– ምንጩ በግልጽ የማይነገርለት የጦር መሳሪያ ዝውውር አሳሳቢ ሆኗል

በተለይ በጋምቤላ በኩል የሚተላለፈው የህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር እጅግ አደገኛ መሆኑንን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ወገኖች በተደጋጋሚ ሲወተውቱ መቆየታቸው የሚታወስ ነው። ይሁን እንጂ ይህ አገሪቱን ወደ እርስ በርስ ግጭትና ስርዓት አልበኛነት ለመውሰድ የሚደረገው የመሳሪያ ዝውውር ሙሉ በሙሉ መግታት ባይቻልም አሁን አሁን ህዝብ በይፋ እየታገለው እንደሆነ የመንግስት ምንጮች ይናገራሉ።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በሱዳን በኩል ወደ አማራ ክልል ሲጋዝ የነበረ የጦር መሳሪያ ካሁን በሁዋላ ከሱዳን መንግስት ጋር በጥምረት ቁጥጥር እንደሚደረገበት በተሰማ ማግስት፣ ከጋምቤላ በሲኖ ትራክ ተጭኖ ኢሉአባቦር ቡሬ ወረዳ ሲደርስ በህዝብ ንቃትና ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉን የኦሮሚያ ክልል የወረዳው ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

ከደቡብ ሱዳን በጋምቤላ ህገወጥ የጦር መሳሪያ በገፍ እየገባ ነው፤ በጀቱ የማን ነው?

አርባ ሶስት ክላሽንኮቭ ጠብመንጃና አርባ አራት የጥይት ካዝና በህዝብ እገዛ በቁጥጥር ስር መዋሉን ያስታወቁት የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ታረቀኝ አሰፋ  ናቸው። በህገ ወጥ መንድ ሲዘዋወሩ የነበረው የጦር መሳሪያ የተያዘው በትናንትናው እለት መሆኑንንም ሃላፊው አመላክተዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ከጋምቤላ ክልል በሲኖትራክ ተሽከርካሪ ተጭኖ ሲጓጓዝ የተያዘው የጦር መሳሪያ ወደ መሃል አገር የሚጓጓዝ እንደነበር የፖሊስ ሃላፊው ተናግረዋል። መሳሪያውን ሲያጓጉዝ የነበረው ግለሰብ ስሙና ማንነቱን ፖሊስ ለጊዜው አልገለጸም።

ፎቶ – ኢዜአ

አገር መውደድ በተግባር ሊገለጽ ይገባል – ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *