ደርግ ሹማምንት ጠመንጃ አንስተዉ በሚወጓቸዉ ፓርቲ ወይም ቡድናት አባላት ላይ የሰሩት ግፍ መንግሥት በሚቆጣጠራቸዉ በኢትዮጵያ መገናኛ ዘዴዎች ሲዘረዘር ፣ያለፈዉን ግፍ አስዘርዛሪ አስተንታኞች የራሳቸዉን ግፍ፣ ዓይነት ባይነት እየዋሉ እንደነበር መስማት በርግጥ እንቆቅልሽ ነዉ።

የቀድሞ ሹማምት የዋሉት ግፍ

ኢትዮጵያዊዉ የሕግ ባለሙያ ተማም አባቡልጎ ሕዝብ፤የሕግ ሰዎች እና ተበዳዮች 27 ዓመታት የጮኹበት፤ ቅኝ ገዢ መሠል መንግሥት የዋለዉ ግፍ የመጋለጡ ጅምር ይሉታል።የቀድሞዉ እስረኛ ያሁኑ ባልደረባችን ተስፋዓለም ወልደየስ በፋንታዉ «የመንግሥትን ወንጀል መንግሥት ሲያሳጣ» አለዉ።እርግጥ ነዉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ከጥቂት ወራት በፊት አሸባሪዉ «መንግሥት ነዉ» ዓይነት ብለዉ ነበር።የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ብርሐኑ ፀጋዬ ዛሬ፣ የሕግ ባለሙያዉ የቅኝ ገዢ መሰል፤ ወይም የጮኽንበት፤ ጋዜጠኛዉ የመንግሥት ወንጀል፤ጠቅላይ ሚንስትሩ «ሽብር» ያሉት በደል መፈፀሙን በይፋ አረጋገጡ። 

እንደ ዓላማ እና መርሁ ቢሆን ኖሮ የሕዝብ ደሕንነትን መጠበቅ ወይም ማስከበር ነበረበት-ኃላፊነቱ።ስሙም ይኸዉ ነዉ።የብሔራዊ መረጃ እና ደሕንነት መስሪያ ቤት።ምግባሩ ግን ኢትዮጵያዉያንን ማፈን፤ማሰር ማሰቃየት ነበር። 27 ዘመን።አገልግሎቱ ፈጣን የህክምና ርዳታ የሚሻ  በሽተኛን ሐኪም ቤት ማድረስ ነበር።አምቡላንስ።የኢትዮጵያ ገዢዎች በተለይም የመረጃ እና ደሕንነት መስሪያ ቤት ሹማምንት እና ባልደረቦች ግን፣ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ብርሐኑ ፀጋዬ እንዳሉት የታፈኑ ሰዎችን ድብቅ እስር ቤት ማድረሻ አደረጉት።

ኦዲዮውን ያድምጡ

                                         

Äthiopien Kundgebung Premierminister Abiy Ahmed in Addis Ababa | Explosion (Oromo Media Network)

 

የሕግ ባለሙያ ተማም አባቡልጎ ግፍ በደሉ ለኛ አዲስ አይደለም ዓይነት ይላሉ።ስንጮኽበት የነበረ።የደርግ ሹማምንት ጠመንጃ አንስተዉ በሚወጓቸዉ ፓርቲ ወይም ቡድናት አባላት ላይ የሰሩት ግፍ መንግሥት በሚቆጣጠራቸዉ በኢትዮጵያ መገናኛ ዘዴዎች ሲዘረዘር ፣ያለፈዉን ግፍ አስዘርዛሪ አስተንታኞች የራሳቸዉን ግፍ፣ ዓይነት ባይነት እየዋሉ እንደነበር መስማት በርግጥ እንቆቅልሽ ነዉ።ብዛት ዓይነቱ ደግሞ አስደማሚ።

ተስፋ ዓለም ይኸ ሁሉ ግፍ ይደርስ ነበር?ታዉቃለሕ ወይም አይተሐል?ሰዉ አደጋ በማያደርስበት፤ በታሰረ፤ ያዉም በገዛ ዜጋዉ ላይ ይሕን መሰል በደል ማድረስ በርግጥ የጤና ይሆን? የሕግ ባለሙያዉ መልስ አላቸዉ።ተስፋዓለም አንተና ባልደረቦችሕ ማዕከላዊ በሚባለዉ እስር ቤት በደርግ ዘመን ግፍ ሥለተፈፀመባቸዉ ሰዎች ታሪክ የጻፋችሁትን አንብቤያለሁ።እራስሕ ያየሕ ወይም የደረሰብሕን ግን አልፃፍክም? ያየኽዉ ወይም የሰማኸዉ ግፍ ይፈፀማል ብለሕ አስበሕ ታዉቅ ነበር።

ሰኔ 16፣ 2010።የአዲስ አበባ ሕዝብ በተሰበሰበት መሐል ቦምብ ፈነዳ።ሁለት ሰዉ ሞተ።በመቶ የሚቆጠሩ ቆሰሉ።የቦምብ አፈንጂዎቹ ዓላማ አዲሱን ጠቅላይ ሚንስትር ለመግደል ነበር ።የመረጃና እየደሕንነት መስሪያ ቤት ኃላፊዎች አዲሱን ጠቅላይ ሚንስትር

Äthiopien Addis Abeba Verletzte nach Bombenexplosion (Ahmed)

ለማስገደል የሸረቡት ሴራ ኦሮሞን በኦሮሞ የሚል ነበር-ይላሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ።

ግፍ በደሉን አድርሰዋል ተብለዉ የተጠረጠሩ ሰላሳ ስድስት ሰዎች መታሰራቸዉን ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ አስታዉቀዋል።ሌሎችንም ለመያዝ ምርመራዉ ቀጥሏል።የቀድሞዎቹ ገዢዎች የዘረፉት የገንዘብ መጠን፤ ምናልባት ገዢዎቹ በራሳቸዉ ዜጋ ላይ ዘግናኙን ግፍ የፈፀሙበትን ምክንያት ለማወቅ ፍንጭ ይሰጥ ይሆናል።ለዘረፋ የሚመቸዉን ሥልጣን ማስጠበቅ። ሜቴክ የተባለዉ የመከላከያ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ብቻ፤ያለጨረታ ከዉጪ ተገዛ ለተባለ ሸቀጥ ብቻ 37 ቢሊዮን ብር አዉጥቷል።በደል ግፉ አድርሰዋል፤ ገንዘብ ዘርፈዋል  ተብለዉ የተጠረጠሩ ባጠቀላይ ከ60 በላይ ሰዎች ታስረዋል።ቀጥሎስ?

ነጋሽ መሐመድ 

አዜብ ታደሰ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *