የሰብአዊ መብት ጥሰትና ዝርፊያን አስመልክቶ የተደበቁ ቁልፍ ተፈላጊዎች በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ተሰማ። የቀድሞው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትርና የአሁን የህወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ጌታቸው ረዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝን ተተያቂ አደረጉ። አሁንም ጸቡ ከትምክህተኞች ጋር ነው ሲሉ ተደመጡ።

ለዛጎል ስማቸውን ሳይጠቅሱ የተናገሩ የኦህዴድ ከፍተኛ አመራር እንዳሉት፣ በየትኛውም ስፍራ ያሉ ተፈላጊዎች በቁትጥር ስር የሚውሉበት ቀን እጅግ ቅርብ ነው። እሳቸው እንዳሉት ስም ሳይጠቅሱ አንዳንድ ክልሎች በብሄር ስም ተፈላጊዎችን የመደበቅ አዝማሚያ ቢያሳዩም ከልብ አይደለም።

ከልብ አይደልም የሚለውን ሲያብራሩ ” አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ማንም ክልል ከፌደራል ክልል የመነጠልና የራሱን ደሴት የመፈጠር አቅምም ሆነ ህዝብን መሰረት ያደረገ ድጋፍ አይኖራቸውም። በዚህ መስፈርት የሚናፈሰው ወሬ ሁሉ ስሜት እንጂ ከእውነት ጋር ግንኙነት የለውም” ለማለት እንደሆነ አመልክተዋል።

ባለስልጣኑ አያይዘውም ወዳጅ አገሮችም በዚህ ጉዳይ ከሚፈለገው ርቀት አልፈው ጫና እያደረጉ መሆናቸውንና    በውጪ አገር የብር ተቋማትም መረጃ በመስጠት መተባበራቸውን አመልክተዋል። መረጃ ከሰጡት አገራት ባንኮች መካከል ቻይና አንደኛዋ አገር መሆኗን ጠቁመዋል። 

ይህንኑ በሚያጠናክር መልኩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዘመቻው እንደሚቀጥል ትናት ባሰተላለፉት ባለ አራት ገጽ ጽሁፍ ለህዝብ አረጋግጠዋል። ሲዘርፉ የራሱትን ህዝብ፣ ችግር ሲገጥማቸው መሸሸጊያ ማድረግ እንደማይቻል ባሳስገነዘቡበት መግለጫቸው፣ ህዝብ “ካንሰር” ሲሉ የጠሩትን ዝርፊያ አንድ ሆኖ እንዲታገል አሳስበዋል።

በተመሳሳይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ” ልክስክስ” ሲሉ የጠሩትን ዝርፊያ ክልላቸው እንደማይቀበልና የዘርፊ ምሽግ እንደማይሆን አመልክተዋል። ፋና ” ክልሉ የተጠርጣሪ መደበቂያ እንደማይሆንና ማንኛውንም በህግ የሚፈለግ ተጠርጣሪ ተጠያቂ ለማድረግ የክልሉ መንግስት ከፌደራል መንግስት ጋር በመቀናጀት ይሰራል ” ማለታቸውን አትሟል። ከምዕራባዊ የህብረተሰብ ክፍል የህዝብ ተጠሪዎች ጋር ባደርጉት ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ነው ይህንን ያሉት። 

“አማራና ኦሮሞ እንዴት ሊስማሙ ቻሉ። ይህ ሁሉ የእኛ ጥፋት ነው” በሚል በይፋ አስተያየት ከሰጡ በሁዋላ በሄዱበት ሁሉ ክፉኛ ተቃውሞ የሚሰነዘርባቸው አቶ ጌታቸው ለኤልቲቪ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ተቀንጭቦ በቀረበበት የማስተዋወቂያ ቅንብር ላይ እንዳሉት አቶ ሃይለማሪያ ለስድስት ዓመታት ምን እርምጃ ሳይወስዱ መቆየታቸው ሊያስጠይቃቸው እንደሚገባ አመልክተዋል።

እርማጃ እንዲወስዱ በተደጋጋሚ እንደመከሩዋቸው ያስታወቁት አቶ ጌታቸው፣ መረጃ ደርሷቸው እርምጃ እንደሚወስዱ በተደጋጋሚ ካሳወቁ በሁዋላ መልሰው አድናቂና አወዳሽ ሲሆኑ እንደሚታይ ተናግረዋል። 

አሁንም ስለ ትምክህተኛ አስተሳሰብ መናገር ያላቆሙት አቶ ጌታቸው ” አሁንም ትግሉ ከትምክህተኛ አስተሳሰብ ጋር ነው” ሲሉ አማራውን ከፊውዳል ዘመን አስመላሽነት ጋር አያይዘው ሲመልሱ ተሰምቷል። “አቶ ኢሳያስም ትግራይ ቢመጡ ያለ አስተርጓሚ መግባባት ይችላሉ” የሚል ምጸት አሰምተዋል። አነጋገራቸው ኢሳያስ አፉወርቂ ላይ ያላቸውን ንዴት የሚያሳብቅ ይመስላል።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *