የግል እይታ 
1 – መግለጫው ከሌሎች ክሎች ቡተለየ መልኩ በቅድመ ሁኔታና በማሳሳብያና፣በስጋት የታጀበ ነው።
የፀረ ሙስና ክስ በአገሪቷ የወንጀልና ሙስናን በሚመለከት የወጡ ህጎችን እንዲሁም ስነስርአቶችን መሰረት አድርጎ የሚታይ ከመሆኑ አንፃር የመንግስታቱ መግለጫ ፉይዳው ፓለቲካዊ እንጂ የህግ ውጤት አይኖረውም።ህግ ፊት የክርክር ጭብጥ ሊሆን የሚችለው ተጠርጣሪዎቹ ህግ ንና ስርአትን ተላልፈው ስልጣናቸውን በመጠቀም የመንግስትንና የህዝብ ህብት ለራስ ወይም ለሶስተኛ ወገን ጥቅም አውለዋል ወይ?የሚለው ነው ። አዎ ክሆነ በአቃቤ ህግ ማስረጃ፣የለም ክሱ የሀሰት ነው የሚለው ወገን የተከሳሽ መከላከያ ሆኖ በመቅረብ የአቃቤ ህግ ማስረጃን ሊያስተባብል ይችላል ከዚያ በዘለለ አንድም ለፓለቲካ ሸቀጥና ማደናገርያ ለመፍጠር የተወጠነ ሴራ ነው። ሁለትም ጉዳዩ በአብላጫው እነማን ላይ ሊያርፍ እንደሚችል ስለሚገመት አውቶብሱ መድረስ ያለበት ሳይደርስ እንዲቆም ጫና ለመፍጠር ነው።
ጉዳዩ የህግ ጉዳይ እንደመሆኑ አንድ ብሄር፣አንድ ብሄር የሚለው ክስም ሆኖ ጉዳዩን ህብረ ብሄራዊ እንደሆነ ለማስረዳት የሚሰጠው ምላሽ ሁለቱም አደገኛ ናቸው።ተጠርጣሪው በተከሰሰበት ወንጀል ያለውን ተሳትፎ እንጂ የብሄር ተዋፆን ለክስም ሆነ ለመከለከያነት የማያገለግል መሆኑ እየታወቀ ማሳሰብያ መደርደሩ ነገር ፍለጋ ይመስለኛል።
ምክንያቱ ደግሞ ሁሉም በግሉ የዘራውን እንደሚያጭድ ቢታወቅም እነማን ቤት በርከት እንደሚል ዛሬ ሳይሆን ከዛሬ 18 አመት በፊት አውቀናል፣ገምግመናል።ስለምን ሰበብ አስባብ እንፈጥራለን?
ለምንይዋሻል?ዶር ደብረ ፅዮን ህወሀት ቤት ሙስና እንደተበራከተ ዛሬ ነው የሰሙት ?
ወደ ኋላ መለስ ብየ ቆየት ካለ የኢህአዴግ ሰነድ ቃል በቃል ላስታውሳችሁ፣የሰነዱ ርእስ “ትምክህትና ጠባብ ነት ከስር መሰረታቸው ይነቀሉ”ሰኔ 1993 በቀድሞው መለስ ዜናዊ ተዘጋጅቶ ለከፍተኛ አመራር ውይይት የቀረበ ሲሆን በወቅቱ ዛሬ አደባባይ ወጥቶ አገር የተዘረፈበት ሌብነት አዝማሚያዎቹና ምልክቶቹ እየተስፋፉ መሆናቸውን ምክንያት በማድረግ በድርጅቱ ውስጥ፣በተለይም በአጋር ፓርቲዎች ውስጥም ጥርጣሬና ማጉረምረም በመበራከቱ ጉዳዩን እንዳላዩ ማለፍ ስለማይችል ቢያንስ ለውይይት አቅርቦ ልማስተንፈስ በማሰብ የተዘጋጀ የተሀድሶ ሰነድ ሲሆን ጥቂት ሀረግ እንምዘዝ
–በትግራይ የታየው ጠባብ ነት ልዩ ገፅታ በሚለው ርእስ ገፅ 25 ከሰፈረው
-“በህወሀት ውስጥ በከፍተኛ አመራር ደረጃ እየተጠናከረ ከመጣው እራስን ወደጥገኛ መደብ የማሸጋገር ዝቅጠት ጋር የተያያዘ ነው።
ይህ እራሱን ወደ ጥገኛ ገዥ መደብ ያሸጋገረ ሀይል ከሌሎች ጋር በመተሳሰር #ሰፋያለሙስና #ያለአግባብ#የመበልፀግ ተግባር ላይ ከተሰማራበት ሁኔታ ታይቷል።”
—እዚህ ዝቅጠት ውስጥ ከገቡ ቦሀላ የየያዙትን ስልጣን በርስትነት በመያዝ አዛዥ ናዛዥ የመሆን ፀረ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ እከገነገነ መጥታል።”
“ይህ ሀይል የትግራይ የበላይነት የተጠናወተው አዲስ ገዥ መደብ የመሆን አመለካከት እያመጣ ያለፈው ስርአት አኝኮ የተፋውን ትምክህተኛ አመለካከት እየወረስ መጥቷል።”ይልና ሱቀጥል
–“በአሁን ሰአት መክበር፣በይበልጥ መጠቀም አለብኝ የሚል አመለካከት እየተጠናከረ የመጣበት ሁኔታ አለ”
-“የትግራይ ጥገኞች በህወሀት የነበሩና የበሰበሱ አጋሮቻቸውን ጨምሮ በትግራይ ስም መነገዳቸውናመንግስትን ስልጣን በመጠቀም ያለ አግባብ መክበራቸው በየ አከባቢው ሙስና እና ፀረ ዲሞክራሲ በህወሀት ስም መፈፀሙ ለተቃዋሚዎች አመለካከታቸውን እንዲያ ሰራጩ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። “
ይህ ከላይ የዘረዘትኩት ሀሳብ እንዳለ ከሰነዱ የተወሰደ ነው።
ልብ ይበሉ የዛሬ 18 አመት የተደራጀ ሙስና ውስጥ ከፍተኛ አመራሩ መዘፈቁን ኢህአዴግ ገምግሞታል።በዚያ ኢኮኖሚ።በዚያ ተጨባጭ ሁኔታ የህወሀት ከፍተኛ አመራር ሌብነት ውስጥ መግባቱ የታየበት ብቸኛ ብሄራዊ ድርጅት ነበር።
አሁን ከድርጊቱ ተምሯል ወይ?
ስርቆት በግለሰብ ደረጃ ቢከናወንም ፓርቲው የግንባር ቀደም ስብስብ ነኝ እያለ የአባላቱን ስነ ምግባር ማረም ስለምን አቃተው?ሌቦችን እየሾመ እየሸለመ እንደ ፓርቲ ሀላፊነት መውሰድ የለበትም ወይ?
ሌባ ብሄርን እና ህዝብን አይወክልም ይሆናል ፣ፓርቲዎች ግን የሌቦች ስብስብ እየሆኑ እንዴት ከደሙ ንፁህ ይሆናሉ?ለኔ እንዲህ አይነት የአመራር ብልግና የሚታይባቸው ፓርቲዎች እየበሰበሱ መሆናቸውን ያረጋግጥልኛል።የመግለጫ ጋጋታም የዚህ መገለጫ ነው።ንቅዘቱ ተቌማዊ እየሆነ ስለመጣ የማውገዝ ሞራል አይኖርም
ሳጠቃልል ሌባ የሚወክለው ብሄር የለም። የሌብነት አዝማምያ ግን ገና ከጠዋቱ 1993 ጀምሮ በህወሀት ፊት አውራሪነት መጀመሩን ታሪክ ያስረዳል እርግጥ ነው ዛሬ ላይ የተሳታፊው ቁጥር በመጠኑ ጉራማይሌ ሊሆን ይችላል፣ነገር ግን እነደብረፅዮን ቤት ቁጥሩ ቢበራከትም ዶር፣አብይ ወይም እነርሱ እንደሚሉት እሳያስ ያመጣው መቅሰፍት ሳይሆን አልታረም ያለ የአመራር ስግብግብነት የፈጠረው ስለሆነ በከንቱ አቧራ ባታነሱ።
በሊቁ በነበሩ የተፃፈ። ሊቁ ጥሩ ነጥብ ነው ያስታወስከን።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *