በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ምህረት ነጻ ወጥቶ ለአገሩ ምድር የበቃው ኦነግ ከኦሮምፕ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኦዴፓ ጋር ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት በመፍታት አብረው ለመስራት መስማማታቸውን አስታወቁ። ውሳኔው ሰፊ ድጋፍና አድናቆት እየተቸረው ነው። ስምምነቱ ወደ ውህደት ሊያመራ እንደሚችል የገመቱም አሉ።

ከሰፊ ውይይት በሁዋላ መግባባት ላይ መደረሱን ያመለከቱት የሁለቱም ፓርቲ መሪዎች ካሁን በሁዋላ በፍጹም መተማመን እንደሚሰሩ ተናግረዋል። አቶ ለማና አቶ ዳውድ በኦሮሚያ ቲቪ ቀርበው ይህንኑ ሲያረጋገጡ እንደታየው ቃላቸውንና ስምምነታቸውን በአኦሮሞ ባህላዊ የምረቃ አግባብ አረጋግጠዋል። ፋና የሚከተለውን ዘግቧል።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ምክትል ሊቀ መንበርና አቶ ለማ መገርሳ እና የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ፥ ለሃገር ሰላም፣ ልማትና ዕድገት ከዚህ በኋላ በመደማመጥ በጋራ እንሰራለን ብለዋል በመግለጫው ላይ።

በሃገርና ህዝብ ላይ ጉዳት ሲያደርሱ የነበሩ ወገኖች ለህግ እንዲቀርቡና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ህዝቡ ለመንግስት ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባም ተናግረዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ህዝቡ ልማትን ለማስቀጠል ሴረኞችን በማጋለጥ ከመንግስት ጋር ሊሰራ እንደሚገባም ነው የተናገሩት።

ቄሮ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆኑ አክቲቪስቶች የተገኘውን የፖለቲካ ድል በመደማመጥና በመደጋገፍ ከዳር ሊያደርሱት ይገባልም ነው ያሉት።

በትግሉ ውስጥ ሁሉም የድርሻው እንዳለው ሁሉ ቀጣይ የሃገሪቱንና የህዝቡን እጣ ፈንታ ለመወሰን በጋራ መስራት ጊዜው የሚጠይቀው ጉዳይ መሆኑንም አንስተዋል።

የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በበኩላቸው፥ ኦነግ ከኦሮሚያ ክልልና ከፌደራሉ መንግስት ጋር አብሮ ለመስራትና በቀጣይ ሊታዩ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ በመነጋገር ለሃገር እድገት አብረው ለመስራት መስማማታቸውን ገልጸዋል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

ኦነግና የኦነግ ሰራዊትም በሰላማዊ መንገድ በመንቀሳቀስ ከመንግስት ጋር አንድ በመሆን ይሰራልም ብለዋል በመግለጫቸው።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *