በዚህ ርዕሰ ጉዳይ በምክንያት ዝምታን መርጬ ቆይቻለሁ።  አሁንም በምክንያት አስተያየት ሰጣለሁ። ሲጀመር አጨቃጫቂ ጉዳይ ሲነሳ ጉዳዩ እልባት የሚሰጠው በሁለት የሚፃረሩ ወገኖች ፍላጎት ላይ ተመስርቶ ሳይሆን
አመክንዮን መሠረት አድርጎ መሆን አለበት።

መጀመሪያ አዲስአበባ የእነማን እንዳልሆነች ግልፅ ላድርግ። ምክንያቱም የማን እንዳልሆነች ማወቁ የማናት?! ወደሚለው መንገድ ይወስደናልና። አዲስአበባ ከ1467 ጀምሮ የራሱ አባገዳና የብቻው አስተዳደር የነበረው የቦረና ኦሮሞ አይደለችም። ከተመሳሳይ ጊዜ ጀምሮ ተመሳሳይ አስተዳደር መሥርቶ ከሌላው ጋር እየተፋቀረም እየተወጋጋም የኖረው የጉጂ ኦሮሞም አይደለቺም።

ከዚሁ ጎንለጎን የየራሳቸው መንግሥት የነበራቸው የአርሲ የጂማ ጎማ ጉማ ሊሙኢናርያ ጌራ ሌቃ-ቄለም ሌቃ ነቀምቴና መሰል የኦሮሞና የደቡብ መንግሥታትም አይደለቺም። የጎጃም የጎንደርና የወሎም አይደለቺም። የሲዳማ የወላይታና የጌዴኦም አይደለቺም። ወደኋላ ከሄድን ሌላ የማያባራ የታሪክ መናከስ እንፈጥራለን እንጂ ቀረብ ወዳለው የታሪክ ዘመን ብንሄድ መሳለመሳ ይኖሩ የነበሩ የሸዋ ኦሮሞና የሸዋ አማራ ነበረች።
።።።።።። ።።።።።። ።።።።።።።። ።።።።።።።።
አሁን የማናት?!
የዓለም አራት ታዋቂ ዲፕሎማቲክ መናኸሪያ ከተሞች ውስጥ የተካተተች (ኒውዮርክ ጄኔቫ አዲስአበባ ቪዬና) የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የኦሮሚያ የፖለቲካ እምብርት እና በዋናነት የመላው አዲስ አበባውያን ናት።
።።።።።።።።።።።። ።።።።።። ።።።።።።።። ።።።።።።
ያልገባኝ ጭቅጭቅ
“የኛ ናት፤ የኛ ናት” ምን ለማድረግ ምን ለመሆን ምን አጀንዳ ተይዞ ነው?! የእናንተ ስለሆነ ምን ይሁን?! ምን ይጠበስ?! አዲስአበባ ትምህርት በአማርኛና ለሚፈልጉ በኦሮምኛ ይሰጣል። ለስራ ሁለቱንም ቋንቋዎች ጎንለጎን መጠቀም ይቻላል። የትኛውም ጉዳይ በውይይት ሰከን ተብሎ ይፈታል። ወለጋና ጎንደር ጫፍ ቁጭ ብለህ በኪይቦርድ ብትደንስ መቀሌ ሆነህ እሳቱ ላይ ቤንዚን ብታርከፈክፍ አልሰማህም። ነጮች ጆሀንስበርግ ከተማን ስለከበቡ ከተማዋ የነጮች ናት ማለት አይደለም። አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ መላው ዓለም መፍትሔ ያገኘው ዛሬ ባለበት ሁኔታ ተስማምቶ ነው።
።።።።። ።።።።።። ።።።።።።። ።።።።።
አዲስአበባ ዛሬ ያለው ሰው ከየት መጣ?! ማነው?! 99% በርግጠኝነት መምህር ሀኪም ነጋዴ ፖሊስ ግብርና ጤና ፓይለት ባንክ ኢንሹራንስ ጉምሩክ ከተማልማት መከላከያ ፌደራል ፖሊስ የፓርላማ ተወካይ ሰርቶበላ ላብአደር ዘበኛ ወዘተርፈ ሆኖ በዘመናት መስተጋብር በትልቋ ማቅለጫ ገንዳ አዲስአበባ የተዋሀደ እንጂ በቀጥታ ራሱ ገበሬውን አፈናቅሎ የሠፈረ አይደለም። ቤቱም ንብረቱም ላቡን ጠብ አድርጎ፤ ገንዘቡን ከስክሶ የሰራው ንብረት ነው።
“ሰውን አልፈለጋችሁም መሬቱን ነው” የምትሉ ጩኸቴን ቀሙኝ ነው እንጂ አንተ ነህ ዛሬ ያለውን 80% የሆነ 80 ብሔር ብሔረሰብ ንቀህ መሬቱን እየፈለግህ ምትጮህ።
።።።። ።።።።። ።።።።።። ።።።።።። ።።።።
ሲጠቃለል አዲስአበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ናት። ከጠበበ የነዋሪዎቿ ናት። ከአርሲና ከጎጃም መጥተህ “የኛ ናት፤ የኛ ናት” የምትለው ነዋሪዎቿን ቀቅለህ ልትበላቸው ነው?!
።።።። ።።።።።።። ።።።።።።። ።።።።።።።
የተፈናቀሉ የኦሮሞ ገበሬዎች መብት ግን ተወደደም ተጠላ በጥናት መመለስ አለበት።

#ማሳሰቢያ
በምክንያት መሟገት ማትችል ድንጋይ ራስ ሁሉ በአመክንዮ ሀሳቤን 1,2,3… ብለህ ሳትቆጥር  ሰፊ አፍህን ከፍተህ እጨማለቃለሁ ብትል ውርድ ከራሴ የማከብረው እንደ ሰው አስቦ በምክንያት የሚወያየውን ብቻ ነው።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *