በመከላከያ ሰራዊቱ የተደረገው ሪፎርም ሰራዊቱ የሚሰጠውን ግዳጅ በአግባቡ እንዲወጣ የሚያደርግ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ተናገሩ። ከሰባት ሺህ በላይ የሰራዊት አባላት ተሰናብተዋል።

የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በዛሬው እለከት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የ6 ወር አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል።

በሪፖርታቸውም ባለፉት ስድስት ወራት መከላከያ ሰራዊቱን የማዘመን ስራ በስፋት መሰራቱን አስታውቀዋል።

በተለይም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከተሰሩት ስራ ውስጥ የመከላከያ ሰራዊት አዋጅ ማሻሻያው አንዱ መሆኑን በመግለጽ፥ በዚህም 20 አንቀፆች ላይ ማሻሻያ መደረጉን ተናግረዋል።

የመከላከያ ሰራዊቱ በቀጣይም ሀገራዊ ተልእኮውን በአግባቡ እንዲወጣ ለማስቻል እና ጠንካራ ተቋሟዊ አደረጃጀት እንዲኖር የማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የባህር ሀይልን በአዲስ መልክ ለማደረጃት ባለፉት ስድስት ወራት በተደረገው አንቅስቃሴ ዙሪያም፥ ከፈረንሳይ እና ከኬንያ ባህር ሀይሎች ልምድ መቀሰሙንም አስታውቀዋል።

Related stories   “የትኅትና ገመድ የመጨረሻዋ ቋጠሮ ብርቱ ክንድ ናት፤ ከተሠነዘረች ሳታደቅቅ አትመለስም”

ሚኒስትሯ አክለምው ከሀምሌ 2010 ዓ.ም ጀምሮ የማእረግ መመልመያ መስፈርትን ለሟሉ የሰራዊት አባላት መንግስት የፈቀደውን ቀጣዩን ማእረግ እንዲለብሱ ተደርጓል ብለዋል።

የአገልግሎት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ፣ ከማእረግ ምልመላ በሳይኮሜትሪክ ፈተና የወደቁ፣ በትምህርት ምክንያት ማደግ የማይችሉ፣ ሁለት ጊዜ ከማዕረድ እድገት የታገዱ በድምሩ 7 ሺህ 17 የሰራዊት አባላት አስፈላጊውን መስፈርት እንዲያሟሉ በማድረግ የማሰናበት ስራ መሰራቱንም አስታውቀዋል።

የጦርነት አደጋን ለመግታት ወይም የሚያጋጥም አደጋን በአጭር ጊዜ እና በአነስተኛ ኪሳራ መጨረስ ዝግጅትን በተመለከተም በተለይም የኢትዮጵያ አየር ክልል በአስተማማኝ ለመጠበቅ እና ተገቢውን የአየር ድጋፍ ለመስጠት ተዋጊ እና የትራንስፖርት አውሮፕላኖች ፍተሻ፣ እንክብካቤ እና ጥገና ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

የአብራሪዎችን አቅም ለማሳደግም ልምምድ ተደርጓል ያሉት ሚኒስትሯ፥ ለብልሽት ተዳርገው የነበሩ ቀላል እና ከባድ የጦር መሳሪያዎች የጥገና ስራ መሰራቱንም ገልፀዋል።

Related stories   ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦችና ተቋማት በጥምቀት በዓል ድሮን መጠቀም እንደማይችሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

ሚኒስትሯ ሪፖርቱን ካቀረቡ በኋላ የተለያዩ ጥያቄዎች እና ሀሳቦች ከምክር ቤቱ አባላት ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የምክር ቤቱ አባላትም የመከላከያ መሻሻያው ምን ያክል አሳታፊ እና ግልፅ ነው፤ የብሄር ብሄረሰቦች ተዋጽኦስ ምን ይመስላል፤ ተቋሙን ለማዘመን የተሰራው ስራስ የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል።

የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድም የመከላከያ ማሻሻያው ህገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ የተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።

ከብሄር ብሄረሰብ ተዋፅኦ ጋር ተያይዞ ለተነሳው ጥያቄም ማሻሻያው ሁሉንም ባሳተፈ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።

ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ፥ የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን እንቅስቃሴ እና ተጋድሎ ወደ ጎን በመተው የሚደረጉ የስም ማጥፋት ተግባራት ሊቆሙ ይገባልሲሉም አክለው ተናግረዋል።

በአፈወርቅ አለሙ FBC

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *