• በሥራ ላይ ካለው የኢትዮጵያ ሕግ አንጻር ሹመታቸው ጥያቄ አስነስቷል

በዚህ ሳምንት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬስ ሴክሬታሪ ሆነው የተሾሙት ወ/ሪት ቢልለኔ ስዩም ወልደየስ በዜግነት ካናዳዊት መሆናቸው ጥያቄ አስነስቷል። ሹመታቸውም በሥራ ላይ ያለውን ሕግ የሚጻረር ነው ተብሏል።

ወ/ሪት ቢልለኔ ለማስተርስ ዲግሪ ያቀረቡትን ጥናታዊ ጽሁፍ “Transformative Spaces: Enabling Authentic Female Leadership Through Self Transformation – the Association of Women in Business” ወደሚል መጽሐፍ ቀይረው ባሳተሙት ገጽ 16 ላይ በትውልድ ኢትዮጵዊት በዜግነት ግን ካናዳዊት መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ከዚህ አንጻር ከታየ ሹመታቸው የሕግ ጥያቄ እንደሚስነሳ የሪፖርተሩዳዊት እንደሻው ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያ ይናገራሉ፤ “አዋጅ ቁጥር 270/1994፣ ‹‹የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎች በትውልድ አገራቸው የሚኖራቸውን መብት ተጠቃሚነት ለመወሰን በወጣው ሕግ መሠረት፣ ማንኛውም የውጭ ዜግነት ያለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ በማናቸውም የአገር መከላከያ፣ የአገር ደኅንነት ወይም በውጭ ጉዳይና መሰል የፖለቲካ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በመደበኝነት ተቀጥሮ መሥራት እንደማይችል ተደንግጓል፤” ይላል።

“በዚህም አዋጅ መሠረት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትም እንደ አንድ ወሳኝ የፖለቲካ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የውጭ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መቀጠር እንደማይችሉ፣ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ይህ ጉዳይ መንግሥት ትኩረት ሊሰጥበት የሚገባው ነው። ምክንያቱም ዜጎች ለየትኛው ፖስፖርት ነው ታማኝነታቸው የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል … ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ እንዲህ ዓይነት ቦታ ላይ መቀመጥ ካለባቸው፣ የያዙትን የውጭ አገር ዜግነት መመለስ ይገባቸዋል” ሲሉ አንድ የሕግ ባለሙያ ተናግረዋል።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ሪፖርተር ፕሬስ ሴክሬታሪዋን በስልክ የጥሪና የጽሑፍ መልዕክት፣ እንዲሁም በትዊተር ገጻቸው መልዕክት በመላክ ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል። አለቃቸውን አቶ ሽመልስ አብዲሣንም ለማግኘት ደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት ሪፖርተር ጠቅሷል።

ሪፖርተር ለቃል አቀባይዋ በስልክ የጥሪና የጽሑፍ መልዕክት፣ እንዲሁም በትዊተር ገጻቸው መልዕክት ቢልክም መልስ ማግኘት አልቻለም። በተጨማሪም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተደርገው የተሾሙትን አቶ ሽመልስ አብዲሳን ለማግኘት የተደረገው ሙከራም አልተሳካም።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *