ኩምሳ ድሪባ ምዕራብ ኦሮሚያ የመሸገው ታጣቂ ኃይል አዛዥ (commander) ነው። በ1996 አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተቃውሞ ሰልፍ ሲወጣ የመጀመሪያ አመት ማኔጅመንት ተማሪ ነበር። በ1998 የኦሮሞ አክቲቪስቶች በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የጀመሩትን “The strugle to resist oppression” እንቅስቃሴ ተከትሎ መንግስት በወሰደው እርምጃ ኩምሳ ድሪባ ወደ ቦረና ዞን በመሸሽ OLA(Oromo Libriation Army) ተቀላቅሎ ስልጠና ወሰደ።

ስልጠናውን ከወሰደ በኃላ ወደ አዲስ አበባ በመመለስ “ቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሚያ” በሚል ድብቅ ስም የሚታወቁ አክቲቪስቶችን ተቀላቀለ። ብዙም ሳይቆይ ደህንነቶች ኔቶርካቸውን በመበጣጠስ ዋና አንቀሳቃሽ የነበሩት ተስፋሁን ጨመዳ እና መስፍን አበበን ሲያስሩ ኩምሳ ወደ ናይሮቢ ፈረጠጠ። ብዙም ሳይቆይ OLA ባደረገለት ጥሪ ወደ ቦረና ተመልሶ በይፋ አማፂ ቡድኑን ተቀላቀለ።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በ2001 በተነሳ የውስጥ ሽኩቻ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሲከፋፈል በጀነራል ከማል ገልቹ የሚመራው አንጃ በደቡብ በኩል ቦረና ላይ ካለው OLA ወታደሮች ጋር ተገናኘ። ነገር ግን መንግስት በከፈተው መጠነ ሰፊ ወረራ አካባቢው ላይ የነበረው ሰራዊት ተሸንፎ ኩምሳም ወደ ኡጋንዳ ሸሸ።

የኢትዮጵያ መንግስት ኡጋንዳ ኩምሳን እንድታስረክበው ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቶ በሀገሩ ህግ ተዳኝቶ አንድ አመት ከግማሽ ተፈርዶበት ታሰረ።

የእስር ጊዜውን ከጨረሰ በኃላ ወደ ኤርትራ በመሄድ ከኦነግ አመራሮች ጋር ተገናኘ። በእስር ቆይታው ወቅት የምዕራብ ኦሮሚያ አዛዥ(ኮማንደር) ለገሰ ዎጊ ተገሎ ወታደሮቹም ተበታትነው ስለነበረ ኩምሳ የምዕራቡን ኃይል ለማደራጀት ተልዕኮ ተሰጥቶት ወደ ኢትዮጵያ በድብቅ ተመለሰ።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ኩምሳ ሰራዊቱን በማሰባሰብ ላይ እንደነበረ በ2012 Oromo protest በመቀስቀሱ ብዙ ወጣቶች በመመልመል OLAን ወታደሮች ቁጥር መጨመር አስቻለው። በ2014 የኢሬቻ አሳዛኝ ክስተትን ተከትሎ ቀለም ወለጋ ያሉ በመቶ የሚቆጠሩ ወጣቶች የአካባቢውን ሚሊሻ መሳሪያ በመንጠቅ ቡድኑን ተቀላቀሉ።

እንደ ቀድሞ መንግስት ከሆነ በ2016 በአራት ወለጋ ዞኖች በርካታ ወረዳዎችን OLA በኩምሳ መሪነት ተቆጣጠሮ የገጠር መንደሮችን ያስተዳድር ነበር። የራሱን ሚሊሺያ አቋቁሞ የመንግስት ሚሊሺያዎችን ያስር ነበር። ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ከመጣ በኃላ ኦዴፓ ኃይል ሲቆጣጠር ምዕራብ ወለጋ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም OLA ዞኑን ተቆጣጥሮ ማስተዳደር ጀመረ።

በኦዴፓ የሚመራው መንግስት እና በዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ አስመራ ላይ የሰላም ስምምነት በማድረግ በአዲስ ምዕራፍ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመስረት ተስማምተው ወደ ሀገር ቤት ገቡ። ነገር ግን ከወራት በኃላ በግልፅ እንደታየው ኩምሳ ስምምነቱን እንዳልተቀበለ አስመሰከረ።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

ከአንድ ሰአት በላይ የሆነ ቪዲዮ በሶሻል የሚዲያ የለቀቀው ኩምሳ ዲሪባ ኦዲፒን እንደማያምን እና ትጥቅ ፍቱ ከተባሉ “እምቢ” እንዲሉ ለወታደሮቹ መልእክት አስተላልፏል። ከውጭ በመጡ አመራሮች ትጥቅ ፍቱ የሚባል ትእዛዝ እንደማይቀበሉ አስረግጦ ይናገራል።

በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ሚሊተሪ ሰፊ ዘመቻ በማካሄድ ፣ መከላከያ ሰራዊት ወለጋና ሰሜን ሸዋ ላይ በማስፈር ፣ የOLA ወታደሮች ለመደምሰስ እና ኩምሳ ዲሪባን ለመያዝ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። መንግስትም ሆነ ኦነግ አሻፈረኝ ያለውን አንጃ እስካሁን አልነገሩንም።

Jemallu Hussen2

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *