ከዛሬዎቹ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሳይንስ ካልተማሩት ፖለቲከኞና የፌስቡክ ተሟጋች ነኝ ብለው ራሳቸውን ካስመረቁት ምሁራን ውስጥ አንድ እንኳን የወደፊቱን የሚያስብና ለነበሩብንና: ላሉብን እንዲሁም ወደፊት ሊመጡ ይችላሉ ተብለው ለሚታሰቡ ችግሮቻችን የመፍትሄ ሀሳብ በማስቀመጥ የሚሞግትና የሚንቀሳቀስ ”ሰው” ይጥፋ!
የ1900, 1800, 1700, 1600, 1500, 1400, 1300ዎቹ እያሉ በ100 ብዜት ወደ ኋልዮሽ እየገሰገሱ የሞቱትንና የገደሉትን የእኛ ነበሩ የእነርሱ በማለት ዘቅጠው ልያዘቅጡን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይተጋሉ:: የሚገርመው ደግሞ ይህንን ስራዬ ብለው የተያያዙት “የተማሩ” ተብለው የሚጠሩ መፃፍና ማንበብ የሚችሉ ድልዱሞች መሆናቸው በሽታቸውን ለማከም አስቸጋሪ ያደርገዋል:: ይህንን አስተሳሰባቸውን እና አስተምሮቶቻቸውን ያለምንም ማላመጥ የፃፈው ሰውዬ “እንትና” በመሆኑ ብቻ like ወይም share በማድረግ ከተባበርናቸው ጅልነታችንን ተጠቅመው እንደካንሰር እስከ አጥንቶቻችን በመዝለቅ መመለስ ወደ ማይቻል የእርስ በርስ ግጭትና ፍጅት ማዳረጋችቸውን ለማብሰር ነብይ መሆን አይጠበቅኝም::
ትላንት ራሱን እንኳን መልሶ አምጥቶ “ዛሬ” ወይም “ነገ” መሆን ላይችል የራሱን መጥፎም ይሁን መልካም ሰርቶ ላይመለስ አልፏል:: ትላንትን ተሻግሮ ዛሬ የደረሰውን መልካም ነገር በማስቀጠልና በዛሬ ላይ ደግሞ ሌላ አዲስ መልካም በመስራት እንዲሁም ለነገ መልካም በማቀድና በማድረግ ልናድግ እንችላለን ብዬ አስባለሁ:: ይህንን ፅሁፌን እንኳን ስታነቡ (ካነባባችሁት) በሀሳቡ ላይ ብቻ ትኩረት ላለማድረግ እዕምሯችሁ ትንሽም ብሆን ይደራደር ይሆናል ብዬ አስባለህ:: በግሌ ያ ማለት መስተካከል ያለበት ነገር እንዳለ አመላካች እንጅ በራሱ ችግር ነው ብዬ አልወስድም::
እስቲ አንድ ሁለት ምሳሌ ላካፍላችሁ! በትምህርት ምክንያት በእንግድነት የሚኖርበት አገር ትልቁ አገራዊ የእኮኖሚው ዋልታ ነዳጅ ነው:: የዚህን የተፈጥሮ ሀብት መንግስት መጠቀም የሚችለው 4% ብቻ ሲሆን 96%ቱ ለቀጣይ ትውልድ የኢኮኖሚ ዋስትና ሁኖ ይቀመጣል:: በአሁን ሰዓት ያለው ሃብታቸው አገራቸው ከዛሬ ጀምሮ ምንም ገቢ ባይኖራትና ሁሉም ሰው ምንም ሳይሰራ የተጠራቀመውን ብቻ እየተጠቀመ መኖር ብጀምር እንኳ ተብሎ ብታሰብ እስከ አራት ትውልድ ድረስ ማኖር የሚችል አቅም አለቸው:: የአንድ ትውልድ እድሜያቸው የእኛን አገር የእድሜ ጣሪያ ሁለት እጥፍ ነው(ለስሌት ጥቆማ):: ከእነዚህ ሰዎች ፌስቡክ:ቫይበር: ቴሌግራም: ዋትስአፕ: ኢሞ: ሜሴንጀር የማያዉቁ ብዙ ናቸው ቢያውቁትም ለእውቀት ብቻ እንጂ ለመጠቀም ጊዜ የላቸውም:: እኛ ጋ ስንመጣ ቀኑ ቶሎ አልመሽልን ብሎ በየካፌው እየዞርን ስናፏሽክ የምንውል ስንቶቻችን ነን?
ወደሀሳቤ ስመለስ ጥንት የነበሩ አባቶቻችን በዚያን ጊዜ በነበረው ሊህቃተ ህሊውና የሰሩትን ስህተት መቁጠር ወይም የዚያን ያክል ወደ ኋላ ሄዶ ተመሳሳይ ስህተት ለመስራት መሞከርን ተፈጥሮዊ እዕምሮ ይፈቅዳል ብዬ አላስብም:: በ13ኛው ክፍለዘመን በነበረው የአስተሳሰብ ደረጃ የተሰሩትን ስህተቶች በ21ኛው ክፍለዘመን የአስተሳሰብ ደረጃ ለፍርድ ማቅረብ እራስን ወደ 13ኛው ዘመን የአስተሳሰብ ደረጃ እንደመውሰድ ነው::
በሽቦ ስልክ ዘመን የተሰረውን ስህተት በስማርት ፎን ለመስራት መሞከር: ቁምጣ ለብሰው ያደረጉት በቦላሌ ለማድረግ መሞከር ኧረ አያምርም(😀አይነፋም)::
ወደፊትን በማሰብ ወደፊት ለመሄድ እንሞክር!

ለአገሬና ህዝቧ ሰላምን ተመኘሁ::

ተኬሳ ኤርጋ FB

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *