በሰብአዊ መብት ጥሰትና በከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ የተጠረጠሩ አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፍ ኢሶህዴፓ አስታወቀ

በሃገር አቀፍ ደረጃ በሰብአዊ መብት ጥሰትና በከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ የተጠረጠሩ አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፍ የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶህዴፓ) አስታወቀ፡፡

ኢሶህዴፓ ለኢቲቪ በላከው መግለጫ እንደጠቀሰው የተጀመረው ሃገር አቀፍ የለውጥ ጉዞው ያስቆጠረው ዕድሜ አጭር ቢሆንም የተገኘው ውጤት ግን በክልሉ ታሪክ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው ነው::

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

ኢሶህዴፓ በክልል ደረጃም ሰብአዊ መብት በጣሱና ስልጣናቸውን ለግል ጥቅም ባዋሉ፣ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር እጦት እንዲስፋፋና የህግ የበላይነት እንዳይሰፍን ባደረጉ አመራሮች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታውቋል::

ድርጅቱ እርምጃውን መውሰድ የጀመረው ባለፉት ጊዜያት ባደረገው ጥልቅ ተሃድሶ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ነው ብሏል መግለጫው:: ይህንን መሰረት በማድረግም በክልሉ አመራሮች ላይ እርምጃ በመውሰድ ለህግ እያቀረበ እና ስር ነቀል ለውጥ በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጿል::

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

በክልሉ የተጀመረውን ለውጥ ከሃገራዊ ለውጡ ጋር በማስተባበር የለውጡን ዘላቂነት ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ለውጡ ተቋማዊ እንዲሆን ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ መሆኑንም ኢሶህዴፓ ገልጿል::

የክልሉ ሕዝብና የኢሶህዴፓ አመራሮቸ እና አባላት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ከመንግስት ጎን በመቆም ሃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪውን አስተላልፏል::

የኢሶህዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት
ህዳር 07/2011ዓ.ም

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *