– ይፋ በሆነው የግፍ ሰቆቃ ዓለም ዓቀፍ ጫናው በርክቷል

ለህወሃት ቅርብ የሆኑ ለዛጎል እንዳሉት ህወሃት በወንጀልና በዝርፊያ የሚፈለጉትን የቀድሞ ባለስልጣናት እንዲያስረክብ ዓለም ዓቀፍ ጫና በርክቶበታል። የፌደራል መንግስትም ቢሆን በዚህ ጉዳይ ከቶውንም እንደማይለሳለስ በማሳወቁ ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ ለመስጥት ህወሃት ይሁንታውን ሰጥቷል።

በተለያዩ ጊዚያት በሰላማዊ ሰልፍና በመግለጫ ከትግራይ ክልል አካሄዱ አንድን ብሄረሰብ ነጥሎ የማጥቃት እንደሆነ በመጥቀስ ተቃውሞ ቢሰነዘርም፣ የፌደራል መንግስት ሊቀበለው አልቻለም። “በአሜሪካ አማካይነት ተሰየሙ” በሚል ዶክተር አብይን እንደማይቀበሉ የሚገልጹ የቀድሞ የህወሃት መሪዎችና ባለስልጣናት፣ በአደባባይ ዘለፋ እስከመሰንዘር ቢደርሱም አሜሪካ በገሃድ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን አስተዳደር እንደምትደገፍ ሃሜታውን በማስተባበል አስረግጣ ተናግራለች።

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

የዜናው ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ ዘመቻው ዓለም አቀፍና በአህጉር ደረጃ በህብረት የታገዘ በመሆኑ ነው ህወሃት ተጠርጣሪዎቹን አሳልፎ ለመስጥት የተስማማው። ምንም እንኳን በአደባባይ የጋለ ተቃውሞ ቢሰማም የህወሃት አመራሮች አካሄዱን ለመቀልበስ የማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸውን አምነዋል። ግትር ባህሪ ሲያሳዩ የነበሩትን ጨምሮ ወደ አንድ አቋም መጥተዋል።

በቅርቡ ኢንተርፖል ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንዳረጋገጠው፣ ማንም ሆነ ማን ወንጀል ሰርቶ መደበቅ እንደማይችል በይፋ መነገሩ ጉዳዩ በጥብቅ መያዙን አመላካች እንደሆነ ምንጮቹ አከለው ገልጸዋል። አያይዘውም የቀድሞው የድህንነት ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ የተለያዩ ተጠርጣሪዎች ህግ ፊት መቅረባቸውን ከሰዓታት ልዩነት ውስጥ ልንሰማ እንችላለን ብለዋል። ከሌለ ሶስተኛ ወገን ማረጋገጥ አልተቻለም እንጂ የተያዙም እንዳሉ ምንጮቹ ተናግረዋል።

Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

በሌላ ዜና በውጭ አገር ባንኮች ገንዘብ አካላትን በመለየት ከአጋር አገሮች ጋር ብ እመሆን ሰነዱ በዝርዝር የፌደራል መንግስት እጅ መግባቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *