አሃዳዊ ሥርዓት በኢትዮጵያ ሲስፋፋና በሕዝቦቿ ላይ ሲጫን፣ አስተዳደራዊ ችግሮችን ለመፍታት ተብሎ፣ በተራ አስተደደራዊ እሳቤ ላይ ተሞርክዞ የተወሰነ ውሳኔ ሳይሆን፣ የአገሪቱን ብሔሮች ማንነት በመጨፍለቅ፣ መሬትን በመንጠቅ፣ እና የሕዝቦችን ባህል እና ሰብዓዊ ክብርን (human dignity) በመስበር፣ በአንድ ብሔር የበላይነት ላይ የተመሠረተ አገራዊ ማንነትና አንድነት ለመፍጠር ታስቦ ነው።

በመሆኑም፣ በኢትዮጵያ፣ አሃዳዊነት አስተዳደራዊ ቅልጥፍናን ለማምጣት የተዘረጋ ስልት ሳይሆን፣ ለአገረ-መንግሥቱ ‘ሌሎች’ (other) የሆኑ ብሔሮችን ለማጥፋት የተቀረፀ ፖለቲካዊ መሳሪያ (technology of governance) ነው።

የኢትዮጵያ ፌደራሊዝምም በዋናነት የተፈለገው፣ ለኢትዮጵያ መልካም የአስተዳደር አወቃቀር ለመፍጠር ሳይሆን፣ በአሃዳዊነት ለጭፍለቃ የተዳረጉ ሕዝቦችን መብት፣ ሰብአዊ ማንነት (agency)፣ ራስ-ገዝነት (autonomy)፣ እና የሉዓላዊነት ሥልጣን (sovereign authority) ለማስመለስ፣ ለመግለፅ፣ ለመንከባከብና ለመጠበቅ ተብሎ ነው። በአሃዳዊው ሥርዓት ጭፍለቃና አግላይነት እንዲጠፉ የተፈለጉትን ብሔሮችን ለመታደግና ለማኖር እንደብቸኛ አማራጭ የተወሰደ ስልት ነው።

አሃዳዊነት፣ የተስፋፊ-ጠቅላይ (imperial) ሥርዓትን በመንተራስ፣ የአንድ ቡድን የበላይነትን ለማጀገን ከመሻት የመነጨ ዘዴ ነው። ፌደራሊዝም በእንፃሩ፣ የተስፋፊ-ጠቅላይ አገዛዝን በመናድ የሕዝቦችን እኩልነትና ነፃነት ለመመለስ ከመሻት የመነጨ ዘዴ ነው።

አሃዳዊነት ግቡ፣ የአንድ ቡድንን የበላይነት (domination and dominance) ማፅናት ነው። ፌደራሊዝም ግቡ፣ የቡድኖችን እኩልነትና ነፃነት (equality and liberty) ማረጋገጥ ነው።

አሃዳዊነት በኢትዮጵያ ሲጠየቅ፣ ጥያቄው፣ የአንድ ቡድን የሥልጣን የበላይነት ጥያቄ (the question of power) ነው የሚሆነው። ፌደራሊዝም በኢትዮጵያ ሲጠየቅ፣ ጥያቄው፣ የብዙ ብሔሮች የፍትህጥያቄ (the question of justice) ነው የሚሆነው።

የአሃዳዊነት ጥያቄ የተቀላጠፈ ፍትሃዊ አስተዳደር ለሕዝቦች በማምጣት ግብ ላይ ያጠውጠነጠነ አይደለም። የፌደራሊዝም ጥያቄም፣ ‘የኢትዮጵያ መንግሥት እንዴት ቢደራጅ በግዛቱ ውስጥ መልካም አስተዳደር ለመፍጠር ይቻላል?’ ለሚል ጥያቄ መልስ ለመስጠት አይደለም።

የአሃዳዊነት የመጨረሻ ግብ፣ ብሔሮችን ለማጥፋት፣ ከፖለቲካ ማህበረሰቡ አባልነት ለማግለል፣ ወይም ከአገራዊው የፖለቲካ ምናብ (political imagination) ውጭ በማድረግ እይታንና እውቅናን (visibility and recognition) በመንሳት፣ እንዳይታዩ (invisible እንዲሆኑ) ማድረግ ነበረ፣ ነውም።

የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም በአንፃሩ፣ የመጨረሻ ግቡ፣ ከፖለቲካ ማህበረሰቡ ተገልለው፣ ከአገራዊው የፖለቲካ ምናብ (political imagination) ውጭ ተደርገው፣ እይታንና እውቅናን ተነፍገው፣ እንዳይታዩ (invisible) የተደረጉትን ሕዝቦች ወደ ፖለቲካ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ በማድረግ፣ ወደ ማህበረሰቡ የፖለቲካ ምናብ ማዕከል እንዲመጡ በማድረግ፣ እና እኩል እውቅና በመስጠት፣ ከአለመታየት ወደ መታየት (from invisibility to visibility) ማምጣት ነው።

ይሄም የብሔሮችን agency, autonomy, እና authority በማጎናፀፍ ብቻ ይፈፀማል። የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ለዚህ ነው የብሔሮች ሕጋዊ ስብዕና (legal personality)፣ ራስ-ገዝነት ወይም የራስን እድል በራስ መወሰን (autonomy/self-determination)፣ እና የሉዓላዊነት ሥልጣን (sovereignty) ላይ የሚያተኩረው።

ለዚህም ነው የኢትዮጵያ ፌደሬሽን፣ ሊከፋፈሉ ከሚችሉ አሃዶች የተፈጠረ፣ እራሱም ሊከፋፈል የሚችል ህብረት (a destructible union composed of further destructible units) ነው የምንለው። ስለ አሃዶቹ ተከፋፋይነት አንቀጽ 47(3)ን፣ ስለ ህብረቱ ተከፋፋይነት ደግሞ አንቀጽ 39ን ማየት ብቻ ይበቃል።

በመሆኑም፣ ልክ የአሃዳዊ ሥርዓት አቀንቃኞች (ለሥልጣንና ለበላይነት ሳይሆን) ለሕዝቦች መልካም አስተዳደር በመሻት የተነሳሱ ይመስል፣ ወይም ‘ሌሎቹ’ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ የኢትዮጵያን አስተዳደር መልካም ለማድረግ ሲሉ ፌደራሊዝምን የናፈቁ ይመስል፣ ዝም ብሎ በዘፈቀደ ብድግ ብሎ ክልሎችን ‘አስተዳደራዊ ምቹነትን እንዲፈጥር ብዙ ትንንሽ ክፍለ-ሀገራት እናድርግ!’ ብሎ መከራከር፣ አገሩን፣ መሠረታዊ የፖለቲካ ጥያቄዎቹንና፣ ታሪካዊ ዳራውን ፈፅሞ አለመረዳት፣ ወይም እያወቁ ከፍትህና ከእኩልነት ጥያቄ ይልቅ፣ ለሥልጣንና ለአንድ ቡድን የበላይነት መከራከር ነው።

#Federalism_lives!!!!

#To_the_imperfect_destructible_union_ofdestructible_units!!!!

By Tsegaye Regassa Ararssa

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *