ለውጡን ተከትሎ ብልጭ ድርግም የሚሉት ግጭቶችና መፈናቀሎች አሁን እየከሰሙ ያሉ ይመስላሉ። ቀደም ሲል የተዘራው ጎሳ ላይ የተተከለ ጥላቻና በታማኝነት ላይ የተመሰረተ መዋቅር ለውጡን በመስጋት ወደ ወደ ማተራመስና አምርቶ ነበር። የለውጥን መሰረታዊ ባህሪ በውል ባለመረዳት ከየአቅጣጫው በለውጡ አራማጆች ላይ የጥላቻ ቅስቀሳም ሲቀጣጠል ነበር። ዛሬ ግን ነግሮች እየተቀየሩ መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ዜናዎች እየተሰሙ ነው። አፋር ክልል መደመሩን ይፋ አድርጓል።

ለውጡ እውን ከመሆኑ በፊት አዲስ አበባ ዙሪያ የተቃረበው ተቃውሞ ዛሬ የለም። ከለውጡ በፊት ድፍን ሁለት ዓመት በድፍን አገሪቷ የተቀጣጠለው የለውጥ ትግል በጠመንጃ እንኳን የሚቆም አልነበረም። ዛሬ ውስን በሆኑ ቦታዎች ከሚታየው በቀር በኦሮሚያ ችግሩ ተፈቶ ቦረና ሲቀር ሌላው ሰክኗል። አማራ ክልል ከትግራይ ክልል ጋር ቀደም ሲሉ ጀምሮ ከነበሩ የማንነት ጥያቄ ውዝግብ በስተቀር በሌሎች ቦታዎች የቀድሞው ሰሜታዊ ስካር የለም።

በደቡብ ክልል የሲዳማ ጥያቄ ምላሽ ካገኘና ሌሎቭም የዞንንና ተመሳሳይ ጥያቄዎች እልባት እንዲሰጣቸው ከተወሰነ በሁዋላ ዛሬ የሚሰማው ዜና እርቅና አብሮነት ነው። በሶማሌ ክልል አልፎ አልፎ የማፈንገጥ ነገር ቢታይም የተፈራው ችግር ተቀልብሶ፣ ፍትህ እየተጠበቀ ነው።

በቤኒሻንጉል ክልል ችግር እየፈጠረች ያለችውን “ኮሪዶር ” ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መላ እንዲበጅላት በጥብቅ እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል እና የፌደራል መንግስት እያስታወቁ ናቸው። አንዳንድ ስትራቴጂካል ስምምነቶችም እየተደረጉ መሆናቸውን ተወዳጁ ኢቲቪ እያሳየን ነው። የጋምቤላ ክልልም የተደገሰለትን የሞት ጥላ ገፎ ፣ እርስ በርስ ከመባላት ድኖ መደመሩን ይፋ ማድረጉን አዲሶቹ መሪዎች በገሃድ አስታውቀዋል።

በከፍተኛ ደረጃ ሲሰራበት የቆየውና ስጋት ተደቅኖበት የነበረው የአፋር ክልልም ዛሬ ” በበቃኝ” እልባት ማግኘቱ የቀኑ ሰበር ዜና ሆኗል። የክልሉ መሪ ሃጂ ስዩም አወል ” እኛ በቃን ተራው አሁን የተማሩት ወጣቶች ነው” ሲሉ ተሰምተዋል። አዲስ አበባ ሶስት ቀን ግምገማ ያካሄደው ፓርቲያቸው የውሳኔ ሃሳብ በመያዝ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ተወያይቷል።

በውይይቱ ላይ የግምገማቸውን ውጤትና የመፍትሄ ሃሳባቸውን አቅርበዋል። በዚሁ መሰረት ክልሉ በትሥሥር ዝርፊያ የሚካሄድበት። በመጠቃቀም ስርቆት የሚፈጸምበት፣ የሰብአዊ መብት የሚጣስበት፣ መናገር፣ መጻፍ፣ መቃወምና የፈለጉትን መደገፍ የማይቻልበት፣ በእቅድ የማይሰራበት፣የስልታን ሽኩቻ የሰፈነበት፣ በጥቅሉ ክልሉ በአመራር ደረጃ ውድቀት ላይ የነበረ፣ ፐሮጀክቶች በሙስና የሚተላለፉበትና የማይጠናቀቁበት፣ የጨው ማእድን በትሥሥር የሚቸበቸብበትና የሚባክነበት፣ ከአመራሩ ጋር ግንኙነት ያላቸው የሚዘርፉት እንደሆነ በሚኒስትር ማዕረግ የኢህአዴግ አጋር ፓርቲዎችና የሲቪል ማህበራት አስተባባሪ አቶ ፈቅዱ ተሰማ ተናግረዋል።

ቀለም ያልዘለቃቸው በሚል የሚታሙት የክልሉ መሪ ሃጂ ስዩም ችግሮቹን አስመልክቶ ግምገማ መደረጉን አመልክተው ” እኔ በቃኝ” ብለዋል። አንጋፋው አመራር በክብር ተሸኝቶ የተማሩ ወጣቶች ወደ አመራር ይወጣሉ። በቅርቡ ጉቤኤ ይካሄድና ይሄው ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል። ኮንፍራንስም ይካሄዳል። ሃጂ ስዩም መልዕክትም አስተላልፈዋል ” ክልላችሁን ጠብቁ፣ ሰላም ጠብቁ” ሲሉ።

ስለ አፋር ክልል የሚከታተሉ እንዳሉት ክልሉ ላይ በከፍተኛ ደረጃ ተቃውሞ ሲያካሄዱና በአገሪቱ የተጀመረው ለውጥ ወደ ክልላቸው እንዲዘልቅ ሲጠይቁ መቆየታቸውን ያስታወሳሉ። ይህንኑ ተከትሎ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን ይጠቁማሉ። የተገደሉ፣ አካላቸው የጎደልና፣ የታሰሩ ጥቂት አይደሉም። ከከፍተኛ መስዋዕት በሁዋላ በጥንቃቄ ወደዚህ መሰሉ ደረጃ መደረሱ የክልሉን የለውጥ አራማጆች እንዳስደሰተ ይናገራሉ። አያይዘውም ህዝብ ያለገደለና መሳሪይ በመወደረ በጅምላ የማያስር መንግስትን አቅም እንደሌለው አድርጎ ከማሰብ በሽታ እንዲላቀቅም መክረዋል። 

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *