በማዕከላዊ ጎንደር ነዋሪ የሆኑ የዓይን ምሥክሮች እንደተናገሩት ትናንት ምሽት በጎንደር ከተማ አስተዳደር አዘዞ አካባቢ ልዩ ሥሙ ግራር ሰፈር በሚባል ቦታ በእንስሳት ማድለቢያ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 60 የሚደርሱ የደለቡ ከብቶች ተቃጥለዋል፤ በጣት የሚቆጠሩ ከብቶችን ብቻ በሕዝቡ ጥረት ማትረፍ ተችሏል፡፡

የዓይን ምሥክሮቹ እሳቱን ለመቆጣጠር የአካባቢው ነዋሪና የጎንደር ከተማ አስተዳደር ጥረት ቢያደረጉም መቆጣጠር የተቻለው በዳግማዊ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪና ሠራተኞች እገዛ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡
የዓይን ምሥክሮቹ አደጋውን ማን እንዳደረሰው በግልጽ ባይታወቅም ከሰሞኑ የአካባቢው ግጭት ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ግን እርግጠኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ሌሊቱን በአዘዞ አካባቢ ተኩስ እንደነበር ያስረዱት የዓይን ምሥክሮቹ ‹‹ተኩሱ ግን እሳቱን ለመቆጣጠር እንዲቻል ጥሪ ለማስተላለፍ ያለመ ነበር›› ነው ያሉት፡፡ በእሳት አደጋው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ገልጸው በብድር ገንዘብ ተደራጅተው በከብት ማድለብ የተሠማሩ ወጣቶችን ለፖለቲካ ጥቅም መጉዳት ተገቢ እንዳልነበር ተናግረዋል፤ መንግሥት በአፋጣኝ ወንጀለኞችን ለሕግ እንዲያቀርብም አሳስበዋል፡፡
በጎንደር ከተማ አስተዳደር የ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ባለሙያ ምክትል ሳጅን ሙሐመድ ሰይድ ደግሞ ምሽት 5፡00 አካባቢ እሳት ቃጠሎው መነሳቱን አስታውሰው በማድለቢያና እንስሳት እርባታ ድርጅት ላይ በደረሰ ቃጠሎ 51 የቁም ከብቶች መሞታቸውን እንዳረጋገጡ ተናግረዋል፡፡ ምን ያክል ከብቶች እንደተረፉ ግን ማረጋገጫ እንደሌላቸው ነው መርማሪው ለአብመድ የተናገሩት፡፡

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

ቃጠሎው በደረሰበት አካባቢ የእንስሳት መኖ መኖሩ ለቃጠሎው መባባስ አስተዋጽኦ ማድረጉን የገለጹት ምክትል ሳጅን ሙሐመድ ‹‹የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ የምርመራ ሂደቱ እንደቀጠለ ነው፤ ወደፊት ውጤት ላይ ስንደርስ ለሕዝብ እናሳውቃለን›› ብለዋል፡፡ በአካባቢው ለእሳት መነሳት ምክንያት የሚሆን ተፈጥሯዊ ምክንያት እንዳልነበረ ግን ባለሙያው አስታውቀዋል፡፡
ድርጊቱን የፈጸሙ አካላትን በተመለከተ መረጃ መስጠት የሚፈልግ ሁሉ ለፖሊስ ጣቢያው ጥቆማ እንዲሰጥም አሳስበዋል፡፡

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ዘጋቢ፡- አብርሃም በዕውቀት – ባሕር ዳር፡ የካቲት 01/2011ዓ.ም (አብመድ)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *