በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ስም ከቀረጥ ነፃ ከሚገቡት መካከል የብረት ምርት ለህገ ወጥ ስራ በማዋል መንግስትን ከፍተኛ ገንዘብ በማሳጣት ቀዳሚ መሆኑን የጉሙሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኢትዮጵያ በየጊዜው የብረት ምርት ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ከመጣባቸው ሀገራት ትጠቀሳለች፡፡መንግስት ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት በሆቴሎች እና መሰል ዘርፎች ላይ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ብረትን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ መፍቀዱ ይታወቃል፡፡

ይህን የማበረታቻ እድል ግን ሀገሪቱን በከፍተኛ ደረጃ ሲጎዳት መቆየቱን አዲስ የተቋቋመው የጉሙሩክ ኮሚሽን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል፡፡

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

የጉሙሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሙለታ በየነ ከቀረጥ ነፃ ከሚገቡ ምርቶች መካከል መንግስትን ከፍተኛ ገንዘብ እያሳጡ ከሚገኙት መካከል ብረትን ቀዳሚው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ምክትል ኮሚሽነሩ ይህን የምንለው አዲስ ቡድን አቋቁመን በጀመርነው ኦዲት ስራ እየተገኙ ባሉ ውጤቶች አማካኝነት ነው ብለዋል።

በርካታ ድርጅቶች በሆቴል ለመሰማራት ፍቃድ አውጥተው ማበረታቸውን ተጠቅመው ማቋረጣቸውንም ተናግረዋል።

ችግሩን ለመከላከል ለአንድ ህንፃ ምን ያህል የብረት መጠን እንደሚያስፈልገው አለመታወቁ አስቸጋሪ እንዳደረገው ጠቁመዋል፡፡

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ጉሙሩክ ኮሚሽን አሁን ላይ እርምጃ ለመውሰድ ቡድን አቋቁሞ ኦዲት እያካሄደ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሩ አብራርተዋል፡፡

FBC

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *