የትግራይ ህዝብ የጥቃት ሰለባ የሆነው በራሱ ክልሉ በሚመራ ድርጅት ነው ። ህዝቡ የሐሳብ ነፃነት ተከልክለዋል ፣ ጥርናፈ በዝቶበታል ፣ በድህነት እንዲኖርም ተደርጓል ። There is  and has been sort of motif systemic political sickness within the political party that administers Tigrai Regional State . ለህግ ልዕልና ተገዢ ያልሆነ  ድርጅት አገራዊ ሆነ ክልላዊ የተረጋጋ ሰላምና የኢኮኖሚ እድገት ሊያመጣ አይችልም ።  በትግራይ ውስጥ ድርጅታዊ አፈና በሰውር ተጠናክሮ ይቀጥላል ። ይህ የማይቀር እውነታ ነው ። ጉዳዩ አንድ በሬ ሰቦ አንድ ድርጅት አሰቦ የሚመጣ ለውጥ ለእኔ ግልፅ አይደለም ። ከታርጋ ለጣፊ ድርጅት የሚገኘው አገልግሎት እርባና የለውም ። አይጋ ፎረም

ልኡል ገብረመድህን (ከአሜሪካ )

ቀን ፣  ጥር 26 /2011 ።

     በእኔ እይታና አሰተሳሰብ ትግራይ የስልጣኔ መሠረት እንደሆነ ይሰማኛል ። ትግራይ ሰልም የትግራይ ህዝብ ማለቴ ነው ። የትግራይ ህዝብ የአስተሳሰብ ደረጃ የሚመጥን የአስተዳደር ተቋምያሰፈልጋል ። በሳይንስ ጥበብና ህዝብ አሰተዳደር መልካም ውጤት የነበረው ህዝብ ያን ሰብዕና የሚያስቀጥል በመርህ ላይ የቆመ አሰተዳደር ያለመኖሩ ከማሳዘንም ያለፈ ነው ።

… በትግራይ ውስጥ ድርጅታዊ አፈና በሰውር ተጠናክሮ ይቀጥላል ። ይህ የማይቀር እውነታ ነው …

    የትግራይ ህዝብ ለኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት  ነው ። የኪነጥበብ  ፣ ሰነ ህንፃ ፣ ሰነ መንግስት ፣ ሰነ ህግ ፣ እንዲሁም የኢኮኖሚ ማዕከል ሆኖ ዘመናት የተሻገረ ህዝብ ቁልቁል የሄደበት አንዱና ዋናው አስረጅ የአስተዳደር ተቋም ብልሹነት ወይም ተቋም ያለመኖር ብሎ መደምደም ይቻላል ። የአክሱም መንግሰታዊ ሰልጣኔ እንደ ራእይ ካልተጠቀምንበት ፣ ሲቀጥልም ካልተማርንበት ወድቀት መጋበዝ እንደሆነ ይሰማኛል ። ትግራይ የዲሞክራሲ ተቋም ተምሳሌት መሆን ነበረባት ። እድሉም ነበራት። ትግራይ ህዝብ ሳይሆን መሪ አጥታ ምጥ ላይ ቆይታለች = አሁንም ምጡ እንዳለ ነው ። የትግራይ ህዝብ የሚመጥን መሪ ወይም የፖለቲካ ተቋም የለም ። የተስተካከለና በጭብጥ የተማከለ ታሪክ ያለው ህዝብ በመንግሥት አሰተዳደር እጦት ሲቸገር ማየት ይከብዳል ።

   በትግራይ ክልል ውስጥ የአስተዳደር ሰልጣን ላይ ያለ የፖለቲካ ድርጅት ለትግራይ ህዝብ ፈፅሞ አይበጅም ። መነሻ ሆነ መድረሻ ምክንያት አንድና ያው አንድ ነው ። ይህውም  ትግራይ እያስተዳደረ ያለ የፖለቲካ ድርጀት በዝምድና ሐረግ የተተበተበ ከመሆኑም ባሻገር ድርጅታዊ ባህሪው ደግሞ ፀረ ዲሞክራሲ ነው ።  የመጀመሪያ ተግባሩም ነፃ ሃሳብን መቀንጠሰ ላይ ያተኮረ ሲሆን በሌላ ጎን ደግሞ የታርጋ ልጣፋ ሥራ ይሰራል ። በዚህ ሁኔታ በርካታ የትግራይ ሙህራን ሰለባ ሆነዋል ። በርካታ የፖለቲካ ሙህራን ተሸመድምደዋል። የትግራይ ሙህራን አገራዊ ሆነ ክልላዊ ሙህራዊ አሰተዋጽኦ ሳያደርጉ ቆይተዋል።

   የትግራይ ህዝብ የጥቃት ሰለባ የሆነው በራሱ ክልሉ በሚመራ ድርጅት ነው ። ህዝቡ የሐሳብ ነፃነት ተከልክለዋል ፣ ጥርናፈ በዝቶበታል ፣ በድህነት እንዲኖርም ተደርጓል ። There is  and has been sort of motif systemic political sickness within the political party that administers Tigrai Regional State . ለህግ ልዕልና ተገዢ ያልሆነ  ድርጅት አገራዊ ሆነ ክልላዊ የተረጋጋ ሰላምና የኢኮኖሚ እድገት ሊያመጣ አይችልም ።  በትግራይ ውስጥ ድርጅታዊ አፈና በሰውር ተጠናክሮ ይቀጥላል ። ይህ የማይቀር እውነታ ነው ። ጉዳዩ አንድ በሬ ሰቦ አንድ ድርጅት አሰቦ የሚመጣ ለውጥ ለእኔ ግልፅ አይደለም ። ከታርጋ ለጣፊ ድርጅት የሚገኘው አገልግሎት እርባና የለውም ።

    በትግራይ ክልል ያልተሸራረፈ የዲሞክራሲና የፍትህ ተቋም ሳይውል ሳያድር ተግባራዊ ማድረግ ግዴታ ነው ። ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ የለም ። እስከአሁን በመዘግየቱ በክልሉ ለተፈፀሙት መንግሰታዊ ጉድለቶች መሪ ድርጅቱ ከተጠያቂነት ነፃ አይሆንም ። ባልፈፀሙት ወንጀል ታረጋ ተለጥፎባቸው በትግራይ ክልል እስርቤቶች ታሰሮ ያሉ የፖለቲካ ድርጅት አባሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈታት አለባቸው ። ትግራይ እያስተዳደረ ያለ መሪ  የፖለቲካ ድርጅት የፖለቲካ ድርጀት አባሎች ለማሰር ተቋማዊ ብቃት ፈፅሞ የለውም ። ማን አሳሪ ማን ታሳሪ ይሆናል ። መታሰርም ካለበት ራሱ መሪ ድርጀቱ መሆን አለበት ። የአረናም ሆኑ የሌላ ፖለቲካ ድርጅት እስረኞች ይፈቱ ! ። በትግራይ ዲሞክራሲና ፍትህ ይንገሥ ፣ አፈና ይወገድ ።

    ትግራይ የውጭ ሆነ የውስጥ ችግሮች ያሉባት ክልል ሆናለች ። ከኤርትራ ጋር ያለው ግኑኝነት ግልጽነት ይጎድለዋል ። የኤረትራ ህዝብ ከማንም በላይ ለትግራይ ህዝብ ይቀርባል ብቻ ሳይሆን ደማዊ ትስስር ያለው ህዝብ ነው ። ህዝቦች ላይ ችግር አልነበረም ፣ የለም ፣ አይኖርም ። የፖለቲካ ጎረምሶች እልህና መካረር የፈጠረው ችግር ለተራው ህዝብ ተረፈ ። በችኮላና ሰሜት የተፈፀመ ስህተት ቤተሰቦች አለያይተዋል ፣ አገር ጎድተዋል ፣ ሰላም ደፍርሷል ። የተፈፀመ ስህተት ለማስተካከል ጊዜ መውሰዱ አይቀርም ። ምክንያትም አሁንም እየተደራደሩ ያሉት ችግር ፈጣሪ  የነበሩ በመሆናቸው ሰላም በአጭር ጊዜ ተግባራዊ አይሆንም ። ችግር ፈጣሪዎች አንዳቸው ወይም ሁለቱም ማሰወገድ የግድ ይላል ። በትግራይና ኤርትራ ህዝብ ቀናኢ ሰላምና መልካም ግኑኝነት እንዲሰፍን የኤርትራ መሪ ሆነ ትግራይ የሚመራ የፖለቲካ ድርጅት መወገድ ጊዜ የማይሰጥ አንገብጋቢ ጉዳዩ ነው ። ሌላው አማራጭ ደግሞ ተቀራርቦ መነጋገርና ፍትሀዊ ይቅርታ መፈጸም ይሆናል ። ከዚህ ውጭ ተአምር የለም ።

     ኢትዮጵያ ያለ ትግራይ ታሪክ የላትም ። በመሆኑም ትግራይ በኢትዮጵያ ውስጥ ያላት ተሰሚነት ክልሉ በሚመራ የፖለቲካ ድርጀት ምከንያት አሁን አሁን እምብዛም አይደለም ። ትግራይ በኢትዮጵያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ክልል ከመሆኗም በላይ የአገር ዘብ ጠባቂ ክልል ነው ። በኢትዮጵያ ታሪክ ብዙም ጊዜ ውጫዊ ሆኑ ውስጣዊ ችግሮች ከሰሜኑ ጫፍ የሚመነጩ በመሆናቸው ትግራይ የመጀመሪያ ተጠቃሚ የመሆን እድሉ ስፋትና ጥልቅ አለው ። በመሆኑም ያለ ትግራይ በኢትዮጵያ የተረጋጋ ሰላም ሊኖር የሚችል አይሆንም ። ውስጣዊ ሰላም ደግሞ የሁሉም መነሻ ምከንያት ነው ። አሁን በኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስትና በትግራይ ክልላዊ መንግስት መልካም ግኑኝነት የለም ።ለህዝብ አይነገር እንጂ ችግሮች አሉ ። የትግራይ ክልላዊ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የማንነትና የአስተዳደር ጉዳዮች ኮምሽን አልተቀበለውም ። ይህ ለማድረግ ክልላዊ ሰልጣን እንዳለው የሚያሳይ የህግ ማዕቀፍ የተዛባ ነው ። የሆነ ሆኖ ይህ የክልል ምክር ቤት ውሳኔ ችግር መውለዱ አይቀርም ። በሌላ ሁኔታ ደግሞ የትግራይ ክልል በሂደት የፀጥታና የኢኮኖሚ ችግሮች ያጋጡሙታል። የክልል በጀት እጥረት / Regional Budget Constrain / ያጋጥመዋል ። ሰራ አጥነትና ወንጀል ይስፋፋል ። ችግሮች ለመፍታት የሚችል የበቃ አመራርና ድርጅት ባለመኖሩ የችግሮች ጥልቀት ከፍተኛ ይሆናል ።

   በትግራይ ክልል በሒደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች ለመፍታት የህዝብ የአስተሳሰብና እይታ ለውጥ / Paradigm shift / በእጅጉ አሰፈላጊ ነው ። ህዝብ በርጋታ ቀጣይ ጥቅሙንና ጉዳቱን መገንዘብ ይኖርበታል ። የክልሉ ፖለቲካ ድርጅት የተሳሳተ አካሔድ ማስቆምና እንዲስተካከል የማድረግ የፖለቲካ ድርጀቱ ሳይሆን የህዝብ ሐላፊነት ነው ። በተለይ የትግራይ ወጣቶች ሙሁራን የተዛቡ የክልሉ ማህበረ አኮኖሚ የመግራት ሀላፊነት አለባቸው ። ድርጅታዊ አፈና እንዲቆም መታገል አለባቸው ። የመናገርና የመደራጀት ነፃነት ያለምንም የክልሉ ፖለቲካዊ ድርጅት ተፅዕኖና አፈና መንቀሳቀስ መቻል ይኖርባቸዋል ። ጠንከር ያለ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግና የትግራይ ህዝብ ከውጭ ሆነ ውስጥ ጥቃት መከላከል የትግራይ ወጣቶች ግዴታ ነው ።

   በትግራይ ክልል ለሚደረጉ የነፃነት አፈናዎች መሪ የፖለቲካ ድርጅቱ ተጠያቂ ይሆናል ። በትግራይ ክልል አንድም ሰው ቢሆን በፖለቲካ አመለከቱና እይታው መታሰርና መቀጣት ይቁም ። የበሰለ የፖለቲካ ወይይት / Political dialogue / መጠናከር ነበረበት ። አሁንም መፈጸም አለበት ። በጠላትነት መተያየት ይቁም ። በውይይትና ደርድረው እንመን። ዛሬ የሚወሰዱ የአፈና እርምጃዎች ለነገ አይበጅም ። ይቅር መባባልና መደማመጥ ማደግ አለበት ። መጠቃቃትና መጠፋፋት ይቁም ።  ለዚህም ያለወንጀላቸው የታሰሩ የትግራይ ፖለቲከኞች ያለምንም ሁኔታ ከእሰር ይፈቱ።

  በትግራይ የፍትህ ሰርአት ይስተካከል ። ያለ ሞያዊ ብቃት የፍትህ ተቋማት ማስተዳደር ፈፅሞ አይታሰብም ። የፍርድ ጉዳይ በፖለቲካ ታማኝነት አይለካም ። የፖለቲካ ሰው ህዝብ ማስተባበር እንጂ የፍትህ ተቋም ማስተዳደር ፖለቲካዊ ካልሆነ በቀር ሞያዊ ሊሆን ፈፅሞ አይችልም ። የትግራይ ህዝብ ከፖለቲካ የፀዳ ገለልተኛ የፍትህ ተቋም ያስፈልገዋል ። በትግራይ ክልል የፍትህ መዛባት ከሌሎች ክልሎች የከፋ ነው ።  የፍትህ ስርአቱ በዝምድናና ትውውቅ አልያም በፖለቲካ ጥገኝነት የሚፈፀም በመሆኑ በክልሉ ፍትህ አለ ለማለት አያስደፍርም ። የሥራ እድልም ቢሆን የፖለቲካ ጥገኝነት ያላቸው ሰዎች የቅድሚያ ቅድሚያ ያገኛሉ ። ያውም ሥራ ከተገኘ ። ይህ አግባብነት የለውም ። ብዙ የተማሩ የትግራይ ወጣቶች ሥራ አጦች ሆነዋል ። አንዱ ምክንያት ደግሞ የክልሉ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ ከአምስት በመቶ (5 %) አይበልጥም ። ክልሉ ሰባ ከመቶ (70 % ) በፌደራል በጀት የሚተዳደር ክልል ነው ።

   ትግራይ በኢንዱስትሪ የበለፀገች ክልል ማድረግ ጊዜ የሚሰጥ ጉዳይ አይደለም ። ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ የሰው ክህሎትና የገንዘብ አቅም ይጠይቃል ። በእኔ እይታ የሰው ክህሎት አለ። የሌለው የገንዘብ አቅም ብቻ ነው ። ክልሉ የሚያስተዳድር የፖለቲካ ድርጅት የናጠጠ እምቅ የገንዘብ አቅም አለው ። ትግራይ ለማበልፀግ የድርጅቱ ገንዘብ ከሚፈለገው በላይ ነው ። የሚያስፈልገው ቀና አመለካከትና እሳቤ ብቻ ነው ። የትግራይ ክልል መሪ ድርጅት ያለው መዋዕለ ንዋይ ትግራይ ለማበልፀግ ከበቂ በላይ ነው ። ይህ ሳያደርግ ቢቀር ግን ድርጅቱ በሒደት አደጋ ላይ መውደቁ የማይቀር ጉዳይ ነው ።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *