ከንቲባ ታከለ ኦማ ጅግና ናቸው። ሆለታ እያሉ አላሙዲ ለአበባ እርሻቸው በሄክታር ሃያ ሳንቲም ሂሳብ ለዓመታት አልከፈሉም በሚል እርሻውን እንደሚነጥቁ ያሳሰቡ፣ በዚህ ምክንያት ሆለታ ላይ የቴክኒክ ትምህርት ቤት ባምስገንባት ጭምር ህዝቡን እንደሚክሱ ቃል ሲገቡ፣ ግንባታው ቀርቶ ግብሩን ይክፈሉ ሲሉ በፊት ለፊት የተፋለሙ ናቸው።

ዛሬ አዲስ አበባ መካከል ፒያሳ ላለፉት ሃያ አንድ ዓመታት ታጥሮ የኖረው ግንባታ ሲከፈት የታየው ጉድ ይህ ነው። ምስሉን ያገኘሁት ከታምሩ ጽጌ ፌስቡክ ላይ ሲሆን የሚገርመው ቦታው የተሰጠው ያለ አንዳች የሊዝ ክፍያ በነሳ ነው። ዱዲ አላወጡበትም።ይህንን እና ሌሎች ጉዳዮችን ለምን ጻፋቹህ በሚል ግን ግድያ የተሞከረባቸው፣ ግድያው ሲከሽፍ አስገዳዩን በማስፈርጠጥ ጉዳዩን አሳፍነዋል። ይህንን ጉዳይ የወቅቱ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ወቅነህ ገበየሁ ያውቃሉ። ቁጭ ብለን ተነጋገረናል። ፋይሉም በእጃቸው ነው። እናም ፍትህ እንፈልጋለን።  በየቀኑ በድንጋጤና በፍርሃት የኖሩም አሉ። ለሁሉም ጊዜ አለው። ሃያ አመት የታጠረው ባለ አርባ ሁለት ፎቅ ህንጻ እንዲህ አምሮበት ይታያል ሲል ፎቶውን የተዋስኩት ጽፏል። አዎ አምሮበታል!! አቃጣሪዎች ዛሬስ ምን ትሉ ይሆን?

 

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *