ዛሬ የካቲት 5/2011 ዓ.ም በአዋሽ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ 80 ኪሎ ግራም የሚመዝን የብር ጌጣጌጥ ገምታዊ ዋጋቸው 3 953200 /ሶስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ሶስት ሺ ሁለት መቶ/ ብር እንዲሁም ግምታዊ ዋጋቸው 661 ሺ የሆኑ የተለያዩ አልባሳት እና መለዋዎጫዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በተመሳሳይ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ግምታዊ ዋጋው 166,700 ብር የሆነ የተለያዩ የኤልክትሮኒክስ ዕቃዎች የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ከሌሊቱ 9፡00 ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስታዎቁ ተዘግቧል።

በጥቅሉ በዛሬው እለት ብቻ 4580900ብር/አራት ሚሊየን አምስት መቶ ሰማኒያ ሺ ዘጠኝ መቶ ብር የሚገመት ኮንትሮ ባንድ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ኮንትሮባንድን የመከላከል ስራ ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስትሯ ወይዘሮ አዳነች ገልጸው በመከላከል ስራ ላይ ለተሳተፉ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ምንጭ የገቢዎች ሚኒስቴር – (ኢፕድ)

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *