሚያመነጩ በ1005 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚያወጡ  ሲሆን ከፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ውስጥ {1} ጋድ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ፣125 ሜጋ ዋት በ150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣ {2} ዲቻቶ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ፣125 ሜጋ ዋት  በ150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣ {3} መቐለ የፀሃይ ሀይል ማመንጫ፣100 ሜጋ ዋት  በ120 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣ {4} ሁመራ የፀሃይ ሀይል ማመንጫ፣ 100 ሜጋ ዋት  በ120 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣ {5} ወለንጪቲ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣ 150 ሜጋ ዋት በ165 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣ {6} መተማ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣125 ሜጋ ዋት በ150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣{7} ሁርሶ የፀሃይ ሀይል ማንጫ ፕሮጀክት፣ 125 ሜጋ ዋት በ150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ናቸው፡፡  የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የሚገኙበት ሥፍራም በአፋር፣ በድሬዳዋ፣ በሶማሌ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና በትግራይ ውስጥ እንደሚገነቡና በተጨማሪ የሚገነቡ ማመንጫዎች፣ ማሰራጫዎችና የኃይል ማስተላለፊያ ጣቢያ/ ሰብስቴሽኖች ሥራ እንደሚካሄድ ጥቅምት 15 ቀን 2011ዓ/ም ተገልፆል። የአሜሪካው ፓወር አፍሪካ ለግሉ ዘርፍ በብድር የሚያሰራቸው ናቸው፡፡

የፀሐይ ሶላር ሴልስ ቴክኖሎጂ፤ የፀሐይ ብርሃንና ሙቀት  ወደ ተዘረጋው ሶላር ሴልስ ጨረሩ ይከማቻል፣ ከዚያም  የፀሐይን ጉልበት ወደ ኤሌትሪክ ጉልበት ይለወጣል፡፡   ሶላር ሴልስ በመጠቀም የፀሐይን ጉልበት ወደ ኤሌትሪክ ጉልበት መለወጥ ይቻላል፡፡ ይህም ተፈጥሮዊ  ታዳሽ ኃይል ከካርቦን በካይ ፍልቀት፣ ልቀትና ርጭት  የተጠበቀ ያደርገዋል፡፡ የጉልበት ምንጮች ከወራጅ ውኃ፣ ጅዋ ተርማል፣ ነፋስና ፀሐይ ተፈጥሮዊ ታዳሽ ኃይል የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት ይቻላል፡፡  ለምሳሌ የሶላር ሴልስ ቴክኖሎጂ፤ በ250 ሄክታር መሬት ላይ በማንጠፍ፣ ሶላር ሴልስ ከፀሐይ የሚሠበስበውን ብርሃንና ሙቀት በማጠራቀም፣ የፀሐይ ጉልበትን ወደ ኤሌትሪክ ጉልበት መለወጥ ይቻለዋል፡፡ ከ300000 ከሶላር ሴልስ ፓኔሎች በመዘርጋት የሚገኘውን 100 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኃይል በማመንጨት ወደ ከፍተኛ የኤሌትሪክ ዥረት ተሸካሚ የሆኑ የኤሌትሪክ መስመሮች ጋር ማገናኘት ቀጣይ ሥራ ይሆናል፡፡ ቀጥሎም ከከፍተኛ የኤሌትሪክ ዥረት ተሸካሚ  ጋር በሽቦ ወይም በሌሎች ኤሌትሪክ አስተላላፊ በሆኑ ነገሮች በኩል የሚያልፍ የኤሌትሪክ ፍሰት (ኮረንቲ) በመኖሪያ ቤቶች ውስጥ የኤሌትሪክ ብርሓን ይሰጠናል፡፡ የአሜሪካው ፓወር አፍሪካ ለመንግሥትና ለግሉ ዘርፍ ለኃይል ማመንጫ ብድር ያመቻቻል፡፡

የኃይድሮ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች፣ የኢትዮጵያ የመንግስትና የግል አጋርነት ፅህፈት ቤት ካፀደቃቸው 16 ፕሮጀክቶች መካከል 13ቱ በሀይል አቅርቦት ዘርፍ ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ 6ቱ በፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች 2221 ሜጋዋት የሚያመነጩ በ4258 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚያወጡ  ሲሆን ከኃይድሮ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ውስጥ {1} ገናሌ ዳዋ 5 የሀይል ማመንጫ ፣ 469 ሜጋ ዋት በ793 ሚሊየን  የአሜሪካ ዶላር፣ {2} ገናሌ ዳዋ 6 የሀይል ማመንጫ፣100 ሜጋ ዋት  በ387 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ፣ {3} ጨሞጋ የዳ 1ና 2 የሀይል ማመንጫ፣ 280 ሜጋ ዋት   በ729 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣ {4} ሀሌሌ ዋራቤሳ የሀይል ማመንጫ፣ 424 ሜጋ ዋት  በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር፣ {5} ዳቡስ የሀይል ማመንጫ፣798 ሜጋ ዋት በ984 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣ {6} ዌራንሶ የሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣150 ሜጋ ዋት በ165 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣ በአጋርነት እንዲገነቡ ውሳኔ ከተሰጠባቸው የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የኃይድሮ ኃይል ፕሮጀክቶች የሚገነቡ ማመንጫዎች፣ ማሰራጫዎችና የኃይል ማስተላለፊያ ጣቢያ/ ሰብስቴሽኖች ሥራ እንደሚካሄድ ታውቆል።

የፍጥነት  መንገድ ፕሮጀክቶች፣ የኢትዮጵያ የመንግስትና የግል አጋርነት ፅህፈት ቤት ካፀደቃቸው 16 ፕሮጀክቶች መካከል 13ቱ በሀይል አቅርቦት ዘርፍ ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ 3ቱ የትራንስፖርት ፕሮጀክቶች 357 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ በ1115 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚያወጡ  ሲሆን የመንገድ  ፕሮጀክቶች ውስጥ {1} የአዳማ አዋሽ 125 ኪሎ ሜትር የፍጥነት  መንገድ በ440 ሚሊየን ዶላር፣ {2} አዋሽ ሚኤሶ 72 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ በ230 ሚሊየን ዶላር እና {3} ከሚኤሶ ድሬደዋ 160 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ  በ445 ሚሊየን ዶላር የሚገነቡ  ሲሆን በዚህ ጨረታ  ወጥቶላቸው ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል። የገንዘቡ ምንጩ ግን አልተገለፀም።

‹‹ አሜሪካ ለቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ፕሮጀክት 1.1 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች የአሜሪካ የንግድና ልማት ኤጀንሲ በኦሮሚያ ክልል ለሚካሄደው የቱሉ ሞዬ የጂኦተርማል ፕሮጀክት ጥናት የሚውል የ1.1 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ፡፡ ምሥራቅ አርሲ ዞን ኢተያ ከተማ አቅራቢያ ቱሉ ሞዬ በተባለ ሥፍራ የሚገነባው የጂኦተርማል የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በአራት ክፍሎች የሚገነባ ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ 520 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል፡፡ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ይገመታል፡፡ የፕሮጀክቱ ባለቤት ቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኢፕሬሽንስ የተሰኘ በኢትዮጵያ የተቋቋመ ኩባንያ ሲሆን፣ በፕሮጀክቱ ላይ ኢንቨስት የሚያደርጉት ሬካቪክ ጂኦተርማል የተባለ የአይስላንድ ኩባንያና ሜሪዲየም የተሰኘ የአሜሪካ ኩባንያ ናቸው፡፡ የአሜሪካ ንግድና ልማት ኤጀንሲ ለቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ፕሮጀክት የመጀመርያ ክፍል የአዋጭነት ጥናት የሚውል 1.1 ሚሊዮን ዶላር እንደለገሰ አስታውቋል፡፡ የመጀመርያው ክፍል 50 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡ ጥናቱን የሚሠራው ዴለሮስ ኢንተርናሽናል የተሰኘ የአሜሪካ ኩባንያ ነው፡፡ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነቱ ሰኞ ነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ተፈርሟል፡፡ ስምምነቱን የፈረሙት የአሜሪካ ንግድና ልማት ኤጀንሲ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ኃላፊ ካትሪን ሂንዳርዴልና የቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኦፕሬሽንስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዳሬል ቦይድ ናቸው፡፡ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ ትሮይ ፊትሬል ለኢትዮጵያ ልማት ዘላቂ፣ አስተማማኝና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ወሳኝ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በጂኦተርማል፣ በፀሐይ፣ በውኃና በንፋስ የኃይል ምንጮች የታደለች መሆኗን የገለጹት ፊትሬል፣ አሜሪካ ኢትዮጵያ ዕምቅ የኃይል ምንጮችን ለማልማት የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስረድተዋል፡፡ ሚስተር ቦይድ ኢትዮጵያ በክልሉ በጂኦተርማል ዕምቅ ሀብቷ ቀዳሚ እንደሆነች ገልጸው፣ የቱሉ ሞዬ ፕሮጀክት ይህን ዕምቅ ኃይል ጥቅም ላይ ለማዋል እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡….የጂኦተርማል ፕሮጀክት ጥናት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ የአሜሪካ መንግሥት ያደረገው የገንዘብ ድጋፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡ ‹‹በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ያለውን ከፍተኛ ዕምቅ የጂኦተርማል ሀብት ለማልማት ሁለት ኩባንያ ብቻ በቂ ላይሆን ስለሚችል፣ ተጨማሪ ኩባንያዎች ይመጣሉ ብለን እየጠበቅን ነው፤›› ያሉት ፍሬሕይወት (ዶ/ር) ግልጽ በሆነ ጨረታ ፕሮጀክቶቹለግል አልሚዎች እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡ ሚስስ ካትሪን በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ታዳሽ የኃይል ምንጮች ለማልማት ቁርጠኝነት ማሳየቱን ገልጸው፣ የአሜሪካ ንግድና ልማት ኤጀንሲ በኃይል፣ በትራንስፖርትና በኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ ልማት እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ገበያ ለሚሳተፉ የአሜሪካ ኩባንያዎች ኤጀንሲው ድጋፍ የመስጠት ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል፡፡ የቱሉ ሞዬና ሻሸመኔ ከተማ አቅራቢያ ኮርቤቲ በተባለ ሥፍራ የሚገነባው 500 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የኮርቤቲ ጂኦተርማል ፕሮጀክት ልማት ስምምነት፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በታኅሳስ 2010 ዓ.ም. መፈረሙ ይታወሳል፡፡ በአጠቃላይ ሁለቱ የጂኦተርማል ኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክቶች 1,000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖራቸዋል፡፡ ፕሮጀክቶቹ በአሜሪካ ንግድና ልማት ኤጀንሲና ፓወር አፍሪካ  እንደሚደገፍ ታውቋል፡፡›› 4    በኢትዮጵያ የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት የገንዘቡን ምንጭ በዝርዝር ለህዝብ አላስረዳም!!!

የመብራት ኃይል ድርጅት የሌብነት ሠንሰለት መረብ ህዝብን እያማረረ በመሆኑ የለውጡ ኃይል ጥብቅ እርምጃ እንዲወሰድ ያስፈልጋል እንላለን!!!

ምንጭ Source:  {1} https://www.usaid.gov/powerafrica/partners {2} (@africaprogress 16.09.2016 / Africa Progress Report 2015) {3} ሪፖርተር ጋዜጣ 31 October 2018  ብርሃኑ ፈቃደ  {4} ሪፖርተር ጋዜጣ 29 August 2018  ቃለየሱስ በቀለ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *