የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) አመራሮች እንደሆኑ የተነገረላቸው በርካታ ሰዎች በግልጽ ባልተነገረ ምክንያት መታሰራቸው ተሰማ። ሰሞኑን ፈጸሙት የተባለውን የሙስና ወንጀል ሲያስተባበሉ የነበሩት የሚቴክ ሃላፊና ምክትላቸው ግን ከታሰሩት ውስጥ ስለመኖራቸው የተባለ ነገር የለም። የዛጎል ምንጭ የታሰሩት ሰዎች ሰላሳ ስድስት መሆናቸውን አመልክተዋል ቢናገሩም ፖሊስ ከሃያ በላይ ናቸው ብሏል።

ፖሊስ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንዳስታወቀው ሌሎች ተጠርጣሪዎችን የመያዙ ስራ እየተሰራ ነው፡፡ ፖሊስ ይህንን ቢልም ስለ ማንነታቸው ማብራሪያ አልሰጠም። በሕዝብ ሃብትና ንብረት፣ እንዲሁም ከፍተኛ የገንዘብ መጠን በማባከን የሚወነጀሉት የሜቴክ አመራሮች ሙሉ በሙሉ እንደሚታሰሩ ቀደም ሲል በተደጋጋሚ መገለጹ የሚታወስ ነው። ፕሊስ ሰኞ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

የሚቴክ ከፍተኛ አመራሮች ድርጅታቸው በጠቅላይ ኦዲተር ኦዲት ተደርጎ እንደማያው ነገር ግን ለአገሪቱ ተቋማት ሞዴል የሆነ የሂሳብ አሰራርን ይከተል እንደነበር፣ የሚወራው በሙሉ ፈጠራ መሆኑንን ሃላፊው ሰሞኑን መናገራቸው ይታወሳል። ይህንኑ ተከትሎ የጠቅላይ ኦዲትር በተደጋጋሚ ኦዲት ለማድረግ ጥያቄ አቅርቦ በማስፈራሪያ ጭምር ስራውን ሊያከናውን አለመቻሉን ተናግረዋል። 

እጅግ ከፍተኛ ሃብት የተዘረፈበትና አገራዊ ፕሮጀክቶችን ያነጠፈው ሚቴክ ሃላፊዎች ትግራይ እንደሚገኙና ክልሉ አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛአ ለመሆኑ ቢነገርም፣ ዶክተር ደብረጽዮን ግን አስተባብለዋል። ሌባን አቅፈው እንደማይዙም ተናግረዋል። ይሁን እንጂ በተግባር የታየ ነገር ስለመኖሩ ፖሊስ የሚሰጠው መግለቻ የሚጠበቀ ይሆናል።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *