አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ከሰማያዊ፣ ከኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና ከቀድሞው አንድነት ፓርቲ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ።

አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ሜክሲኮ በሚገኘው የመብራት ሃይል አዳራሽ ከአባላቶቹና ደጋፊዎቹ ጋር ውይይት እያደረገ ነው።

ውይይቱ አሁናዊ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና በቀጣይ የድርጅቱ መዋቅር ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

ንቅናቄው ከዚህ ቀደም የመጣበትን መዋቅር በመተው እንደ አስፈላጊነቱ የስም ለውጥ አድርጎ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ማድረግ የሚያስችል አደረጃጀት ለማድረግ መዘጋጀቱን የንቅናቄው አመራሮች ገልጸዋል።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

ከዚህ ባለፈም በሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች ዜግነት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ አደረጃጀት እንደሚከተልና፥ ይህን አስተሳሰብ ከሚደግፉ ፓርቲዎች ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል።

ንቅናቄው አሁናዊ የሃገሪቱን ሁኔታም በተስፋና በስጋት እንደሚመለከተውም ገልጿል።

ከዜግነት ፖለቲካ ጋር በተያያዘም ከሰማያዊ፣ ከኢዴፓ እና ከቀድሞው አንድነት ፓርቲ ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሱን የንቅናቄው ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ተናግረዋል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

የንቅናቄው ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው፥ ሃገሪቱ ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንድትሸጋገር ንቅናቄው የሚችለውን እንደሚያደርግ ነው የተናገሩት።

በውይይቱ ላይ በሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታና በድርጅቱ መዋቅር ላይ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ እየተሰጠባቸው ይገኛል።

ንቅናቄው የሚያደርገው ውይይት በነገው እለትም በመገናኛ ኮኮብ አዳራሽ የሚቀጥል ይሆናል።

በሃይለሚካኤል ዴቢሳ FBC

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *