ሰሞኑንን መንግስት የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች፣ የተለያዩ አገር የብር ኖቶችና ሃሰተኛ ገንዘብ መያዙን ይፋ ሲያደርግ ዝርዝር ጉዳይ ውስጥ አልገባም። ይሁንና በአማራ ክልል ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት በስውር ሲሰሩ የነበሩ የሽብር ሃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከመተማ መረጃ ያላቸውና የአይን እማኞች  ለዛጎል ተናግረዋል።

እንደ እንዚሁ ሰዎች ገለጻ ከሆነ በቅማንት ህዝብ ስም የሚንቀሳቀሰው አሸባሪ ቡድን በአማራ ክልል ልዩ ሃይል ውስጥ የዘረጋው መዋቅር ተመቷል። ከዚህም በላይ በተለያዩ የአስተዳደር መዋቅርና ቢሮዎች ውስጥ የሚሰሩ የነበሩ በርካታ የሽፍታው ተባባሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው።

ሕዝብ መንግስት ዝም ብሏል ቢልም የመከላከያ ሰራዊት አግባብ ካላቸው የክልሉ ሃላፊዎችና የጸጥታ መዋቅር፣ እንዲሁም ሰላም ወዳድ ከሆነውና ያለ እውቅናው የሚነገድበት ህዝብ ባደረገው ትብብር የሽፍቶቹ ምሽግ ሙሉ በሙሉ ወድሟል። ስፍራውም በመከላከያ ሙሉ ቁጥጥር ስር ውሏል።

ቀደም ሲል በሶማሌ ክልል ተሞክሮና በርካታ ንጹሃንን ሰለባ አድርጎ ያለፈው ጥቃት መቀልበሱ ይታወሳል። በኦሮሚያ ወንድም ወንድሙን እንዲገል ተወጥኖ የተጀመረው ግጭት በቅርቡ መክኖ ሰላም መውረዱ አይዘነጋም። በቦረናም በተመሳሳይ ሲካሄድ የነበረው ጭፍጨፋ አሁን መልክ እየያዘና ወደ አስተማማኝ እርቅ እያመራ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። በጋምቤላ ሊቀጣጠል የነበረው እሳት ወሃ በልቶታል። የአፋር ክልል ከቀድሞው ወረርሺኙ እንዲድን ስራ እየተሰራ ነው። የቢኒሻንጉል የደም አዝመራ ሙሉ በሙሉ ተገልብጦ  ዛሬ ሰላም እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት ከጅምሩ ከፍተኛ ችግር ቢጋረጥበትም በህዝብ ካለው ድጋፍ አንጻር በድል አልፏል። ህዝብ በትኩሱ አምጾ እንዲቀብረው ከፍተኛ ደባ የሚፈጸምበትና የሴራ ፖለቲካ የሚጎነጎንበት የአብይ አስተዳደር በአማራ ክልል ያለውን ተቀባይነት ለማሳነስና ህዝብ ላይ መከራ ሲደርስ ፍጹም መታደግ እንደማይችል ሲያቀርቡ የነበሩ አካላቶች ምላሽ ያገኙበት ርምጃ መወሰዱን ነው የመረጃው ሰዎች የሚናገሩት።

ይህንኑ ተከትሎ ይመስላል የ “ቅማንት ነጻ አውጪ” ወይም ሞት በሚል እስክስታና ከበሮ የሚደልቁ ሰሞኑንን ወደ ጦርነት ነጋሪት የተዛወሩት። አሁን እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በቀጥታ በመቃወም ሳይሆን በተዘዋዋሪ የጦርነት አዋጅ የማወጅ ያህል ጥሪ እየቀረበ ነው።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ለመንግስት ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለዛጎል እንዳሉት እዚህም እዚያም ቀውስ በመፍጠር የውክልና ግጭት የሚያስፋፉ አካላትን መንግስት ሲታገስ የቆየው ውስጡን እስኪያጠራ ነው። አሁን ባለው ሁኔታ በስለላና በምከላከያ ውስጥ ይህ የሰርጎ ገብ አካሄድና የቡድን አተያይ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የለም። በተለያዩ ቦታዎች ተከስተው የነበሩ ግጭቶችም ተወገደዋል። እናም ከዚህ በሁዋላ መንግስት በቀጥታ በማንኛውም አጥፊና የጥፋት ሃይሎችን እያደራጀ በሚልክ ሃይል ላይ የማያዳግም እርምጃ የመውሰድ ሙሉ አቅም አለው።

ህዝብን ከፊት በማድርገ የሚካሄዱ የፖለቲካ ጨዋታዎች ጉዳዩን ቢያወሳስቡትም ስርዓትን ማክበርና ህግን ጠብቆ መኖር ለድርድር ስለማይቀርብ በቅርቡ መንግስት ጥርት ያለ አቋሙን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። የመተማ ምንጭ እንዳሉት በቅማንት ምስኪን ህዝብ ስም ቁማር የሚጫወቱ አካላት ጉዳይ የሚያበቃበት ቀን እጅግ መቅረቡንም አመልክተዋል። ከዚህ ውጭ የመደረበና አሰልጥኖ ለሽብር የምሰማራቱ ጉዳይ የሚቀጥል ከሆነ የችግር አፈታቱ ሂደት ምን አልባትም ከመከላከያ ጋር በገሃድ ጦርነት የመክፈት ያህል ይሆናል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

የክልሉ መንግስት የፌደራል መንግስትን እገዛ በመጠየቁ መከላከያ በስፋት ሰላም ለማስከበር በሚንቀሳቀስበት ሁኔታ፣ የሚደረጉ ህግን የተላለፉ አካሄዶች በዝምታ እንደማይታለፉ ምንጮቹ አመልክተዋል።

ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ሰሞኑንን ቃለ ምልልስ አድርገው የነበሩት ብ/ጄ/አሳምነው ጽጌ “ብሬንና ድሽቃ ሁለቱም በከባድ መሳሪያ ምድብ ውስጥ ያሉ ናቸው፡፡ እነሱን በመደበኛ ሁኔታ ይጠቀማሉ፡፡ ይሄ አሁን የተለመደ ሆኗል፡፡ የቡድን መሳሪያዎችን ነው የሚጠቀሙት፡፡ ይሄን የሚያደርገው በሚገባ የሰለጠነ ፕሮፌሽናል የሆነ ኃይል ነው፡፡ ምንም ጥርጥር የለውም፡” ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

ሀገር ለመበታተን ለሚዘጋጁ ኃይሎች ሕብረተሰቡ ራሱን አሳልፎ እንዳይሰጥ፤ የበለጠ ነቅቶ ራሱን፣ ቤተሰቡንና አካባቢውን እንዲጠብቅ ራሱን እንዲከላከል ከምንም ነገር በላይ ደግሞ የራሱ አካባቢ ባለቤት ራሱ መሆኑን አውቆ መጠበቅ መቻል አለበት ያሉት ጀነራሉ ” ሕብረተሰቡ በየአካባቢው ራሱን አደራጅቶ እንዲጠብቅ ከመንግሥት በኩልም አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግለት ተነጋግረናል፤ ተግባብ ተናል” ማለታቸውም አይዘነጋም።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *